TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #40

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች291የዕይታ ቁጥር
ታትሟልዲሴም 3131/12/2023 06:04 ጥዋት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

#HaSab #collaboration Yo! How do you see your classmates, dorm mates, or the midfielder on the football field, the high-achieving student at the college? The active and interactive one? How do you see your surroundings? Let me tell you about a bunch of opportunities you shouldn't miss! If you're in an environment that has the chance to be exposed to diversity, this blog is for you! እንደ ግለሰብ የትምህርት ስርዓታችን የአንደኝነት አተያያችንን አዛብቷል ብዬ አምናለሁ። ከታች ጀምሮ ተሻግረን ከመጣናቸው ብዙ ደረጃዎች ስኬት በላይ በተቀደምነው አንድ ደረጃ ላይ ትኩረታችንን እንድናደርግ ሁነናል! ቀለሜዎች ከእናንተ መሃል ሁለተኛ ስለወጣ ያላዘነ ማነው? ከደረደራቸው ብዙ A+ በላይ የተፎካካሪው B ያላስደሰተው ማነው? በርግጥ አንዱ ሌላውን የመብለጥ ጉዳይ ተፈጥሯዊ መሆኑና ሁላችንም የአሸናፊነት ስሜት እና ወኔ ሌኖረን የተገባ ቢሆንም ለአንደኝነት ያለን ግምት እና የትምህርት ስርዓታችን ውስጥ ያለው የእሽቅቅድም ስሜት ግን አንድ ከአሸናፊነት ማማ ሁላችንንም የሚያወጣን መንገድ ወደጎን እንድንተው ያደረገ ይመስለኛል! መንገዱን ጠየከኝ? ቆይ እነግርሃለው ታገስ! እየተማርክ ያለኸው ዘርፍ እንደ ባህር ያለ ነው። ብትቀዳው ከያዝከው አቁማዳ በላይ የሆነ፣ ሞልቶ የሚፈስ። ስለዚህ ከምትማራቸው እልፍ ጉዳዮች በተወሰኑት ላይ ብቁ እና ከሁሉም የተሻልክ መሆንህ አይቀሬ ነው። የተወሰኑት ደግሞ ትኩረትህን ላይስቡት ይችላሉ። ወዳጅህስ? ክፍል ውስጥ ከጎንህ ያለው ተማሪ በየትኛው ሌክቸር ክላስ ይመሠጣል? ዶርም በሶ አብሮህ የሚበጠብጥ ጓደኛል የትኛውን ኮርስ ፈተና ቢኖር ባይኖር ሁሌም ያነባል? የተኛው ወዳጅህ ከየትኛው የ Clinical case ፊት አታጣውም? ይህንን የምጠይቅህ አውቀህ እንድታደንቀው ብቻ አይደለም! ማድነቅ እማ አለብህ! ነገር ግን ልነግርህ ያሰብኩት ከዛ ይልቃል። Actually its a good opportunity you shouldn't miss! potential collaborator! አዎን የዛሬው ዶርም ሜትህ የነገ ትልቅ ቢዝነስ ካምፓኒ ፓርትነርህ ሊሆን ይችላል። ዥረት የሚፈጥሩት የመርፌ ክር ታህል ቅጥነት ያላቸው የወሃ መስመሮች ተዋህደው ነው። በጋራ ጥሩ የሆናችሁበትን ነገር በማዋሃድ አልያም አንዳችሁ ጎበዝ የሆናችሁበት ነገር የሌላኛችሁን ክፍተት እንዲሞላ በማድረግ ነገ ትልቅ ደረጃ የሚደርስ #HaSab ማፍለቅ ትችላላችሁ። እመኑኝ ከግቢ ከወጣችሁ በኋላ ይህን እድል አታገኙትም! ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ገንዘብ ያለው ሰው በብዛት የሚሰማራው ንግድ ላይ ነው! ብራቮ እናንተ ደግሞ ካፒታላችሁን በጋራ አድርጋችሁ ከባንክ ብድር ተባጥሳችሁ አምራች መሆን ትችላላችሁ። በየትኛውም መስክ ሊሆን ይችላል። ይህን የሚወስነው ያንተ እና የወዳጅህ እውቀት እና ፍላጎት ነው። ከፉክክር ይልቅ የትብብር ሀይል ይበልጥ ያደምቃል። ለየብቻችን ጭላንጭል ብርሃናትን መፍጠር ላይከብደን ይችላል። መድመቅ ግን ያለው ከህብረት ነው። ከባህር ውስጥ ብዙ ወሃ የሚጨልፈውም ቢሆን ከአንድ ይልቅ ሁለት ሦስት አቁማዳ ነው። አሁን ያለው ገበያ እጅግ ፉክክር ያለበት እና ንቁ አምራች እና ሻጭ የሚፈልግ ነው። Dave Ramsay ምን ይላል መሠለህ:- " Marketing is not an option for business that wants to keep their doors open." ሁሌም በሩ ክፍት የሆነ የማይናወጥ ስኬታማ የስራ መስክ ከፈለክ የያዝከውን እውቀት፣ ጥበብ፣ ልምድ ፣ የፈጠራ ሀሳብ እና ገንዘብ ይበልጥ እንዲያተርፍ አድርገህ መሸጥ የምርጫ ጉዳይ አይደለም!! ግዴታ እንጂ። ስለዚህ የምረቃ ጋወንህን እንዳወለክ ያለህን ለረጅም አመት ተባብረህ ካጠናኸው አብሮ አደርህ(dorm mate ለማለት😁) አልያም ብርቱ ከምትለው ወዳጅህ ጋር አዋህደህ በ bulk አምርት። በገበያው ውስጥ ሁሌም ክፍት የሆነ ቢዝነስ ይኑርህ! why not? ይህንን የጻፈልህ ያሬድ ነው። ገና ተማሪ ሳለህ በተለይ በአንድ ጤና እሳቤ፣ በእንስሳት ደህንነት ዙርያ መሥራት የምትፈልገው ልዩ ሀሳብ ካለህ መተባበር እንችላለን። ማናችንም የምንሰራቸው እያንዳንዱ ስራዎቻችን የሰዎችን፣ የእንስሳትን እና የአከባቢ ጤናን ያገናዘቡ ሊሆኑ ይገባል። እኚህን የሚያጓድል ስራ ብኩን ነው። የእንስሳትን ደህንነት የሚጠብቅ ሰው ሩህሩህ ነው። ርህራሄ እውቀት ብቻ ሳይሆን ለተፈጥሮ የሚጨነቅ መልካም ልብን ይፈልጋል። ይህን ለመፍጠር ትሩ ግንዛቤ እና ሁሉን ማጣቀሻ የሚደርገው የጋራ ህግ ያስፈልጋል። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ መስራት ፋይዳው ብዙ ነውና አሳብህን ልታጋራን ወደኋላ አትበል። ሀሳብህን መሬት ለማውረድ እና ተጽእኖ ለመፍጠር መተባበር እንችላለን። የተለየ #HaSab ካለህም አጋራን። @Adey67@yared2774 ደግሞ እንዲያነቡ ወዳጆችህን ጋብዝ! መልካም የረፍት ቀን!!