የልጥፍ ይዘት
#HaSab #Animalwelfare ከቻይና እንበልጣለን! በኢትዮጵያ በተለይም በገጠራማው አከባቢ ከሦስት አባወራዎች አንዱ አህያ እንዳለው ይታመናል። የሀገራችን የአህያ ዝርያ በአራት የሚከፈል ሲሆን እኚህ ዝርያዎች ጅማ፣ አቢሲኒያ፣ ኦጋዴን እና ሰናር የሚባሉ ሲሆን፤ በሀገሪቱ በቆላ፣ደጋ እንዲሁም በተለያዩ የምድሪቱ የተፈጥሮ ሁኔታዎች ጋር ስሙሙ ሆነው ይኖራሉ።እ.ኢ.አ በ2013 በFAO በተሰራ ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ የ7 million አህዮች መገኛ ናት። የቅርብ መረጃዎች ደግሞ ቁጥራቸው እስከ 8.5 million ሊደርስ እንደሚችል ይናገራሉ። ይህ ቁጥር ቻይናን በማስከተል በአለም ትልቅ ቁጥር ያላት ሀገር ያደርጋታል።(ከቻይና የምንበልጠው እንግዲህ በቁጥር ነው!) አህያ የፈረስ ቤተሰብ የሆነው Family Equidae አባል ነች። አመቱን ሙሉ መራባት ትችላለች። በእንክብካቤ እና በደህንነት መያዝ ከተቻለ እስከ 30 አመት ትኖራለች።(በኢትዮጵያ በአማካይ ከ4-6 ዓመት ብቻ ነው የምትኖረው)። ደረሰች የምትባልበት እድሜ ከ2-3 ዓመት ሲሆን በዚህ ግዜ ጥሩ የሚባለው የሰውነት ክብደት 105kg ነው።እህች ጠንካራ እና ብርቱ ፍጥረት ጥሩ የማስታወስ ችሎታ አላት።የተጓዘችበትን መንገድ በፍጹም አትረሳም።(የሀገር ሰው ሲተርት "የምትሄድበት መንገድ ቢጠፋህ አህያህን ተከተል።" ይላል።) የሸሆና ጥፍራቸው ጠንካራ መሆን እና አስቸጋሪ መንገዶችን ተጋፍጠው መጓዝ መቻላቸው ከሌሎች የፈረስ ቤተሰቦች ይልቅ ለሸክም እና ለማጓጓዣነት ተመራጭ አድርጓቸዋል በኢትዮጵያ አንዲት አህያ ከ6-100kg(አንዳንዴም ከዛ በላይ) ተሸክማ ከ15-20 km ያክል ርቀት ከ5-6 ሰዓታት ያለ እረፍት ልትጓዝ ትችላለች። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የምድር ወገብ ሀሩር አውራጃዎች(Tropical region) አህዮች በብዛት በመንጋጋ ቆልፍ (tetanus)፣ ተዋስያን(internal and external parasites)፣ ወበቅ(intense heat)፣ በተለያዩ የመቁሰል አደጋዎች( Traumatic injury)፣ ተገቢ የሆነ አመጋገብ እጥረት እና የሸሆና ጥፍራቸው ከመጠን ያለፈ በማደጉ ለሚመጡ ችግሮች ተጋላጭ ናቸው። በተለይም በሸክም መብዛት እና ከመጠን ያለፈ ድብደባ የሚቆስሉ እና የሚሰቃዩ አህዮች ቁጥር ቀላል አይደለም። Donkey sanctuary በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የእንስሳት ህክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል። Donkey sanctuary እ.አ.አ በ1969 ኤልሳቤት ሳፈንድሰን በተባለች የእንስሳት ደህንነት አቀንቃኝ በእንግሊዟ ዴቮን ተመሥርቷል።ሲቋቋም ዋና አላማው ለአህዮች ደህንነት ምቹ የሆነ ከባቢን መፍጠር የነበረ ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅተ በአውሮፓ፣አፍሪካ እና አሜሪካ ውስጥ በአህዮች ደህንነት ጥበቃ፣ በእንስሳት ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጥ እንዲሁም የተለያዩ ባለሞያዎችን ማስተማርና ማሰልጠን ላይ አበክሮ ይሰራል። ቅርንጫፉም በ40 ሀገራት ውስጥ ይገኛል። Donkey sanctuary በኢትዮጵያ እ.ኢ.አ በ1986 ዓ.ም በፕሮፌሰር ፍሰሃ ገ/አብ አማካኝነት ተመስርቶ እየሰራ ይገኛል።