TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #6

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች48የዕይታ ቁጥር
ታትሟልሴፕቴ 1010/09/2023 08:15 ከሰዓት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

#HaSab #Animalhealth መኝታ ብቻ እስኪለይህ አብረሃት የምትውል ግልገል ከነ እናቷ ተሽጠው ወደ ገዥው አልሄድም ብላ ወዳንተ ዞራ ስትጮህ አልቅሰሃል? ጥጃ በስምህ ተገዝቶልህ ስታድግ ወተቷ ያንተ ነው ተብለሃል? ለውሻህ ስጋ ለድመትህ ሳምባ ለማምጣት በለሊት ቄራ ድረስ ሄደሃል? በምሽት ሁሉም መግባታቸውን ቆጥረህ አስገብተህ ጠዋት በራቸውን ከፍተህ ከከፍታው ጎጇቸው እየበረሩ ሲወርዱ ጥሬ ሰጥተህ እንቁላል የሚሰጡህን ዶሮዎች ተንከባክበሃል? ከእነዚህ ቢያንስ አንዱን ሳያደርግ ያደገ መኖሩን እጠራጠራለሁ። በልጅነታችን እንኳን ለሰው ለእንሰሳም እጅግ ስስ ነን። ፍቅራችን ልዩ ነው። ይህንን የልጅነት ስስት ጣዕም አሁን እያገኘሁት ነው። በእንሰሳት ህክምና ኮሌጅ ውስጥ ስለ እንሰሳት ጤና አጠናለሁ። ስቃያቸው ምንድነው፣ እንዴት ህመማቸውን ልረዳ እችላለሁ፣ ተፈጥሯቸው እንዴት ያለ ነው፣ ከሰዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዴት ያለ ነው ስል አስባለሁ። በፊት በፊት በውስጤ በለው ስሜት አሁን ደግሞ ተፈጥሯቸውን ይበልጥ በመረዳት ቅርባቸው ሁኛለሁ(ታድያለሁ)። ህመሙን ማስረጃ አንደበት የሌለውን ፍጡር ከመረዳት በላይ ምን አለ? በሀገራችን እንስሳ ማርባት የቅንጦት ጉዳይ አይደለም። ሁለት በሬዎች ከአባቶቻችን ጋር መግበው አስተምረው ያበቁን ነን። አንዲት ላም ቤተሰብ ስታስተዳድር የወተት ገቢ ምርቷ የቤተሰብ ቀዳዳ ሲሸፍን ተመልክቻለሁ። አንድ አህያ እውነት አንድ ብቻ ነች? ስንት ሸክማችንን አቅልላለች? በሀገሬ እልፍ ህዝብ አርብቶ አደር ነው። ህልውናው፣ የልጆቹ ተስፋ፣ በማህበረሰቡ ያለው ደረጃ እጁ ላይ ባለው እንስሳ ሀብት የተወሰነ ነው። የእነዚህ እንስሳት ጤና መታወክ እና ምርት መቀነስ የቤቱን መሠረት ያናጋዋል። ይህ መሠረት እንዳይናጋ ነው መማሬ። የእንስሳቱን ጤና መጠበቅ ጤናማ አመጋገብ እንዲኖረን ያደርግ የለ? ለወገን ጤና ነው መማሬ። ሀገሬ የምትኮራበት ኤክስፖርት የምታደርገው ሌጦ አላት። አለም ከኢትዮጵያ በተገኘ ቆዳ የተሰራ ጫማ ሲሉት ተሽቀዳድሞ ይገዛል። በእንክብካቤ ያደጉ የቆዳ ጤናቸው የተጠበቀ እንስሳት ሲኖሩን ደግሞ አስቡት። የእንስሳት ጤና ጥቅሙ እጅግ ብዙ ነው። Yared Ermias Second Year Student at AAU-CVMA