Death Toll from Gamo Zone Flood, Landslide now over 70. Read more. https://borkena.com/2026/03/12/ethiopia-death-toll-from-gamo-zone-flood-landslide-now-over-70/#Ethiopia#News#EthiopianNews#GamoZone#Landslide#flood
#Lantau#大屿山 之前购买过的,可以联系 @ljfxz 退款,直接发机场邮箱给他 剩余价值退款按照( 剩余时长*时长单价)+(剩余流量*流量单价)的形式退款 流量单价=套餐价格*0.8/套餐流量总数 时长单价=套餐价格*0.2/套餐时长总数 例如轻量套餐价格为9元,流量为80G,时长为30天。那天数单价为(0.2*9)/30,流量单价为(0.8*9)/80。 此时轻量用户还剩10天,流量还有70G,那退款为10*[(0.2*9)/30] + 70*[(0.8*9)/80] 注* 充了流量的钱也可退
找到 4 条相似帖子
搜索 #gamozone
የ3 ቀናት ብሔራዊ ሀዘን ታወጀ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው የመሬት ናዳ እና የጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የ3 ቀናት ብሔራዊ ሀዘን ታውጇል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፥ በዞኑ ጋጫ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ መጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ከጠፉ 125 ሰዎች ውስጥ የ80 ወገኖችን ሕይወት ማለፉን ገልፀዋል። የቀሪ ሰዎች አስከሬን ፍለጋ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ምክር ቤቱ በዜጎቻችን ላይ በተከሰተው አደጋ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶታል ብለዋል። በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፕብሊክ የሰንደቅ አላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ (2) ብሔራዊ የሀዘን ቀንና ሰንደቅ አላማው ዝቅ ብሎ የሚውለበለብባቸውን ሁኔታዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ መደንገጉን ተናግረዋል። በዚሁ መሠረት በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ዜጎቻችንን በማስመልከት ከመጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታውጇል ብለዋል። በእነዚህ ቀናት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ አላማ በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች፣ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንጽላ ጽ/ቤት ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ውሳኔ መተላለፉን ገልፀዋል። #Ethiopia#News#gamozone#ዜና#የጎርፍአደጋ#ጋሞዞን#ቦርከና_ዜና
በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት የሟቾች ቁጥር 107 ደረሰ። በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ፣ ካምባ እና ቦንኬ ወረዳዎች በደረሰ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ የ107 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ዋና አስተዳዳሪው በአደጋው 127 ሰዎች መጥፋታቸው እና እስካሁን አለመገኘታቸውን ገልፀዋል። በአካባቢው መልከዓ ምድር አስቸጋሪነት ምክንያት አስክሬን ፍለጋው መጓተቱን ተናግረዋል። ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የዕለት እርዳታ እየቀረበ መሆኑን ጠቁመዋል። #Ethiopia#gamozone#South_Ethiopia#ዜና#ቦርከና_ዜና#ጋሞዞን#የጎርፍአደጋ
እናት ከሁለት ልጆቿ ጋር በመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው አለፈ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ቤተሰብ የሆኑ እናትና ሁለት ልጆች ሕይወታቸውን አጥተዋል። አባወራው ከፍተኛ ጉዳት ተደርሶባቸው በቦንኬ ጋዜሶ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል። ከአርባ ምንጭ–ጊና–ቦንኬ የሚያገናኘው ዋና መንገድ በመሬት መንሸራተት ተዘግቶ በመገኘቱ ተጎጂውን ወደ ሆስፒታል ለማድረስ ችግር መፍጠሩ ተገልጿል። ዞኑ በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳና በከምባ ዙሪያ ወረዳ አካባቢዎች የጎርፍ ስጋት መኖሩን የጋሞ ዞን ፖሊስ አስጠንቅቋል፤ ነዋሪዎችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል። #Ethiopia#Borkena_news#Ethiopiannews#gamozone#አርባምንጭ#ጋሞዞን#ዜና#ቦርከና_ዜና