የልጥፍ ይዘት
#HaSab #Animal_welfare #Against_Donkey_slaughtering_For_Ejiao የአፍሪካ መሪዎች ጎሽ የሚያስብል ውሳኔ አስተላልፈዋል! ተፈጻሚነቱ የእኛን ክትትል ይፈልጋል። ከዚህ በፊት ይህ ጉዳይ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ Viral ሆኖ ሲዘዋወር ሁላችንም እናስታውሳለን። የአህያ ቄራ ጉዳይ። "At first our governments saw this as an opportunity, and many legal slaughterhouses opened in Africa, But between 2016 and 2019, about half of our donkeys were killed for the trade." ይህን የተናገሩት ዶ/ር ሰለሞን ኦንያንጎ(Dr Solomon Onyango) ከኬኒያው Donkey Sanctuary ከBBC ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው። አብዛኛዎቹ ሀገራት ቻይና የአህያ ቆዳ እንድትልኩልኝ እፈልጋለሁ ስትል ጉዳዩን የቆጠሩት እንደትልቅ እድል እና የውጪ ምንዛሪ ማግኛ መንገድ ነበር። ነገር ግን ለኢጃኦ የሚፈለገው የአህያ እርድ ከጥቅሙ ጉዳት የጎላ ሆኖ ተገኝቷል። ያሳለፍነው እሁድ የካቲት 10 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ የአለም የአህያ ብዛት 2/3 የሚይዙት 55 ሀገራት ግሽ የሚያስብል ውሳኔን አስተላልፈዋል። በአፍሪካ ለቆዳ ንግድ አህያ ማረድ ከእንግዲህ ወንጀል ይሆናል። ይህ ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ግን የእንስሳት ጤና እና ደህንነት ላይ የሚሰሩ ተቋማትን ብርቱ ክትትል ይፈልጋል። በተለይ በኢትዮጵያ ጉዳዩ የመንግስትን ይሁንታ ያገኘ እና ለህዝብ በቂ የሆነ መረጃ የሚሰጥበት ግልጽ ንግድ ባለመሆኑ በርግጥም ይህ ውሳኔ ተፈጻሚ መሆን አለመሆኑን እየተከታተለ ለህዝብ የሚያደርስ እና የሚጠይቅ አካል መኖር ግድ ይለዋል። ለዚህ ተቀዳሚዎቹ ባለ ሀላፊነቶች እኛው በዘርፉ ያለን ባለሞያዎች ነን። ሁሉም ሰው እንዲገነዘብ የምፈልገው ነገር ቢኖር ይህንን ንግድ የምንቃወምበት አበይት ምክንያት ንግዱ ቀጣይነት የሌለው እና ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን በመሆኑ ነው። ይህን ቻይና ራሷ ተመልክታዋለች። ከዚህ ቀደም የኢጃኦ ፍላጎቷን ለማሟላት ከራሷ ብቻ የአህያ ቆዳ ትጠቀም የነበረ ቢሆንም በሀገሪቱ የሚገኘው የአህያ ቁጥር እጅግ በመመናመኑ ፊቷን ወደሌሎች ሀገራት አዙራለች። ፊቷ የዞረባቸው ሀገራት ሁሉ በዚህ ንግድ መጎዳታቸውን አምነዋል። በአጠቃላይ የቻይና የአህያ ቆዳ ፍላጎት አለም ካላት 53 ሚልየን አህያ ቁጥር ጋር አይመጣጠነም። በአፍሪካ ለአህያ ደህንነት መሟገት ቅንጦት አይደለም! ለገጠር ማህበረሰብን ህልውና መቆርቆር እንጂ። ቸር ያቆየን! ያሬድ ኤርሚያስ