TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #19

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች76የዕይታ ቁጥር
ታትሟልሴፕቴ 1010/09/2023 08:51 ከሰዓት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

#HaSab #Animalwelfare 1.4 Billion ዶላር አመታዊ ፋይዳ! ባለፈው "ከቻይና እንበልጣለን" በሚል ርዕስ አንድ ጽሑፍ አጋርቼ ነበር። ጽሑፉ በሀገራችን ያለውን የአህያ መረጃ እንዲሁም የDonkey sanctuary አመሠራረት ለመዳሰስ ሞክርያለሁ። በዛሬው ጽሑፍ ደግሞ የአህያ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እና በአሰላ ከተማ የተገነባው የአህያ ቄራን ሁኔታ ለመመልከት እንሞክር። በሀገራችን አብዛኛው የእርሻ ቦታ እና የመኖርያ መንደር እጅግ የተራራቀ ነው። ገበሬው በለሊት ተነስቶ በሬውን፣ ሞፈር እና ቀንበሩን ይዞ ሌሎች በእርሻው ወቅት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በአህያው ጀርባ አኑሮ ወደ እርሻው ይሄዳል። ቡቃያው አፍርቱ እህሉ እስኪደርስ ድረስ ለሚያከናውናቸው ተግባራት የሚጠቀማቸውን መሠርያዎች የምትሸከምለት አህያው ነች። በተጨማሪም አዝመራ በደረሰ ጊዜ አህያ የእውቅያ ስርዓቱ ላይ ትልቅ ሚና አላት።(የህዳር አህያን ታውቃላችሁ? ህዳር አዝመራ የሚደርስበት ወቅት እንደመሆኑ የህዳር አህያ ለመንደሩ ሰው ሁሉ ግልጋሎት ትሰጣለች። አህያዬን ለምን ወሰድክ የለም!) ስለዚህ አንዲት አህያ ከእርሻ እስከ ጎተራ መሙላት ድረስ ፋይዳዋ ብዙ ነው። የሀገሬ ገበሬ "አህያዬ ባትኖር እኔ ና ሚስቴ አህዮች ነበርንን ይላል።" ሸክማችን ሸክሟ ሆኖ ነው እንደሰው ያለ ሸክም የምራመደው ማለቱ ነው። በተጨማሪም በሀገራችን ጉራማይሌ መልከዓ ምድር የቆላን ምርት ለደጋ የደጋውን ለቆላ ለማድረስ የአህያ ማጓጓዣ መጠቀም ግዴታ ነው። ገና መሠረተ ልማት በየደጃፋችን የደረሰልን ሀብታም ሀገር አይደለንም። እጅግ ብዙ ይቀረናል። የአቀበት ቁልቁለት ስቃይን ተቋቁሞ እንደ አህያ የተሸከመልን ቴክኖሎጂ የለም። መሠረተ ልማት ቢሟላልን እንኳ የነዳጅ ነገር እንኳን ለገጠሩ ለከተማውም ከአቅም በላይ ነው። እጅ ላይ ያለች ብቸኛ አማራጭ ነች አህያ። ቅዳሜ ገበያ ሄዶ ሊሸምት ያሰበ ከአህያ ጀርባ ላይ ሸክም ሲወርድ ሳያይ አይመለስም። ይህ ብቻ ሳይሆን በገጠር ከተማዎች የእለት ጉርሳቸው በአህያ ጋሪ ጭነት የሚጎርሱ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። የአንዲት አህያ በቤት ውስጥ መኖር ለሴቶች፣ለአቅመ ደካሞች እና ህፃናት ፍይዳው ብዙ ነው። አንድ በሬ ሊጠቀምበት የሚችለው የቤቱ አባወራ ብቻ ነው። ነገር ግን አንዲት አህያ ለአባወራው እህል በመውቃት፣ በመሸከም እና በማጓጓዝ ብታግዝ ለእማወራይቱ ደግሞ ወሃ ከሩቅ ቀድቶ በመምጣት፣ ለማገዶ እንጨት ለቅሞ ለማምጣት፣ በጓሮ ተክለው ያጸደቁት አትክልት ጀርበቸው ሳይጎብጥ የሚፈለገው ቦታ ወስዶ ለመሸጥ ግልጋሎት ይሰጣሉ። የግል ገቢም ይኖራቸዋል። እቤቱ አህያ ያለ ህፃናት "ወሃ ከምንጭ ሳትቀዳ ወደ ትምህርት ቤት አትሄድም!" አይባልም። ጉልበቱ በመጠኑም ቢሆን ከመበዝበዝ ያርፋል። ለማጥናት ጊዜ ይኖረዋል። ለአቅመ ደካሞችም የለት ገቢያቸው ጥቂት ለሆነ የአህያ ጭነት መተዳደርያ ነው። ስለዚህ አህያዎች እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት በተለይም ለገጠርራማይቱ ክፍል እጅግ ጠቃሚ ናቸው። ሰዎች እና ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ፣ ለእርሻ እና ውቅያ፣በተጨማሪም በተለያዩ የግንባታ ስራዎች ወቅት የግንባታ እቃዎች ለማጓጓዝ ያገለግላሉ። ከሌሎች የትራንስፖርት አማራጮች አንጻር(እንደ መኪና) ዋጋቸው ርካሽ መሆኑ በቀላል በታችኛው የኑሮ እርከን ያሉ ሰዎች እንዲያገኟቸው እና እንዲጠቀሙባቸው ያደርጋል። ይህ ችላ የሚባል ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አይደለም። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አህያ ለኢትዮጵያ GDP 1.4 Million የአሜሪካ ዶላር አመታዊ ፋይዳ አላት። አሁን ባለው የእንስሳት ደህንነት ደረጃ እና የግብርና አቅም ይህን ያህል ከፈየደ ይበልጥ ብናድግ እና ብንሻሻል ፋይዳው ምን ይህል ይሆን? እንቀጥላለን ያሬድ ኤርሚያስ 3rd year DVM student, AAU-OHC Founder and secretary, Membership director of Rotaract club of Kuriftu.