@ebcnewsnow · Post #53890 · 23.04.2026 г., 06:27
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ ************************ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ዛሬ ጠዋት ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት ዑመር ጌሌህ የተላከ መልዕክት በመያዝ የመጡትን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው መወያየታቸውን ገለጹ። በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገሮች መካከል ስላለው ትብብር መምከራቸውን አስታውቀዋል። #EBC#Ethiopia#Djibouti#diplomacy#diplomaticrelations