TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #83 · 8月30日

#旅游#福建#武夷山

Results

找到 1 条相似帖子

搜索 #digitalregistration

当前筛选 #digitalregistration清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52008 · 2026/03/03 12:45

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወንባቸው ሦስት ዘመናዊ አማራጮች ***************** ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚከናወነው የመራጮች ምዝገባ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ባገናዘበ መልኩ በሦስት ዋና ዋና አማራጮች እንደሚከናወን ቦርዱ አስታውቋል። የመጀመሪያው አማራጭ መራጮች በተለመደው አሠራር በአካል በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ምዝገባ የሚያከናውኑበት መደበኛ ሂደት ነው። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሂደቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ 'ምርጫዬ' የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ በቅርቡ ተደራሽ ያደርጋል። መራጮች ይህንን መተግበሪያ ከፕሌይ ስቶር (Play Store) ወይም ከአፕ ስቶር (App Store) በማውረድ ባሉበት ሆነው ራሳቸውን መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን፥ ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀውን የዌብ አማራጭ ሊንክም በቦርዱ ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል። ሦስተኛው አማራጭ ደግሞ በምርጫ ጣቢያዎች በሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች እገዛ በታብሌት (Tablet) የሚከናወን የዲጂታል ምዝገባ ሂደት መሆኑ ተገልጿል። በምርጫ ጣቢያም ሆነ በግል ስልክ የሚከናወኑት የዲጂታል ምዝገባ አማራጮች ተፈጻሚ የሚሆኑት ቦርዱ የኢንተርኔት ተደራሽነትን መሠረት በማድረግ ይፋ በሚያደርጋቸው የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ብቻ መሆኑ ታውቋል። በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል። #Ethiopia#Election2018#DigitalRegistration#NEBE#EthiopianElection#NewsUpdate