የልጥፍ ይዘት
#HaSab #Veteducation ለ12ተኞች አድርሱልኝ🙏 በቅድምያ ሀገራችን ያለችበት ነባራዊ ሁኔታ በትምህርታችሁ ላይ ያደረሰውን ጫና ተቋቅማችሁ የሚያስደንቅ ውጤት በጥረታችሁ ላመጣችሁ ተማሪዎች አድናቆት እና አክብሮቴ ይድረስ።(በናንተ የወደፊቷን ኢትዮጵያ መልካም እንድትሆን እመኛለሁ) በተለይ ባለፉት ሦስት እና አራት አመታት ውስጥ የ12ተኛ ክፍል ፈተና ማለፍ አይደለም መፈተን በራሱ ብዙ ችግሮች ያሉበት ነው።(እንክርዳድ የበዛበት እህል ሆኗል)። በርግጠኝነት ቀለሜ ሆነው ዝግጅት በማድረግ ላይ ሳሉ በተደረጉ ብርታትንና ሞራልን የሚያደክሙ ውሳኔዎች የተሰበሩ ውጤታቸው እንደምኞታቸው ያልሆነላቸው የነገ ሀገር ተስፋዎች ይኖራሉ(እናንት ጠንካሮች ሆይ ተነሱ አቧራችሁን አራግፋችሁ ለእንደገና ሩጫ ራሳችሁን ኣበርቱ) EUEE እንደ ድሮው ኣይደለም።ጭራሽ ምንም ዝግጅት ሳያደርጉ ትምህርት ሚንስቴር አይቶ አይኔን ግንባር ያድርገው አላየሁም እያለ እልል ብለው በተሰረቁ ፈተናዎች ያለፉ ተማሪዎች እንዳሉ ሀቅ ነው። ለእነዚህም ሆነ ለሌሎች ተማሪዎች ንቁ! ዩኒቨርስቲ በተለይ የመጀመርያ አመት የመጀመርያ ሴሚስተር የሚከተለው ነው የሚል እንዳለፈበት ተማሪ መጠነኛ ሀሳቤ ይድረስ.... ውጤታችሁን እንደመመልከታችሁ ከወዲሁ ለሚጠብቃችሁ ኮርስ በትበት ብትሉ አሪፍ ነው። የፍሬሽ ማን ኮርሶች ከጥቂቶቹ በቀር ከ11 እና 12ተኛ ክፍል ትምህርት ጋር ያው ናቸው።(ለfinal exterme series መጽሐፍትን ነው ያነበብነው)። ችግሩ ያካልቧችኋል። አርፍዳችሁ እንደመግባታችሁ የምትማሩት ለመጨረስ እንጂ ለመረዳትም አይመስልም...ቀድማችሁ ዝግጅት አድርጋችሁ ብትገቡ ግን ቀለል ይልላችኋል። ጫናውን አሁን ባላችሁ ትርፍ ግዜ ትቀንሱታላችሁ።(እንዲያ አድርገው የገቡ ተማሪዎች በብዙ ነበር ያተረፉት)። የትምህርት መርጃ መጽሐፍት እና ስለ ኮርሶች ያለውን ሁሉMuja MercuryyyATC tube ላይ አስቀምጦላችኋል(ይመችህ ኣባቴ) ሁሉም ነገር ግዚያችንን ይፈልጋል። ሁሉም ቢተገብርቱት ጥሩ ትሩፋት ኣለው። በተለይ አስታውሳለሁ ዩኒቨርሲቲ ስገባ ኣደርጋቸዋለሁ የምላቸው መልካም ነገሮች ሁሉ ግርርር ብለው መጥተውብኝ የቱን ላስቀድም የሚለው ነገር በጣም ግራ ኣጋብቶኝ ነበር። የፍሬሽ ማን ኮርስ ደግሞ ግዜ አይሰጥም። ቀጣይ የምትመርጡት ፊልድ አሁን ባመጣችሁት ውጤት እና በመጀመርያ ሴሚስተር ባመጣችሁት(ለአንዳንዱ ሙሉ የመጀመርያ አመት) ውጤት ላይ የተመሠረተ ነው። ታድያ ግዜያችሁን በይበልጥ የነገ ጉዟችሁን በሚወስነው ችከላ ላይ ማድረግ ሸግዬ ነው(ያራድዬ ልጅ የሚያደርገው እንደዛ ነው) ዩኒቨርሲቲ ከመግባታችሁ በፊት ስለ ግቢዎች ወይም ፊልድ ከመምረጣችሁ በፊት ስለ ፊልዶች የሚነዙ ቀልዶች እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎቹ ሰዎች እንደሚሉት አይደለም። በጭፍን የምትጠሏቸውን ግቢዎች እና ፊልዶች አጢኗቸው። ለተራ ቀልዶች እጅ አትስጡ። በተለይ እንደግል ያለኝ ምክር የፊልድ መረጣችሁ በፍላጎትና ችሎታችሁ ይሁን የሚል ነው(ሸግዬ ውጤት ካላችሁ የፈለጋችሁበት መግባት ኣያሳስብም) "ያበላል?" የሚለው ጥያቄ interest በሌላችሁ ፊልድ ላይ እንደመግብያ ሰበብ ባትጠቀሙ መልካም ነው። ምክንያቱም የሚያጠግብ እንጀራ ለመብላት መጀመርያ እንጀራ መውደድ ያሻል!! Lets talk vet!💙 Veterinary medicine በሀገራችን ባሉ በአስራ የሚቆጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል። እውነት ለመናገር DVM እንደደረሰኝ ባወኩ ግዜ እጅግ ትልቅ ሀዘን እና ተስፋ መቁረጥ ነበር የተሰማኝ። የደረሰኝን የሰሙ ሁሉ ፊታቸው ጨፍጋጋ ነበር(ከጥቂቶቹ በቀር)። ገብቼ ልየው ካልሆነ እቀይራለሁ በሚል መንፈስ ነበር የገባሁት። ነገር ግን ጥቂት እንደተማርኩ የገባኝ እጅግ ድንቅ ሳይንስ(የልብ የሚያደርስ) እና ሰፊ የስራ መስክ ያለው ሞያ መሆኑን ነው። ከምነግራችሁ በላይ አድማሰ ሰፊ ነው። እንደኔ ለህክምና ሞያ ጥልቅ ፍቅርና ጉጉት ያላችሁ ተማሪዎች ስለ እንስሳት ህክምናም ብታስቡና በቂ ጥናት ብታደርጉ ባይ ነኝ። ለሀገርም ለራስም የሚበጅ ነገር በዚህ አለ(እስቲ The Blue Vetን ሾፍ አድርጓት) በቀረውስ ያሰባችሁት የሚሰምርበት የትምህርት ዘመን ከፊታችሁ እንዲመጣ እመኛለሁ። ሀገራችን ሰላም ሁና ሁሉም ወጣት የሚመኘው እየተማረ እንዲኖር ምኞቴ ነው። መልካም እድል! ሻሎም! Yared Ermiyas Second year student, AAU-CVMA (DVM)