የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
መለያ: #hasab · 17 ልጥፎች
#HaSab ለቅዳሜያችን! ብዙ ሰዎች Animal welfare እና Animal rightsን ተመሣሣይ አድርጎ ስለሚጽፍ እዚህ ጋር አንድ ነገር ልበል። በእንስሳት ጉዳይ የተለያዩ አስተሳሰቦች አሉ። ያው አስተሳሰባቻችን ካለንበት ማህበረሰብ እሳቤ ፣ ሀይማኖት ጋር ቁርኝት ያለው ቢሆንም ጠቅለል አድርገን በሦስት ከፍለን መመልከት እንችላለን። 1. Pro-animal use ይህን ሀሳብ የሚከተሉ ሰዎች The use of animals to save life of human being and others is "absolutely essential" ብለው የሚያምኑ ናቸው። ሰዎች እንስሳት የመጠቀማቸው ጉዳይ የግድ ነው አይነት አኪያሄድ ነው ያለቸው ለአብነት የ Pasteurን በውሻ ላይ ያደረገውን experiment በመጥቀስ "Human and animals would still be dying from Rabies if Pasteur Hadn't experimented with dogs." ብለው ይከራከራሉ፣ በተለይ ለምርምር እንስሳትን አንጠቀም የሚል አሳብ የሚያበሽቃቸው አይነት። 2.Welfarists/ Utilitarianism የእንስሳት ደህንነት This accepts the uitility status of animals as long as animals suffering is minimized as much aa possible, and believe animal suffering is morally relevant. ለምግብነት ማዋልን ጨምሮ እንስሳትን በመጠቀም የሚያምኑ ሲሆን ነገር ግን አላስፈላጊ የሆነ ስቃይን በማስወገድ የሚያምኑ ናቸው። እንስሳትን ለጭነት መጠቀም እንችላለን ግን ከአቅማቸው በላይ አይሁን፣ እንስሳትን መመገብ እንችላለን ግን የሚሞቱበት መንገድ ስቃይ ያለበት አይሁን የሚሉ ይዘቶች ያላቸው ሀሳቦች የሚገዟቸው ሰዎች ያሉበት ነው። የእንስሳት ደህንነት እንስሳት አምስት መሠረታዊ ፍላጎቶች እንዳሏቸው ያምናል -ምግብ እና ወሃ የማግኘት -ከህመም ፣ ከመቁሰል እና በሽታ መራቅ -ተፈጥሯዊ በሃሪን ማንጸባረቅ - ጥሩ ምቾት የማግኘት (መጠለያ) - ከፍርሃት እና ጭንቀት የመራቅ የእንስሳት ደህንነት በአንፃራዊነት ከሌሎቹ ይልቅ በብዙ ሀገራት ተቀባይነት አለው። አንድ ሀገር የእንሰሳት ደህንነት ህግ ማርቀቅ አለማርቀቋ በእንስሳት ተዋጽኦ ኤክስፖርት ንግዷ ላይ (በተለይ ከአውሮፓ ሀገራት ጋር በምታደርገው) ቀጥተኛ የሆነ ተጽእኖ አለው። አውሮፓዎቹ በምንም አይነት ሁኔታ እንስሳት ደህንነታቸው ባልተጠበቀ ሁኔታ ተይዘው የተመረቱ ነገሮችን አትቀበልም። ሀገራችንም የእንጽሳት ደህንነት ረቂቅ አዋጅ ዘንድሮ ነው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቀችው። 3. Abolitionist / Animal right የእንስሳት መብት Animal rights are moral principles grounded in the belief that non- human animals deserve the ability to live as they wish, without being subjected to the desires of human being. እንስሳትን እንዳሻቸው እንዲኖሩ እንፍቀድላቸው የሰው ልጅ የተፈጥሮ የበላይ ነኝ ሁሉ ነገር ለኔ ነው የተፈጠረው egoን ይተው አይነት ይዘት ያለው እሳቤ ነው። Animal rights come into direct opposition with animal exploitation, which includes animals used by humans for a variety of reasons, be it for food, as experimental objects, or even pets. Animal rights can also be violated when it comes to human destruction of animal habitats. This negatively impacts the ability of animals to lead full lives of their choosing. ይህ አይነቱ ሀሳብ እንደ እኛ ላለ ሀይማኖተኛ ሀገር ከባድ ቢሆንም በዚህ በጽኑ የሚያምኑ ሰዎች ገጥመውኝ ያውቃሉ። ብዙ ያስተዋልኩት ነገር ግን ስለ እንስሳት ያለን አስተሳሰብ ከባህል ፣ ሀይማኖት እና ህግ ባሻገር በግል አመለካከታችን ተጽእኖ ውስጥም ይወድቃል። እኔ በእንስሳት መብት አምናለሁ ብሎ የእንሰሳት ደህንነትን የሚበድል ነር የሚያደርግ። ከላይ ተጠቀስናቸውን ነገሮች ምንም ሳይሰማ ለእንስሳት የሚራራ ሰውም አለ። ብቻ ሀሳቡ ብዙ ነው። ከ vet Ethics course በመጠኑ የተመለሰ! የእናንተ ምልከታስ ምንድነው? https://t.me/campus_voice_2016
Hashtags
#haSab Did you know that a handful of staple crops replaced the once-wide range of subsistence crops? 75% of Crop Varieties disappeared over the 20th C only three plant crops (Maize, rice & wheat) accounted for 41% ofthe world's Caloric intake. What Do you think on bringing back neglected crops? Share ur #haSab on @yared2774
Hashtags
