TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #9

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች54የዕይታ ቁጥር
ታትሟልሴፕቴ 1010/09/2023 08:17 ከሰዓት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

#HaSab #Exportmarket እያለ እንደሌለ! * ጥሩ መሠረት ያለው ነገር በሚገባ ሳይሰራበት ሲቀር እና ትከሉረት ሲነፈግ ያበሽቃል። ትልቅ ሀብት መፍጠር የሚችል ነገር ተይዞ እያለ እንደሌለ ሲኮን ግራ ያጋባል። ዛሬ በአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ለጉብኝት በሄድን ሰዓት ባስተዋልኩት ነገር የተሰማኝን ልበል። የቆዳና ሌጦ ነገር ሀገራችን ከሰባት አመት በፊት እንኳ እንደነበረችበት ጊዜ ከቡና ቀጥሎ የምትተማመንበት የውጪ ምንዛሪ አምጪ እየሆነ አይደለም። ፋብሪካዎች ኦና እየሆኑ ነው፣ አንዳንዶቹ ተዘግተዋል፣ሊለበሱ የሚገባቸው ሌጦዎች ማጌጫ እና መዘነጫ ከመሆን ይልቅ በእየመንገዱ አፍንጫችንን ይዘንባቸው እናልፋለን። የሚጣል ተረፈ ምርት(ቆሻሻ) እየሆኑ ነው። በርግጥ ለዚህ ምክንያቱ አለምአቀፍም ሀገር ተኮርም ተደማምሮ ቢሆን የማያበሽቅ ግን አይደለም! ቢሰራበት የስራ እድል፣ገንዘብ እና ሀብት የሚሆን ነገር ቆሻሻ ሆኖ የማናይበት ዘመንን እመኛለሁ(ኢንሻ ኣላህ) ሌላው እና የገረመኝ፤ በአለም የቅንጦት ፋሽን ገበያ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚይዘው የአዞ ቆዳ የኤክስፖርት መረቡ ከተበጠሰ 15 አመታትን መሻገሩ ነው። የአዞ ቆዳ ምርትን የሚሰጠው አየርባምንጭ አዞ እርባታ ማዕከል ቅርቤ እንደመሆኑ ይህንን ያክል ጊዜ ምርቱ ገበያ ውስጥ አለመኖሩን ሳውቅ አዝኛለሁ።(አይቼዋለኋ!) የአርባምንጭ አዞ እርባታ ማዕከል እስከ 20,000 አዞ መያዝ የሚችሉ ኩሬዎች ሲኖሩት በአመት 3000 የአዞ ቆዳ ለኤክስፖርት ገባያ ዝግጁ ማድረግ ይችላል።(ይሄ እንግዲ ሁሉ ነገር ከተመቻቸለት ነው) አንድ ሴንቲሜትር (1cm) የአዞ ቆዳ ውስጠኛው ክፍል እስከ 5$ ይሸጣል። አንድ አዞ ደግሞ 50cm ድረስ የሚረዝም ቆዳ ሊወጣው ይችላል(250$) እንግዲህ ለ15 ዓመት አንድም አልሸጥንም። መረጃዎች ሳስስ እንደዋና ምክንያት ሆኖ ያገኘሁት የገበያ ትስስር ማጣት እና የገበያ መቀዛቀዝ ነው። ይህ የሚያሳየው ማዕከሉ የገበያ ትስስሩ ቢጠናከርለት እና በጥሩ ሁኔታ ቢተዋወቅ መቸብቸብ ይቻላል(Dear Diaspora think about it!) ጥራቱ ላይ አድምተን ብንሰራ ደግሞ! አጀብ! ከዚህ ጋር በተያያዘ ቦታውን ለመጎብኘት የሚመጡ የቻይና አልፎ አልፎ የጀርመን ጎብኚዎች ስጋውን አስበልተው እንደሚወስዱ እና ለምግብነት እንደሚያውሉት አንድ የቦታው ባለሞያ ሲያወራ አስታውሳለሁ። የአዞ ስጋ በጠቀስኳቸው ሀገራት ተወዳጅ መብል ነው። ስለዚህ ይህ ማዕከል ወደነዚህ ሀገራት ስጋ ኤክስፖርት ማድር የሚችልበት መንገድ ቢታሰብበትስ??? POV: እያሉ እንደሌሉ እየጠቀሙ እንደ ቆሻሻ በምንተዋቸው ነገሮች ላይ እናተኩር። ችላ ባልናቸው በጣልናቸው ነገሮች ውስጥ እልፍ ሀብት አለ!