TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #35

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች225የዕይታ ቁጥር
ታትሟልዲሴም 2424/12/2023 08:43 ጥዋት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

#Advocacy #HaSab ውረድ ወደ መሬት! አሁን አሁን አዲስ ነገር ሳነብ ወይንም ከመምህሬ ስሰማ አንድ ሀሳብ ደጋግሞ በምዕናቤ ይመላለሳል:-'Ah, what if I had learned this earlier?!'🤦‍♂️ ብዙዎቹ ከጤና ጋር የተያያዙ ጉዳዎች በሀገራችን ለመላምት የተጋለጡ ናቸው። ሁሉም የመሠለውን ይናገራል። በርግጥ ከመላምት የተሻገሩ ባህላዊ እውቀጦች እንዳሉ ባይካድም.... እናም በልጅነት አእምሮም ይሁን ሁነኛ መረጃ በማጣት የብርቱካን ፍሬ ውጦ ከመችመች በአናቴ የዛፍ ቅርንጫፍ ተንዠረገገ እንደሚል ብላቴና ሆኜ ያሳለፍኩባቸውን ጊዜያት ሳስብ ፈገግ እላለሁ። ከነበርኩበት ላይብረሪ አልያም ከመማርያ ክፍል ወጥቼ ለማህበረሰቤ በሚያውቀው ቋንቋ፣ በሚረዳበት አዎድ "ይሄ የሆነው ለዚህ ነው፣ ይህ ማለት ይህ ነው!" ማለት ያምረኛል። ብዙውን ጊዜ የምንነጋገረው እርስ በእርስ ነው። (እዚህ LinkedIn ላይ ራሱ ስንት blog አነበብኩ ስንት የታተሙ ጆርናሎች አስደነቁኝ) በሞያዊ ቋንቋችን ባለን የትምህርት ደረጃ ልክ እንወያያለን እንከራከራለን ከድምዳሜ እንደርሳለን። የሚዘጋጁ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችም የሚሞሉት በባለሞያው ነው። ይህ እርስ በእርስ እንድንግባባ ቢያደርገንም ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ገና ብዙ እንደሚቀረን ጠቋሚ ነው። ለዛ ይሆን የመፍትሄ ሀሳቦቻችን መሬት የማይወርዱት? ዋናው ችግር ያለው መሬት ላይ ነው። ለመሬት እጅግ ቅርብ የሆነው ደግሞ አራሹ ነው። ህመም የጅማሮ ምልክቱን የሚያሳየው ቤት ነው። ቤት ውስጥ ያለው ደግሞ ቤተሰብ ነው። ኤኮኖሚው ሲዘም የሚያርደው የቤቱን ምሰሶ ነው። ምሰሶውን ቀጥ አድርጎ ለማቆም መሰሶ ካለበት መሄድ ያሻል። ስለዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫዎቻችን እርስ በእርስ ካለን መድረኮች የሚሻገሩ እና ማህበረሰቡ በማረዳው ቋንቋና አውድ የተተረጎመው ሆነው የሚዘጋጁ ለማድረግ ብዙ መስራት ያለብን ይመስለኛል። ባለሁበት የእንስሳት ጤና ዘርፍ - ስለተለያዩ ምርታማነትን የሚቀንሱ የእንስሳት በሽታዎች ( animal production and health) - ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በተዋሲያን የሚመጡ በሽታዎች (Zoonosis) - ስለ ጸረ-ተዋሲያን መድሀኒቶች በጀርሞች መላመድ ( antimicrobial resistance ) - ስለ ምግብ ደህንነት (food safety) - ስለ እንስሳት ደህንነት እና ፋይዳው ( Animal welfare and its impact ) - የማህበረሰብ ፣ እንስሳት እና አከባቢ ጤና ግንኙነት ( one health ) ማህበረሰቡን ለማስተማር ግንዛቤ ለመስጠት እና ለውጥ ለማምጣት ጽኑ ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ በጋራ መስራት እንችላለን። ያወቅነውን የማሳወቅ ሐላፊነት አለብንና! Advocacy for the community should be a slogan like "መሬት ላራሹ!" Lets connect on LinkedIn መልካም የረፍት ቀን!