#HaSab #Animal_welfare #Against_Donkey_slaughtering_For_Ejiao የአፍሪካ መሪዎች ጎሽ የሚያስብል ውሳኔ አስተላልፈዋል! ተፈጻሚነቱ የእኛን ክትትል ይፈልጋል። ከዚህ በፊት ይህ ጉዳይ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ Viral ሆኖ ሲዘዋወር ሁላችንም እናስታውሳለን። የአህያ ቄራ ጉዳይ። "At first our governments saw this as an opportunity, and many legal slaughterhouses opened in Africa, But between 2016 and 2019, about half of our donkeys were killed for the trade." ይህን የተናገሩት ዶ/ር ሰለሞን ኦንያንጎ(Dr Solomon Onyango) ከኬኒያው Donkey Sanctuary ከBBC ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው። አብዛኛዎቹ ሀገራት ቻይና የአህያ ቆዳ እንድትልኩልኝ እፈልጋለሁ ስትል ጉዳዩን የቆጠሩት እንደትልቅ እድል እና የውጪ ምንዛሪ ማግኛ መንገድ ነበር። ነገር ግን ለኢጃኦ የሚፈለገው የአህያ እርድ ከጥቅሙ ጉዳት የጎላ ሆኖ ተገኝቷል። ያሳለፍነው እሁድ የካቲት 10 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ የአለም የአህያ ብዛት 2/3 የሚይዙት 55 ሀገራት ግሽ የሚያስብል ውሳኔን አስተላልፈዋል። በአፍሪካ ለቆዳ ንግድ አህያ ማረድ ከእንግዲህ ወንጀል ይሆናል። ይህ ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ግን የእንስሳት ጤና እና ደህንነት ላይ የሚሰሩ ተቋማትን ብርቱ ክትትል ይፈልጋል። በተለይ በኢትዮጵያ ጉዳዩ የመንግስትን ይሁንታ ያገኘ እና ለህዝብ በቂ የሆነ መረጃ የሚሰጥበት ግልጽ ንግድ ባለመሆኑ በርግጥም ይህ ውሳኔ ተፈጻሚ መሆን አለመሆኑን እየተከታተለ ለህዝብ የሚያደርስ እና የሚጠይቅ አካል መኖር ግድ ይለዋል። ለዚህ ተቀዳሚዎቹ ባለ ሀላፊነቶች እኛው በዘርፉ ያለን ባለሞያዎች ነን። ሁሉም ሰው እንዲገነዘብ የምፈልገው ነገር ቢኖር ይህንን ንግድ የምንቃወምበት አበይት ምክንያት ንግዱ ቀጣይነት የሌለው እና ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን በመሆኑ ነው። ይህን ቻይና ራሷ ተመልክታዋለች። ከዚህ ቀደም የኢጃኦ ፍላጎቷን ለማሟላት ከራሷ ብቻ የአህያ ቆዳ ትጠቀም የነበረ ቢሆንም በሀገሪቱ የሚገኘው የአህያ ቁጥር እጅግ በመመናመኑ ፊቷን ወደሌሎች ሀገራት አዙራለች። ፊቷ የዞረባቸው ሀገራት ሁሉ በዚህ ንግድ መጎዳታቸውን አምነዋል። በአጠቃላይ የቻይና የአህያ ቆዳ ፍላጎት አለም ካላት 53 ሚልየን አህያ ቁጥር ጋር አይመጣጠነም። በአፍሪካ ለአህያ ደህንነት መሟገት ቅንጦት አይደለም! ለገጠር ማህበረሰብን ህልውና መቆርቆር እንጂ። ቸር ያቆየን! ያሬድ ኤርሚያስ
#HaSab #collaboration Yo! How do you see your classmates, dorm mates, or the midfielder on the football field, the high-achieving student at the college? The active and interactive one? How do you see your surroundings? Let me tell you about a bunch of opportunities you shouldn't miss! If you're in an environment that has the chance to be exposed to diversity, this blog is for you! እንደ ግለሰብ የትምህርት ስርዓታችን የአንደኝነት አተያያችንን አዛብቷል ብዬ አምናለሁ። ከታች ጀምሮ ተሻግረን ከመጣናቸው ብዙ ደረጃዎች ስኬት በላይ በተቀደምነው አንድ ደረጃ ላይ ትኩረታችንን እንድናደርግ ሁነናል! ቀለሜዎች ከእናንተ መሃል ሁለተኛ ስለወጣ ያላዘነ ማነው? ከደረደራቸው ብዙ A+ በላይ የተፎካካሪው B ያላስደሰተው ማነው? በርግጥ አንዱ ሌላውን የመብለጥ ጉዳይ ተፈጥሯዊ መሆኑና ሁላችንም የአሸናፊነት ስሜት እና ወኔ ሌኖረን የተገባ ቢሆንም ለአንደኝነት ያለን ግምት እና የትምህርት ስርዓታችን ውስጥ ያለው የእሽቅቅድም ስሜት ግን አንድ ከአሸናፊነት ማማ ሁላችንንም የሚያወጣን መንገድ ወደጎን እንድንተው ያደረገ ይመስለኛል! መንገዱን ጠየከኝ? ቆይ እነግርሃለው ታገስ! እየተማርክ ያለኸው ዘርፍ እንደ ባህር ያለ ነው። ብትቀዳው ከያዝከው አቁማዳ በላይ የሆነ፣ ሞልቶ የሚፈስ። ስለዚህ ከምትማራቸው እልፍ ጉዳዮች በተወሰኑት ላይ ብቁ እና ከሁሉም የተሻልክ መሆንህ አይቀሬ ነው። የተወሰኑት ደግሞ ትኩረትህን ላይስቡት ይችላሉ። ወዳጅህስ? ክፍል ውስጥ ከጎንህ ያለው ተማሪ በየትኛው ሌክቸር ክላስ ይመሠጣል? ዶርም በሶ አብሮህ የሚበጠብጥ ጓደኛል የትኛውን ኮርስ ፈተና ቢኖር ባይኖር ሁሌም ያነባል? የተኛው ወዳጅህ ከየትኛው የ Clinical case ፊት አታጣውም? ይህንን የምጠይቅህ አውቀህ እንድታደንቀው ብቻ አይደለም! ማድነቅ እማ አለብህ! ነገር ግን ልነግርህ ያሰብኩት ከዛ ይልቃል። Actually its a good opportunity you shouldn't miss! potential collaborator! አዎን የዛሬው ዶርም ሜትህ የነገ ትልቅ ቢዝነስ ካምፓኒ ፓርትነርህ ሊሆን ይችላል። ዥረት የሚፈጥሩት የመርፌ ክር ታህል ቅጥነት ያላቸው የወሃ መስመሮች ተዋህደው ነው። በጋራ ጥሩ የሆናችሁበትን ነገር በማዋሃድ አልያም አንዳችሁ ጎበዝ የሆናችሁበት ነገር የሌላኛችሁን ክፍተት እንዲሞላ በማድረግ ነገ ትልቅ ደረጃ የሚደርስ #HaSab ማፍለቅ ትችላላችሁ። እመኑኝ ከግቢ ከወጣችሁ በኋላ ይህን እድል አታገኙትም! ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ገንዘብ ያለው ሰው በብዛት የሚሰማራው ንግድ ላይ ነው! ብራቮ እናንተ ደግሞ ካፒታላችሁን በጋራ አድርጋችሁ ከባንክ ብድር ተባጥሳችሁ አምራች መሆን ትችላላችሁ። በየትኛውም መስክ ሊሆን ይችላል። ይህን የሚወስነው ያንተ እና የወዳጅህ እውቀት እና ፍላጎት ነው። ከፉክክር ይልቅ የትብብር ሀይል ይበልጥ ያደምቃል። ለየብቻችን ጭላንጭል ብርሃናትን መፍጠር ላይከብደን ይችላል። መድመቅ ግን ያለው ከህብረት ነው። ከባህር ውስጥ ብዙ ወሃ የሚጨልፈውም ቢሆን ከአንድ ይልቅ ሁለት ሦስት አቁማዳ ነው። አሁን ያለው ገበያ እጅግ ፉክክር ያለበት እና ንቁ አምራች እና ሻጭ የሚፈልግ ነው። Dave Ramsay ምን ይላል መሠለህ:- " Marketing is not an option for business that wants to keep their doors open." ሁሌም በሩ ክፍት የሆነ የማይናወጥ ስኬታማ የስራ መስክ ከፈለክ የያዝከውን እውቀት፣ ጥበብ፣ ልምድ ፣ የፈጠራ ሀሳብ እና ገንዘብ ይበልጥ እንዲያተርፍ አድርገህ መሸጥ የምርጫ ጉዳይ አይደለም!! ግዴታ እንጂ። ስለዚህ የምረቃ ጋወንህን እንዳወለክ ያለህን ለረጅም አመት ተባብረህ ካጠናኸው አብሮ አደርህ(dorm mate ለማለት😁) አልያም ብርቱ ከምትለው ወዳጅህ ጋር አዋህደህ በ bulk አምርት። በገበያው ውስጥ ሁሌም ክፍት የሆነ ቢዝነስ ይኑርህ! why not? ይህንን የጻፈልህ ያሬድ ነው። ገና ተማሪ ሳለህ በተለይ በአንድ ጤና እሳቤ፣ በእንስሳት ደህንነት ዙርያ መሥራት የምትፈልገው ልዩ ሀሳብ ካለህ መተባበር እንችላለን። ማናችንም የምንሰራቸው እያንዳንዱ ስራዎቻችን የሰዎችን፣ የእንስሳትን እና የአከባቢ ጤናን ያገናዘቡ ሊሆኑ ይገባል። እኚህን የሚያጓድል ስራ ብኩን ነው። የእንስሳትን ደህንነት የሚጠብቅ ሰው ሩህሩህ ነው። ርህራሄ እውቀት ብቻ ሳይሆን ለተፈጥሮ የሚጨነቅ መልካም ልብን ይፈልጋል። ይህን ለመፍጠር ትሩ ግንዛቤ እና ሁሉን ማጣቀሻ የሚደርገው የጋራ ህግ ያስፈልጋል። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ መስራት ፋይዳው ብዙ ነውና አሳብህን ልታጋራን ወደኋላ አትበል። ሀሳብህን መሬት ለማውረድ እና ተጽእኖ ለመፍጠር መተባበር እንችላለን። የተለየ #HaSab ካለህም አጋራን። @Adey67@yared2774 ደግሞ እንዲያነቡ ወዳጆችህን ጋብዝ! መልካም የረፍት ቀን!!
Hashtags
#Advocacy #HaSab ውረድ ወደ መሬት! አሁን አሁን አዲስ ነገር ሳነብ ወይንም ከመምህሬ ስሰማ አንድ ሀሳብ ደጋግሞ በምዕናቤ ይመላለሳል:-'Ah, what if I had learned this earlier?!'🤦♂️ ብዙዎቹ ከጤና ጋር የተያያዙ ጉዳዎች በሀገራችን ለመላምት የተጋለጡ ናቸው። ሁሉም የመሠለውን ይናገራል። በርግጥ ከመላምት የተሻገሩ ባህላዊ እውቀጦች እንዳሉ ባይካድም.... እናም በልጅነት አእምሮም ይሁን ሁነኛ መረጃ በማጣት የብርቱካን ፍሬ ውጦ ከመችመች በአናቴ የዛፍ ቅርንጫፍ ተንዠረገገ እንደሚል ብላቴና ሆኜ ያሳለፍኩባቸውን ጊዜያት ሳስብ ፈገግ እላለሁ። ከነበርኩበት ላይብረሪ አልያም ከመማርያ ክፍል ወጥቼ ለማህበረሰቤ በሚያውቀው ቋንቋ፣ በሚረዳበት አዎድ "ይሄ የሆነው ለዚህ ነው፣ ይህ ማለት ይህ ነው!" ማለት ያምረኛል። ብዙውን ጊዜ የምንነጋገረው እርስ በእርስ ነው። (እዚህ LinkedIn ላይ ራሱ ስንት blog አነበብኩ ስንት የታተሙ ጆርናሎች አስደነቁኝ) በሞያዊ ቋንቋችን ባለን የትምህርት ደረጃ ልክ እንወያያለን እንከራከራለን ከድምዳሜ እንደርሳለን። የሚዘጋጁ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችም የሚሞሉት በባለሞያው ነው። ይህ እርስ በእርስ እንድንግባባ ቢያደርገንም ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ገና ብዙ እንደሚቀረን ጠቋሚ ነው። ለዛ ይሆን የመፍትሄ ሀሳቦቻችን መሬት የማይወርዱት? ዋናው ችግር ያለው መሬት ላይ ነው። ለመሬት እጅግ ቅርብ የሆነው ደግሞ አራሹ ነው። ህመም የጅማሮ ምልክቱን የሚያሳየው ቤት ነው። ቤት ውስጥ ያለው ደግሞ ቤተሰብ ነው። ኤኮኖሚው ሲዘም የሚያርደው የቤቱን ምሰሶ ነው። ምሰሶውን ቀጥ አድርጎ ለማቆም መሰሶ ካለበት መሄድ ያሻል። ስለዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫዎቻችን እርስ በእርስ ካለን መድረኮች የሚሻገሩ እና ማህበረሰቡ በማረዳው ቋንቋና አውድ የተተረጎመው ሆነው የሚዘጋጁ ለማድረግ ብዙ መስራት ያለብን ይመስለኛል። ባለሁበት የእንስሳት ጤና ዘርፍ - ስለተለያዩ ምርታማነትን የሚቀንሱ የእንስሳት በሽታዎች ( animal production and health) - ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በተዋሲያን የሚመጡ በሽታዎች (Zoonosis) - ስለ ጸረ-ተዋሲያን መድሀኒቶች በጀርሞች መላመድ ( antimicrobial resistance ) - ስለ ምግብ ደህንነት (food safety) - ስለ እንስሳት ደህንነት እና ፋይዳው ( Animal welfare and its impact ) - የማህበረሰብ ፣ እንስሳት እና አከባቢ ጤና ግንኙነት ( one health ) ማህበረሰቡን ለማስተማር ግንዛቤ ለመስጠት እና ለውጥ ለማምጣት ጽኑ ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ በጋራ መስራት እንችላለን። ያወቅነውን የማሳወቅ ሐላፊነት አለብንና! Advocacy for the community should be a slogan like "መሬት ላራሹ!" Lets connect on LinkedIn መልካም የረፍት ቀን!
