የልጥፍ ይዘት
#HaSab #animalwelfare ወደ አህያ ቄራ ጉዳይ ደግሞ እንምጣ! ቻይና ኢጃ'ኦ(Ejiao) የሚባል ባህላዊ መድሀኒት አላት። መድሃኒቱ ለደማነስ፣ ራስ መታወክ፣ የእንቅልፍ እጦት እና የወር አበባ መዛባት ፍትሁን ነው ተብሎ በተጠቃሚዎቹ ይታሰባል። የሚቀመመውም የአህያ ቆዳ በእሳት ተፈትኖ በሚገኘው ጄላቲን ነው። ኢጃ'ኦን ለማምረት ቻይና በአመት የ4.8 million አህዮችን እርድ ትፈልጋለች። ይህ አለም ካላት 55.5 million የአህዮች ብዛት አንጻር እጅግ የተጋነነ እና ጣርያ የነካ የፍላጎት መጠን ከ1990-2018(እ.አ.አ) የቻይናን የአህያ ብዛት ከ11.1 million ወደ 2.5 million እንዲሽቆለቁል አድርጎታል። የሀገሪቱ የመካከለኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ ክፍል የዚህ መድሃኒት ሁነኛ ፈላጊ መሆንና የመካከለኛው ኢኮኖሚ በቻይና ጥሩ መሻሻል በማሳየቱ ቁጥሩን አግዝፎታል። በተጨማሪም ቻይና በምርቱ ላይ ያላትን የቀረጥ መጠን መቀነሷ እና የኢንፖርት መጠን እንዲያድግ ማድረጓ እንዲሁም የመድሃኒቱ ዝነኛ መሆን ለፍጆታው መጨመር እንደምክንያት ይጠቀሳል። እ.አ.አ በ2017 አንድ ኪሎ ለኢዳ'ኦ የሚውል የአህያ ቆዳ በ830 የአሜሪካ ዶላር ተሽጧል። ከዚህ ውስጥ 90% የተገኘው ከሌሎች እንደ አፍሪካ ያሉ የአለም ክፍሎች ኤክስፖርት ከተደረገ አቅርቦት ነው። The gardian በ2019 እንዳወጣው ዘገባ ከሆነ ይህ ፍላጎት በዚህ ከቀጠለ በኢጃ'ኦ ምክንያት የአለም የአህያ ብዛት በአምስት አመት ውስጥ በግማሽ ይቀንሳል። ቻይና አህዮቻቸውን ፍለጋ የዳበሰቻቸውን ሀገራት ዳታ ስንመለከት ደግሞ:- -ጋና እ.አ.አ በ2013 የአህያ ቄራ ከፍታ እጅግ አሳሳቢ በሆነ መልኩ የአህያ ቁጥር መመናመን፣ ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ በመስፋፋቱ በ2017 ዘግታለች። -በቦትስዋና የአህያ ቆዳ ኤክስፖርት መጀመሩን ተከትሎ 60% የአህያ ቁጥር ቀንሷል። -ታንዛኒያ ጫናውን ለመቋቋም ለ10 አመት የአህያ እርድን ከሀገሯ አግዳለች። -ናይጄርያ የኢጃ'ኦ ምርት በህጋዊም በህገወጥም መንገድ ጥሬ እቃ የሚያገኝባት ማዕከል ሆናለች -ጎረቤት ሀገር ኬንያ ደግሞ ከቻይና ጋር ይህንን ንግድ ለማሳለጥ የሁለትዮሽ ስምምነት አላት። እነዚህ ሀገራት ቀጣይ እጣ ፋንታዎቻቸው ምን የሚሆን ይመስላችኋል? ይህ ንግድ ጉዳቱ ወይንስ ጠቀሜታው ይጎላል? የሀገራችንን ጉዳይ ደግሞ በመጨረሻ ጽሑፌ እንመለከታለን። ያሬድ ኤርሚያስ 3rd year DVM student, AAU-OHC Founder and secretary, Membership director of Rotaract club of Kuriftu.