TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #11

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች79የዕይታ ቁጥር
ታትሟልሴፕቴ 1010/09/2023 08:18 ከሰዓት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

#HaSab #Veteducation የሀይስኩል ተማሪዎች ስለ እኛ ምን ያስባሉ? ዛሬ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በምሰራበት የኩሪፍቱ ሮትራክት ክለብ አማካኝነት ከ2ተኛ ደረጃ እና መሠናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር በ profession day መገናኘት ችዬ ነበር። የመርሃ ግብሩ ዋነኛ አላማ ተማሪዎች መሆን የሚፈልጓቸው ፊልዶች እና የስራ መስኮች ውስጥ ያሉ እና እየተማሩ የሚገኙ ሰዎች ስለ ሞያው መጠየቅ የሚፈልጓቸውን ጥያቄዎች በመጠየቅ ተጨባጭ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ ነበር። እኔ የእንስሳት ህክምና ተማሪዎችን(DVM) በመወከል ከጎኔ የምትመለከቷት ምዕራፍ ተወልደ ደግሞ የእንስሳት ህክምና ላቦራቶሪ ቴክኖሎጂ(VLT) ተማሪዎችን በመወከል ተገኝተናል። በዝግጅቱ ላይ ከተገኙት ተማሪዎች እጅግ ጥቂት የሚባሉት ወደ እኛ በመምጣት ስለ እንስሳት ህክምና ለማወቅ ፍላጎት ያሳዩ ሲሆን፤ የጥያቄዎቻቸው ይዘት እና ማወቅ የሚፈልጉት ከዚህ በማስከትል የዘረዘርኳቸው ሆነው አግኝተናል። -የእንስሳት ህክምና ክትባት ከመስጠት ውጪ ምንድነው የሚሰራው? -የእንስሳት ህክምና ከሰዎች ህክምና የሚለየው ምንድነው? -የእንስሳት ሀኪም ሰውን ማከም ይችላል? -የእንስሳት ህክምና ትምህርት ጊዜ የሚፈጀው ምን ያህል ነው? -እኔ የእንስሳት ሀኪም መሆን እፈልጋለሁ ግን የእንስሳት ሀኪሞች ደግሞ ብር ብዙ አያገኙም! -ሰዎች ያን ያክል ትኩረት ሰጥተው እንስሳን ያሳክማሉ? -በውሻ ተነከስን ስንል ሀኪሞች ውሻው አምጡት የሚሉን ለምንድነው? በአጠቃላይ ለተጠየቅናቸው ጥያቄዎች የእንስሳት ጤና ዘርፍ የስራው መስክ ሰፊ እና ጉራማይሌ መሆኑን አውስተን በአጭሩ ለመረዳት፤ የክሊኒክ ስራዎች(Clinical practice)፣የስነ ህይወት ጤና ምርምሮች(biomedical researches)፣ ትምህርት(education)፣ የላቦራቶሪ ምርመራዎች(diagnostic laboratory)፣ የማማከር ስራ(consultation)፣የሀገርን የምግብ ደህንነት እና አቅርቦት ማሳለጥ( safeguarding our nations food safety and supply)፣እና የህብረተሰብ ጤና(public health) የትኩረት አቅጣጫቸው መሆኑን ለማስረዳት ሞክረናል። ከነበረን ቆይታ እንደተረዳነው የሚመጣው ትውልድ ስለ እንስሳት ህክምና በወፍ በረረር ከመስማት ውጪ ገና በበቂ እንዳላወቀው እና አሁን ያለውጰባለሞያ ያለበት የኑሮ ሁኔታ ወደፊት እኔም ብገባ እንዲህ ነው የምሆነው የሚል ስጋት እንዳለው ተረድተናል። በተጨማሪም ሰዎች በግል የሚሰሯቸው የእንስሳት እርባታ እና መሰል ስራዎች በሌሎች የዘርፉ ባለሞያ ባልሆኑ ሰዎች በሰፊው እንደመሠራታቸው እንዲህ ያለው ስራ አላማ ተይዞለት ለትምህርት እንደሚገባ ግንዛቤው ያለ አይመስለኝም። ለእንሰሳት ያላቸው ርህራሄ እና ፍቅር ግን እጅግ አስደሳች መሆኑን በሚያወሩን ጊዜ መታዘብ ችለናል(ስለ ውሾቻቸው ሲያወሩ ፊታቸው ላይ ያለው ፈገግታ ይማርካል) ስለዚህ በሞያችን ውስጥ ንቁ እና ደስተኛ ብሎም አርአያ የሚሆን ባለሞያ እንዲኖር። መጪው ትውልድ ከተቀዳሚ ምርጫዎቹ መካከል የእንስሳት ጤና ዘርፍ እንዲኖር የሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት ቢሰጥባቸው እላለሁ። -የእንስሳት ጤና ባለሞያው በይበልጥ የሚሻሻልበት እና ዘርፉ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ ቢሆን -በግል ሴክተር ውስጥ ጠንካራ ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉ የእንስሳት ጤና ዘርፍ ምሩቃንን ማፍራት -በእያንዳንዱ ወረዳ የሚገኝ የእንስሳት ሀኪምና ባለሞያ የደሞዝ እና ደረጃ እድገት ቢሻሻል -ጥሩ ስነ ምግባር እና ሞያ አክባሪነት ያለው አርአያ መሆን የሚችል ማፍራት። እኚህን ጉዳዮች ትኩረት አድርጎ መሥራት የእንስሳት ጤና ዘርፍ ለሚመጣው ትውልድ በልበሙሉነት የሚመርጠው ሞያ እንዲሆን ማድረግ እንደሚችል ልባዊ እምነቴ ነው። ያሬድ ኤርሚያስ 3rd year DVM student, AAU-OHC Founder and secretary, Membership director of Rotaract club of Kuriftu.