#HaSab #Experience_sharing በመጀመሪያ ይሄንን በጎ ተግባር በመደገፍ ፈጣሪ ከሰጣችሁ የህይወት ጊዜ መካካል ከ-120 ደቂቃ በላይ ጊዜያችሁን መስዋዕት በማድረግ ይሄ በጎ ተግባር የፀነሰውን እና የሚወልደውን በጎ አላማ ደግፋችሁ ለማዋለድ እና ለማረስ እኛ ጋር የተሰማራችሁ ሁሉ በ-3-H Initiative ስም ከልብ እናመሰግናለን። ዛሬ እኛ 3-H-ኦች ፣ የዕለቱ ተጋባዥ የክብር እንግዳችን (Prof. Alemayehu Lemma) እና የተነገረው የዕለቱ መልዕክት የሚመለከታቸው ተሳታፊ ተማሪዎቻችን የነበረን የጋራ የአብሮነት ጊዜ It was really ineffable and ethereal. ተጋባዥ እንግዳችን (Prof. Alemayehu Lemma) ተማሪዎችን ይመለከታሉ ብለው የሚያምኑባቸውን የእሳቸውን የህይወት ታሪክ እና ተሞክሮ ማለትም ያጋጠሟቸውን መሰናክሎች ፣ ያለፉባቸውን ውጣውረዶች እንዲሁም እሳቸው አሁን ካሉበት ደረጃ እንዲደርሱ ያደረጋቸውን እና ያስቻላቸውን ጥሩ አጋጣሚዎች በጥሩ ለዛ እና በማራኪ አንደበት ለታዳሚያን አቅርበዋል። እሳቸው ከተናገሯቸው ንግግሮች መካከል የተወሰኑትን እነሆ :- # " U guys have to be persistent and u have to have consistency in order to get what u want ur life" # " ተሰፋ መቁረጥ የሚባለው ነገር በኔ Dictionary ውስጥ አልነበረም" # "ሁሉን ነገር ለመሞከር አላመነታም ፤ የተማርኩትን ነገር እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ወደኋላ አልልም ነበር" # "Failure/ውድቀትን እንደ-ጥሩ አጋጣሚ ከመጠቀም ባለፈ ተስፋ አስቆርጦኝ አያቅም" # "የደሀ ልጅ ሲኒማ ቤት ላይብረሪ ነው ፤ ላይብረሪ ገብቶ Encyclopedia እና ሌሎች ትምህርት አዘል ቁምነገሮችን መቅሰም እና መሸመት በጣም እወድ ነበር While I was in University" # "የእናንተ grade እናንተን አይወስንም ፣ ትክክለኛውንም የእናንተን ማንነት አይናገርም ፤ Ur grade doesn't define u" ከላይ ለመጥቀስ የተሞከሩት ሀሳቦች Prof. Alemayehu Lemma ዛሬ ከእኛ ጋ በነበራቸው ቆይታ ከእሳቸው አንደበት ከፈለቁት ወርቃማ ንግግሮች መካከል የሚጠቀሱ እና በማይሆን ጭንቅላት ውስጥ ገብተው እንዳይባክኑ የሚያሳሱ Powerful thoughts ነበሩ ፤ The most exciting thing is that እዛ ተሰብስበን የነበርነው ስብስቦች ሀገርን ከ-ውድቀት እንዲሁም ትውልድን ከጥፋት ለመከላከል የተለየ ግን አንድ አይነት አስተሳሰብን ሲያራምድ ፣ እያራመደ እና ለማራመድ ያሰበ ስብስብ ነበር። ከ-Prof.Alemayehu Lemma ጋር ከነበረን የጋራ እና የአብሮነት ጊዜ በኋላ ተማሪዎች ስለ-ፕሮግራሙ የነበራቸውን የልብ ትርታ እና አስተያየት ለማወቅ በግል እና በቡድን አስተያየታቸውን ከ-አንደበታቸው በሚፈልቁ ቃላት ለመገምገም ጥረት አድርገን ነበር ፤ እናም ያገኘነው response አበረታች እና ይበል የሚያሰኝ ነው። ከተማሪዎች አስተያየት መካከል የተወሰኑትን ጀባ ለማለት ወደድን፦ - " Dedicated መሆንንና የህይወትን ጥፍጥና ሰው በመሆን ማጣጣም እንዳለብኝ ተረድቻለሁ" ሳሙኤል ይፍረደው-3rd year DVM - " ፍዳየን ብበላም የምፈልገው ነገር እስኪሳካ ተስፋ መቁረጥ እንደሌለብኝ" ባድማው ይታይህ-4th year DVM - "እስካሁን መኖር እንዳልጀመርኩ እና ከ-አሁን በኋላ ግን መኖር እንዳለብኝ ተረድቻለሁ" ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ተማሪ - " የህይወቴን ማርሽ የምቀይርበትን ዲስኩር አግኝቻለሁ" ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ተማሪ - "On Dec 16,2023 Everyone one was over the moon and on cloud nine by the event that was held on year 5 class. We really had a whale of time" Someone amongst of today's participant. ከላይ የተጠቀሱትን እና ከላይ የተጠቀሱትን መሰል ሀሳቦች እና አስተያየቶች ከተለያዩ የተማሪ አንደበቶች ለማግኘት የቻልን ቢሆንም ለማቅረብ የተገደድነው ግን የተወሰኑትን ብቻ ነው። የ-Prof.Alemayehu Lemma-ን recorded voice /ድምጥ በቅርቡ በዚሁ በ-3-H initiative የ-telegram group ላይ የምንለቅ መሆኑን ከወዲሁ እያስታወስን ስለነበረን የአብሮነት ቆይታ በድጋሚ በ-3-H initiative ስም ለማመስገን እንወዳለን። "Positive ነገሮችን በጭንቅላቱ አስቦ ፣ በልቡ አመዛዝኖ ፣ በእጁ ተግባር ላይ የሚያውል እንዲሁም ሀገርን ከውድቀት የሚታደግ እና ትውልድን ከጥፋት የሚከላከል ትውልድን እንቀርፃለን።" 3-H initiative #3_H_Initiative t.me/Head4Heart4HandInitiative ተፃፈ በ-Jemal D. Mengistu (James)
We are thrilled to announce the launch of new hashtag on our channel: #HaSab #ሀሳብ it's a fascinating hash tag platform dedicated to share insightful opinions about veterinary fields, Animal production, food safety, public health, animal welfare, one health, entrepreneurship and other related issues. The term #HaSab means "opinion" in Amharic, and its purpose is to stimulate constructive discussions and encourage meaningful change. We believe that every individual's opinion is valuable and unique, based on