የልጥፍ ይዘት
#HaSab #Animalwelfare The way to independence እ.አ.አ በ1908 ናሽቪል በምትባል የአሜሪካ ከተማ ውስጥ ሞሪስ ፍራንክ(Morris Frank) የሚባል ሰው ተወለደ። ይህ ሰው ልጅነቱን ያሳለፈው ማየት የተሳናት እናቱን በመርዳት እና በምትጓዝበት መንገድ ሁሉ አይኗ በመሆን ነው። ነገር ግን በስድስት አመቱ በፈረስ ጀርባ ላይ ሆኖ ሽምጥ ሲጋልብ የቀኝ አይኑን የዛፍ ቅርንጫፍ ጠነቆለው። አንድ አይኑን አጣ። በአስራ ስድት አመቱ ደግሞ ሌላኛው አይኑ በቡጢ ፈሰሰ። ፍራንክ ማየት የተሳነው ሆነ። ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገባ ሊለምድ ያልቻለው እና ሁሌ ይማረርበት የነበረው ማየት የተሳነው በመሆኑ ሁሌም የሰዎችን እርዳታ መፈለጉ ነበር። ብቻውን ያሻው ቦታ ብድግ ብሎ ባለመሄዱ እጅግ ያዝን ነበር። ይባስ ብሎ የእድሜ እኩዮቹ የሚፈልገውን ቦታ እንዲወስዱት በጠየቀ ጊዜ ታማኝ ተባባሪ ሊሆኑ አልቻሉም።ህይወት እጅግ ከብዳው ነበር።አንድ ዜና ሲነበብ እስኪሰማ ድረስ። በህዳር 1927(እ.አ.አ) የፍራንክ አባት የቅዳሜ ምሽት ዜናን ሲያነብለት የሰማው ነገር ግን ህይወቱን እስከወዲያኛው ቀየረ። በርግጥ ያ ዜና የፍራንክን ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ ያሉ እጅግ በርካታ ማየት የተሳናቸው ሰዎች ህይወትም የለወጠ እጅግ አስደሳች ዜና ነበር። ነገሩ እንዲህ ነው። በአሜሪካዊቷ የውሾች አሰልጣኝ ድሮቲ ሒርሰን አውስተስ(Dorothy Harrison Eustis) ጀርመን ውስጥ የተከፈተ ትምህርት ቤት በመጀመርያው የአለም ጦርነት አይናቸውን ያጡ የዘመቻ ተመላሾች ከአጋዥ ውሾች ጋር ሆነው መሥራት እንዲችሉ የሚያደርግ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የሚያበስር ዜና ነበር። ፍራንክ ይሄን ሲሰማ ጊዜ ሳያጠፋ ለአውስተስ ጻፈላት። ህይወቱ ውስጥ ታማኝ የሆነው እና ወዲህ እንሂድ ወዲያ ቢል የማይሰለቸው አጋዥ ጋር መሠልጠን እንደሚፈልግ ነገራት። እሷም ሲውዘርላድ ወደሚገኘው ትምህርት ቤት እንዲሄድ የእድል በር ከፈተችለት። ሲውዘርላንድ እንደደረሰ 'kiss' የምትባል ውሻ ተሰጠችው። ይህችን እስከ ህይወቱ ፍጻሜ ባጣቸው አይኖች ፈንታ አይን ሆነ የኖረችን ታማኝ ፍጥረት ፍራንክ 'buddy' ብሎ ሰየማት። ፍራንክ እና ባዲ አብረው 50,000 ማይሎችን ተጉዘዋል። ይህም ውሾች ማየት የተሳናቸውን ሰዎች እንዴት ሊያገዙ እና በህይወታቸው ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ለአለም አስመስክሯል። ባዲ እጅግ አስደናቂ በሆነ መልኩ የፍራንክን የየእለት ጉዞ አይን ሆና ከመምራት አልፋ እ.አ.አ በ1938 ለመጀመርያ ጊዜ ከቺካጎ ወደ ኒዎዮርክ ለሚደረገው በረራ ሙሉ አጃቢው ሆና በነጻነት የማንንም እርዳታ ሳይጠይቅ እንዲጓዝ አድርጋዋለች። ይህ ስራዋ አለም የውሾች ለማየት የተሳናቸው ሁነኛ አጋዥ መሆንን ሙሉ በሙሉ እንዲስማማ እና እንዲደግፍ ያደረገ ሆኗል። በባዲ ይህወቱ የቀለለት ፍራንክ ታድያ እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም። እ.አ.አ በ1929 ከአውስተስ ጋር በመሆን በአሜሪካ የመጀመርያውን የማየት የተሳናቸው አጋዥ ውሾች ማሰልጠኛ (The seeing eye) ከፍቷል።ምክትል ፕሬዝደንት በመሆንም አገልግሏል። በተጨማሪም በተገኘባቸው ስፍራዎች ሁሉ ስለ ውሾች እና ማየት የተሳናቸው ሰዎች ቁርኝት 'The divine gift of freedom' እያለ ለማስተማር ጥሯል። ዛሬ ላይ እንደ International Association of Assistance Dog Partners(IAADP) ዌብሳይት ገለጻ ከሆነ በአሜሪካ 100,000 ገደማ Assistant dogኦች ለተለያዩ አካልጉዳተኛች አጋዥ ጓደኛ ናቸው። ማየት ለተሳነው አይን፣መስማት ለተሳነው ጆሮ፣መንቀሳቀስ ለከበደው ተላላኪ እንዲሁም የአእምሮ ህመም ላጋጠመው እንደ ቴራፒ ሆነው ያገለግላሉ። በሀገራችን ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ደግሞ ከ5000 ያላነሱ ውሾች ይገኛሉ። ገና ሰዎች ሲያዩዋቸው አርፈው በተኙበት ድንጋይ ይወረውሩባቸዋል። በሽታ ያስተላልፉብናል በሚል ሰበብ ሰቅለው ገድረው የሙት በድን አፋቸው ድንገይ አነጣጥሮ መጨመር ይጫወቱባቸዋል።በሀገራችን የእንስሳትን ደህንነት መጠበቅ እጅግ ቅንጦት ነው።በጥቂት ግለሰቦች ደረጃ ካልሆነ በቀር እንደ ሀገር ለእንስሳት ደህንነት ብዙ አላሰብንም፣አልተጨነቅንም። ከሌላው አለም ተምረን ተንከባክበናው ይበልጥ እንዲጠቅሙን ለማድረግ ለምን ተሳነን ይሆን? ፍራንክ እና ባዲ በ Morristown Green, New Jersey በቁመናቸው ልክ የሚሆን(life sized) የነሃስ ሐውልት እ.አ.አ በ2005 ሁሌ በሚመላለሱበት መንገድ አቅራብያ ተሰርቶላቸዋል። (ምስሉ ኮመንት ውስጥ አለ) እንዲህ ያለ ታሪክ ስሰማ ለሀገሬ እቀናለሁ! ያሬድ ኤርሚያስ 3rd year DVM student, AAU-OHC Founder and secretary, Membership director of Rotaract club of Kuriftu.