their own experiences, studies, and thoughts. By sharing your opinion through this platform, you can contribute to better understanding the challenges we face and inspire others to take action. We challenge all members of our channel to participate in this exciting initiative and collaborate with us in finding solutions to the problems we encounter as a sector and a country. Don't hesitate to contact us at @yared2774 & @adey67, and let's start sharing our opinions using #HaSab! https://t.me/Hasab_2016
#HaSab #Animalhealth ✳️ሰላም ውድ የCVMA ማህበረሰብ ቻናል ቤተሰቦች እረፍት እንዴት ነው? በምንስ እያለፈ ነው? ጥሩ እና አሪፍ ነው የሚል ምላሽ እንደሰጣችሁኝ አልጠራጠርም። እንደ ግሌ አንዳንድ የተሰሙኝን እና መናገር አለብኝ ብዬ ያሰብኳቸውን መልዕክቶች ለማጋራት ወደድኩ። ✳️ስሜ በተስፋሁን ይባላል የካምፓስ Voice መስራች እና Editor ነኝ። ሁል ጊዜ የትምህርት መንፈቀ አመት ከተጠናቀቀ ቡኃላ የእረፍት ጊዜ ሲመጣ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ብዙ በማቀድ ትንሽ በመስራት የማሳልፍ ነኝ፤ የምሰራት ስራ ትንሽ.....ነገር ግን ፍሬያማ እንድትሆን እጅጉን እተጋለሁ።ጓደኛዬ ያሬድ በምንሰራቸው ስራዎች ሁሌም ጉልህ ሚና ይጫወታል።በምንሰራቸው ብቻ ሳይሆን ከእኔነቴ እንዳልጎድል እንደ ታላቅ ወንድም No በተስፋ ይሄ ጥሩ አይደለም ይለኛል። ✳️ብቻ ለእኔ መሰረት መያዝ ጉልህ ሚና የተጫወተ እና ወደፊትም የሚጫወት ወንድሜ ነው ዛሬ ለወንድሜ ያሬድ Credit ለመስጠት ወይም ስለግል ታሪኬ ለማጋራት ሳይሆን አሁን ያለሁበት ጅማ ከተማ ከመጣሁበት ሰዓት አንስቶ ለሞያችን እድገት መንቀራፈፍ እንደ ግብዐት ሆኖ የሚያገለግሉ ችግሮችን ለመጥቀስ ነው።በእርግጥ በአሃዝ የተገለፀ ቁጥራዊ መረጃ ባይኖረኝም በአይኔ አይቼ በልቤ ያስተዋልኳቸውን ችግሮች እንደሚከተለው እዘረዝራለሁ። ✳️እዚህ ያለሁበት ጅማ ከመጣሁ የመጀመሪያ ችግር ሆኖ ያየሁት የመድኃኒት እጥረት ነው፤ ይሄ ችግር ቀላል የሚባል አይደለም። ለምሳሌ በ 2030 እናጠፈዋለን ብለን ዘመቻ ለጀመርነው Rabies virus vaccination የመድኃኒቱ አቅርቦት ማነስና በተገቢው አለመሰጠት ትልቅ ተግዳሮት ይሆናል። ጅማ ላይ አምና እና ካቻምና በጠየቁበት ሰዓት በርካታ Vaccine የተላከ ቢሆንም ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስላልተሰጠ የህክምና ጣቢያ የመጡት ብቻ ተከትበው መድኀኒቱ ሙሉ ለሙሉ Expired ሆኗል። አሁን ለእረፍት በገባውበት ሰዓት ደግሞ ተማሪዎች አስተባብረን ለመከተብ ስናስብ የመድኃኒት አቅርቦት የለም።ሚገርም ነው መድኃኒቱ ሲገኝ ባለሙያዎች ትኩረት አንሰጥም😔ትኩረት ስንሰጥ ደግሞ መድኃኒት የለም😔ብቻ Rabies Vaccine እንደምሳሌ አነሳው እንጂ በርካታ መድኃኒት በየህክምና ጣቢያው የለም!!! ያለውም ከጥቅም ውጪ እየሆነ ነው። የሚመለከተው አካል ትኩረት ቢሰጠው እላለሁ 🙏🙏🙏 ✳️እኛም እንደ ተማሪና ጉዳዩ ይመለከተኛል እንደሚል ባለሙያ ምን መደረግ ነበረበት❓ምንስ እናድርግ❓ ✳️ሁለተኛ በሀገር አቀፍ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ምክንያት እና በተለያዩ ምክንያቶች የህክምና ጣቢያዎች ዝግ ይሆናሉ። እንደ ጅማ ከሰሞኑ Emergency case መተው እርዳታ ባለማግኘታቸው የሞቱብን እንስሳት በርካታ ናቸው Including my neighbouring dog 😔። ጊቢው እንዲፈቅድ ባለሙያዎቹ ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ማንም ሰው የህክምና ቅጥር ጊቢ ውስጥ መገኘት ስለሌለበት እንደተከለከሉ ሰምቻለሁ። ✳️ምን ያክል የእንስሳት ህክምና ጣቢያዎች እንደ ሀገር ተዘግተው ይሁን❓ይሄን ተከትሎም ምን ያክሉ እንስሳት መዳን እየቻሉ ሞተው ይሁን❓በአንጋፋው CVMA እንኳን የአገልግሎት ጊዜ ከጠዋት 2 ሰዓት እስከ ቀን 6 ሰዓት ብቻ ነው አገልግሎት የሚሰጠው WHY❓እንደግሌ አልተመለሰልኝም❓እንደኔ እንደኔ ወጣት እና በቂ የሆነ የሰው ኃይል በዲፓርትመታችን አለን ቢቻል እስከ ቀን 11 ወይም 12 ሰዓት ቢሰራ✅ አንድ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠርና ማገልገል ይቻላል፤ሁለት እንስሳቶቹ ተገቢውን ህክምና ያገኛሉ፤ሶስት ሞያችን ይከበራል ያድጋልም። ---በተስፋሁን አበራ-- 4th year DVM
Hashtags
#HaSab #animalwelfare ወደ አህያ ቄራ ጉዳይ ደግሞ እንምጣ! ቻይና ኢጃ'ኦ(Ejiao) የሚባል ባህላዊ መድሀኒት አላት። መድሃኒቱ ለደማነስ፣ ራስ መታወክ፣ የእንቅልፍ እጦት እና የወር አበባ መዛባት ፍትሁን ነው ተብሎ በተጠቃሚዎቹ ይታሰባል። የሚቀመመውም የአህያ ቆዳ በእሳት ተፈትኖ በሚገኘው ጄላቲን ነው። ኢጃ'ኦን ለማምረት ቻይና በአመት የ4.8 million አህዮችን እርድ ትፈልጋለች። ይህ አለም ካላት 55.5 million የአህዮች ብዛት አንጻር እጅግ የተጋነነ እና ጣርያ የነካ የፍላጎት መጠን ከ1990-2018(እ.አ.አ) የቻይናን የአህያ ብዛት ከ11.1 million ወደ 2.5 million እንዲሽቆለቁል አድርጎታል። የሀገሪቱ የመካከለኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ ክፍል የዚህ መድሃኒት ሁነኛ ፈላጊ መሆንና የመካከለኛው ኢኮኖሚ በቻይና ጥሩ መሻሻል በማሳየቱ ቁጥሩን አግዝፎታል። በተጨማሪም ቻይና በምርቱ ላይ ያላትን የቀረጥ መጠን መቀነሷ እና የኢንፖርት መጠን እንዲያድግ ማድረጓ እንዲሁም የመድሃኒቱ ዝነኛ መሆን ለፍጆታው መጨመር እንደምክንያት ይጠቀሳል። እ.አ.አ በ2017 አንድ ኪሎ ለኢዳ'ኦ የሚውል የአህያ ቆዳ በ830 የአሜሪካ ዶላር ተሽጧል። ከዚህ ውስጥ 90% የተገኘው ከሌሎች እንደ አፍሪካ ያሉ የአለም ክፍሎች ኤክስፖርት ከተደረገ አቅርቦት ነው። The gardian በ2019 እንዳወጣው ዘገባ ከሆነ ይህ ፍላጎት በዚህ ከቀጠለ በኢጃ'ኦ ምክንያት የአለም የአህያ ብዛት በአምስት አመት ውስጥ በግማሽ ይቀንሳል። ቻይና አህዮቻቸውን ፍለጋ የዳበሰቻቸውን ሀገራት ዳታ ስንመለከት ደግሞ:- -ጋና እ.አ.አ በ2013 የአህያ ቄራ ከፍታ እጅግ አሳሳቢ በሆነ መልኩ የአህያ ቁጥር መመናመን፣ ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ በመስፋፋቱ በ2017 ዘግታለች። -በቦትስዋና የአህያ ቆዳ ኤክስፖርት መጀመሩን ተከትሎ 60% የአህያ ቁጥር ቀንሷል። -ታንዛኒያ ጫናውን ለመቋቋም ለ10 አመት የአህያ እርድን ከሀገሯ አግዳለች። -ናይጄርያ የኢጃ'ኦ ምርት በህጋዊም በህገወጥም መንገድ ጥሬ እቃ የሚያገኝባት ማዕከል ሆናለች -ጎረቤት ሀገር ኬንያ ደግሞ ከቻይና ጋር ይህንን ንግድ ለማሳለጥ የሁለትዮሽ ስምምነት አላት። እነዚህ ሀገራት ቀጣይ እጣ ፋንታዎቻቸው ምን የሚሆን ይመስላችኋል? ይህ ንግድ ጉዳቱ ወይንስ ጠቀሜታው ይጎላል? የሀገራችንን ጉዳይ ደግሞ በመጨረሻ ጽሑፌ እንመለከታለን። ያሬድ ኤርሚያስ 3rd year DVM student, AAU-OHC Founder and secretary, Membership director of Rotaract club of Kuriftu.
Hashtags
#HaSab #Animalwelfare 1.4 Billion ዶላር አመታዊ ፋይዳ! ባለፈው "ከቻይና እንበልጣለን" በሚል ርዕስ አንድ ጽሑፍ አጋርቼ ነበር። ጽሑፉ በሀገራችን ያለውን የአህያ መረጃ እንዲሁም የDonkey sanctuary አመሠራረት ለመዳሰስ ሞክርያለሁ። በዛሬው ጽሑፍ ደግሞ የአህያ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እና በአሰላ ከተማ የተገነባው የአህያ ቄራን ሁኔታ ለመመልከት እንሞክር። በሀገራችን አብዛኛው የእርሻ ቦታ እና የመኖርያ መንደር እጅግ የተራራቀ ነው። ገበሬው በለሊት ተነስቶ በሬውን፣ ሞፈር እና ቀንበሩን ይዞ ሌሎች በእርሻው ወቅት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በአህያው ጀርባ አኑሮ ወደ እርሻው ይሄዳል። ቡቃያው አፍርቱ እህሉ እስኪደርስ ድረስ ለሚያከናውናቸው ተግባራት የሚጠቀማቸውን መሠርያዎች የምትሸከምለት አህያው ነች። በተጨማሪም አዝመራ በደረሰ ጊዜ አህያ የእውቅያ ስርዓቱ ላይ ትልቅ ሚና አላት።(የህዳር አህያን ታውቃላችሁ? ህዳር አዝመራ የሚደርስበት ወቅት እንደመሆኑ የህዳር አህያ ለመንደሩ ሰው ሁሉ ግልጋሎት ትሰጣለች። አህያዬን ለምን ወሰድክ የለም!) ስለዚህ አንዲት አህያ ከእርሻ እስከ ጎተራ መሙላት ድረስ ፋይዳዋ ብዙ ነው። የሀገሬ ገበሬ "አህያዬ ባትኖር እኔ ና ሚስቴ አህዮች ነበርንን ይላል።" ሸክማችን ሸክሟ ሆኖ ነው እንደሰው ያለ ሸክም የምራመደው ማለቱ ነው። በተጨማሪም በሀገራችን ጉራማይሌ መልከዓ ምድር የቆላን ምርት ለደጋ የደጋውን ለቆላ ለማድረስ የአህያ ማጓጓዣ መጠቀም ግዴታ ነው። ገና መሠረተ ልማት በየደጃፋችን የደረሰልን ሀብታም ሀገር አይደለንም። እጅግ ብዙ ይቀረናል። የአቀበት ቁልቁለት ስቃይን ተቋቁሞ እንደ አህያ የተሸከመልን ቴክኖሎጂ የለም። መሠረተ ልማት ቢሟላልን እንኳ የነዳጅ ነገር እንኳን ለገጠሩ ለከተማውም ከአቅም በላይ ነው። እጅ ላይ ያለች ብቸኛ አማራጭ ነች አህያ። ቅዳሜ ገበያ ሄዶ ሊሸምት ያሰበ ከአህያ ጀርባ ላይ ሸክም ሲወርድ ሳያይ አይመለስም። ይህ ብቻ ሳይሆን በገጠር ከተማዎች የእለት ጉርሳቸው በአህያ ጋሪ ጭነት የሚጎርሱ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። የአንዲት አህያ በቤት ውስጥ መኖር ለሴቶች፣ለአቅመ ደካሞች እና ህፃናት ፍይዳው ብዙ ነው። አንድ በሬ ሊጠቀምበት የሚችለው የቤቱ አባወራ ብቻ ነው። ነገር ግን አንዲት አህያ ለአባወራው እህል በመውቃት፣ በመሸከም እና በማጓጓዝ ብታግዝ ለእማወራይቱ ደግሞ ወሃ ከሩቅ ቀድቶ በመምጣት፣ ለማገዶ እንጨት ለቅሞ ለማምጣት፣ በጓሮ ተክለው ያጸደቁት አትክልት ጀርበቸው ሳይጎብጥ የሚፈለገው ቦታ ወስዶ ለመሸጥ ግልጋሎት ይሰጣሉ። የግል ገቢም ይኖራቸዋል። እቤቱ አህያ ያለ ህፃናት "ወሃ ከምንጭ ሳትቀዳ ወደ ትምህርት ቤት አትሄድም!" አይባልም። ጉልበቱ በመጠኑም ቢሆን ከመበዝበዝ ያርፋል። ለማጥናት ጊዜ ይኖረዋል። ለአቅመ ደካሞችም የለት ገቢያቸው ጥቂት ለሆነ የአህያ ጭነት መተዳደርያ ነው። ስለዚህ አህያዎች እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት በተለይም ለገጠርራማይቱ ክፍል እጅግ ጠቃሚ ናቸው። ሰዎች እና ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ፣ ለእርሻ እና ውቅያ፣በተጨማሪም በተለያዩ የግንባታ ስራዎች ወቅት የግንባታ እቃዎች ለማጓጓዝ ያገለግላሉ። ከሌሎች የትራንስፖርት አማራጮች አንጻር(እንደ መኪና) ዋጋቸው ርካሽ መሆኑ በቀላል በታችኛው የኑሮ እርከን ያሉ ሰዎች እንዲያገኟቸው እና እንዲጠቀሙባቸው ያደርጋል። ይህ ችላ የሚባል ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አይደለም። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አህያ ለኢትዮጵያ GDP 1.4 Million የአሜሪካ ዶላር አመታዊ ፋይዳ አላት። አሁን ባለው የእንስሳት ደህንነት ደረጃ እና የግብርና አቅም ይህን ያህል ከፈየደ ይበልጥ ብናድግ እና ብንሻሻል ፋይዳው ምን ይህል ይሆን? እንቀጥላለን ያሬድ ኤርሚያስ 3rd year DVM student, AAU-OHC Founder and secretary, Membership director of Rotaract club of Kuriftu.
Hashtags
#HaSab #Animalwelfare ከቻይና እንበልጣለን! በኢትዮጵያ በተለይም በገጠራማው አከባቢ ከሦስት አባወራዎች አንዱ አህያ እንዳለው ይታመናል። የሀገራችን የአህያ ዝርያ በአራት የሚከፈል ሲሆን እኚህ ዝርያዎች ጅማ፣ አቢሲኒያ፣ ኦጋዴን እና ሰናር የሚባሉ ሲሆን፤ በሀገሪቱ በቆላ፣ደጋ እንዲሁም በተለያዩ የምድሪቱ የተፈጥሮ ሁኔታዎች ጋር ስሙሙ ሆነው ይኖራሉ።እ.ኢ.አ በ2013 በFAO በተሰራ ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ የ7 million አህዮች መገኛ ናት። የቅርብ መረጃዎች ደግሞ ቁጥራቸው እስከ 8.5 million ሊደርስ እንደሚችል ይናገራሉ። ይህ ቁጥር ቻይናን በማስከተል በአለም ትልቅ ቁጥር ያላት ሀገር ያደርጋታል።(ከቻይና የምንበልጠው እንግዲህ በቁጥር ነው!) አህያ የፈረስ ቤተሰብ የሆነው Family Equidae አባል ነች። አመቱን ሙሉ መራባት ትችላለች። በእንክብካቤ እና በደህንነት መያዝ ከተቻለ እስከ 30 አመት ትኖራለች።(በኢትዮጵያ በአማካይ ከ4-6 ዓመት ብቻ ነው የምትኖረው)። ደረሰች የምትባልበት እድሜ ከ2-3 ዓመት ሲሆን በዚህ ግዜ ጥሩ የሚባለው የሰውነት ክብደት 105kg ነው።እህች ጠንካራ እና ብርቱ ፍጥረት ጥሩ የማስታወስ ችሎታ አላት።የተጓዘችበትን መንገድ በፍጹም አትረሳም።(የሀገር ሰው ሲተርት "የምትሄድበት መንገድ ቢጠፋህ አህያህን ተከተል።" ይላል።) የሸሆና ጥፍራቸው ጠንካራ መሆን እና አስቸጋሪ መንገዶችን ተጋፍጠው መጓዝ መቻላቸው ከሌሎች የፈረስ ቤተሰቦች ይልቅ ለሸክም እና ለማጓጓዣነት ተመራጭ አድርጓቸዋል በኢትዮጵያ አንዲት አህያ ከ6-100kg(አንዳንዴም ከዛ በላይ) ተሸክማ ከ15-20 km ያክል ርቀት ከ5-6 ሰዓታት ያለ እረፍት ልትጓዝ ትችላለች። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የምድር ወገብ ሀሩር አውራጃዎች(Tropical region) አህዮች በብዛት በመንጋጋ ቆልፍ (tetanus)፣ ተዋስያን(internal and external parasites)፣ ወበቅ(intense heat)፣ በተለያዩ የመቁሰል አደጋዎች( Traumatic injury)፣ ተገቢ የሆነ አመጋገብ እጥረት እና የሸሆና ጥፍራቸው ከመጠን ያለፈ በማደጉ ለሚመጡ ችግሮች ተጋላጭ ናቸው። በተለይም በሸክም መብዛት እና ከመጠን ያለፈ ድብደባ የሚቆስሉ እና የሚሰቃዩ አህዮች ቁጥር ቀላል አይደለም። Donkey sanctuary በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የእንስሳት ህክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል። Donkey sanctuary እ.አ.አ በ1969 ኤልሳቤት ሳፈንድሰን በተባለች የእንስሳት ደህንነት አቀንቃኝ በእንግሊዟ ዴቮን ተመሥርቷል።ሲቋቋም ዋና አላማው ለአህዮች ደህንነት ምቹ የሆነ ከባቢን መፍጠር የነበረ ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅተ በአውሮፓ፣አፍሪካ እና አሜሪካ ውስጥ በአህዮች ደህንነት ጥበቃ፣ በእንስሳት ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጥ እንዲሁም የተለያዩ ባለሞያዎችን ማስተማርና ማሰልጠን ላይ አበክሮ ይሰራል። ቅርንጫፉም በ40 ሀገራት ውስጥ ይገኛል። Donkey sanctuary በኢትዮጵያ እ.ኢ.አ በ1986 ዓ.ም በፕሮፌሰር ፍሰሃ ገ/አብ አማካኝነት ተመስርቶ እየሰራ ይገኛል።
Hashtags
#HaSab #Animalwelfare The way to independence እ.አ.አ በ1908 ናሽቪል በምትባል የአሜሪካ ከተማ ውስጥ ሞሪስ ፍራንክ(Morris Frank) የሚባል ሰው ተወለደ። ይህ ሰው ልጅነቱን ያሳለፈው ማየት የተሳናት እናቱን በመርዳት እና በምትጓዝበት መንገድ ሁሉ አይኗ በመሆን ነው። ነገር ግን በስድስት አመቱ በፈረስ ጀርባ ላይ ሆኖ ሽምጥ ሲጋልብ የቀኝ አይኑን የዛፍ ቅርንጫፍ ጠነቆለው። አንድ አይኑን አጣ። በአስራ ስድት አመቱ ደግሞ ሌላኛው አይኑ በቡጢ ፈሰሰ። ፍራንክ ማየት የተሳነው ሆነ። ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገባ ሊለምድ ያልቻለው እና ሁሌ ይማረርበት የነበረው ማየት የተሳነው በመሆኑ ሁሌም የሰዎችን እርዳታ መፈለጉ ነበር። ብቻውን ያሻው ቦታ ብድግ ብሎ ባለመሄዱ እጅግ ያዝን ነበር። ይባስ ብሎ የእድሜ እኩዮቹ የሚፈልገውን ቦታ እንዲወስዱት በጠየቀ ጊዜ ታማኝ ተባባሪ ሊሆኑ አልቻሉም።ህይወት እጅግ ከብዳው ነበር።አንድ ዜና ሲነበብ እስኪሰማ ድረስ። በህዳር 1927(እ.አ.አ) የፍራንክ አባት የቅዳሜ ምሽት ዜናን ሲያነብለት የሰማው ነገር ግን ህይወቱን እስከወዲያኛው ቀየረ። በርግጥ ያ ዜና የፍራንክን ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ ያሉ እጅግ በርካታ ማየት የተሳናቸው ሰዎች ህይወትም የለወጠ እጅግ አስደሳች ዜና ነበር። ነገሩ እንዲህ ነው። በአሜሪካዊቷ የውሾች አሰልጣኝ ድሮቲ ሒርሰን አውስተስ(Dorothy Harrison Eustis) ጀርመን ውስጥ የተከፈተ ትምህርት ቤት በመጀመርያው የአለም ጦርነት አይናቸውን ያጡ የዘመቻ ተመላሾች ከአጋዥ ውሾች ጋር ሆነው መሥራት እንዲችሉ የሚያደርግ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የሚያበስር ዜና ነበር። ፍራንክ ይሄን ሲሰማ ጊዜ ሳያጠፋ ለአውስተስ ጻፈላት። ህይወቱ ውስጥ ታማኝ የሆነው እና ወዲህ እንሂድ ወዲያ ቢል የማይሰለቸው አጋዥ ጋር መሠልጠን እንደሚፈልግ ነገራት። እሷም ሲውዘርላድ ወደሚገኘው ትምህርት ቤት እንዲሄድ የእድል በር ከፈተችለት። ሲውዘርላንድ እንደደረሰ 'kiss' የምትባል ውሻ ተሰጠችው። ይህችን እስከ ህይወቱ ፍጻሜ ባጣቸው አይኖች ፈንታ አይን ሆነ የኖረችን ታማኝ ፍጥረት ፍራንክ 'buddy' ብሎ ሰየማት። ፍራንክ እና ባዲ አብረው 50,000 ማይሎችን ተጉዘዋል። ይህም ውሾች ማየት የተሳናቸውን ሰዎች እንዴት ሊያገዙ እና በህይወታቸው ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ለአለም አስመስክሯል። ባዲ እጅግ አስደናቂ በሆነ መልኩ የፍራንክን የየእለት ጉዞ አይን ሆና ከመምራት አልፋ እ.አ.አ በ1938 ለመጀመርያ ጊዜ ከቺካጎ ወደ ኒዎዮርክ ለሚደረገው በረራ ሙሉ አጃቢው ሆና በነጻነት የማንንም እርዳታ ሳይጠይቅ እንዲጓዝ አድርጋዋለች። ይህ ስራዋ አለም የውሾች ለማየት የተሳናቸው ሁነኛ አጋዥ መሆንን ሙሉ በሙሉ እንዲስማማ እና እንዲደግፍ ያደረገ ሆኗል። በባዲ ይህወቱ የቀለለት ፍራንክ ታድያ እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም። እ.አ.አ በ1929 ከአውስተስ ጋር በመሆን በአሜሪካ የመጀመርያውን የማየት የተሳናቸው አጋዥ ውሾች ማሰልጠኛ (The seeing eye) ከፍቷል።ምክትል ፕሬዝደንት በመሆንም አገልግሏል። በተጨማሪም በተገኘባቸው ስፍራዎች ሁሉ ስለ ውሾች እና ማየት የተሳናቸው ሰዎች ቁርኝት 'The divine gift of freedom' እያለ ለማስተማር ጥሯል። ዛሬ ላይ እንደ International Association of Assistance Dog Partners(IAADP) ዌብሳይት ገለጻ ከሆነ በአሜሪካ 100,000 ገደማ Assistant dogኦች ለተለያዩ አካልጉዳተኛች አጋዥ ጓደኛ ናቸው። ማየት ለተሳነው አይን፣መስማት ለተሳነው ጆሮ፣መንቀሳቀስ ለከበደው ተላላኪ እንዲሁም የአእምሮ ህመም ላጋጠመው እንደ ቴራፒ ሆነው ያገለግላሉ። በሀገራችን ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ደግሞ ከ5000 ያላነሱ ውሾች ይገኛሉ። ገና ሰዎች ሲያዩዋቸው አርፈው በተኙበት ድንጋይ ይወረውሩባቸዋል። በሽታ ያስተላልፉብናል በሚል ሰበብ ሰቅለው ገድረው የሙት በድን አፋቸው ድንገይ አነጣጥሮ መጨመር ይጫወቱባቸዋል።በሀገራችን የእንስሳትን ደህንነት መጠበቅ እጅግ ቅንጦት ነው።በጥቂት ግለሰቦች ደረጃ ካልሆነ በቀር እንደ ሀገር ለእንስሳት ደህንነት ብዙ አላሰብንም፣አልተጨነቅንም። ከሌላው አለም ተምረን ተንከባክበናው ይበልጥ እንዲጠቅሙን ለማድረግ ለምን ተሳነን ይሆን? ፍራንክ እና ባዲ በ Morristown Green, New Jersey በቁመናቸው ልክ የሚሆን(life sized) የነሃስ ሐውልት እ.አ.አ በ2005 ሁሌ በሚመላለሱበት መንገድ አቅራብያ ተሰርቶላቸዋል። (ምስሉ ኮመንት ውስጥ አለ) እንዲህ ያለ ታሪክ ስሰማ ለሀገሬ እቀናለሁ! ያሬድ ኤርሚያስ 3rd year DVM student, AAU-OHC Founder and secretary, Membership director of Rotaract club of Kuriftu.
Hashtags