@ebcnewsnow · Post #51708 · 17.02.2026 г., 06:42
ለ2018 ጠቅላላ ምርጫ ተዘጋጅተዋል? ************** የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት፣ የፖለቲካ ስብራት መድኃኒት! በኢትዮጵያ ታሪክ ስልጣን በጉልበት እና በጠመንጃ የሚገኝበት አዙሪት ሀገራዊ ስብራታችንን ከባድ አድርጎት ቆይቷል። ዛሬ ግን ይህንን አዙሪት ሰብረን ለመውጣት ከሚያግዘንና የሀገረ መንግስት ግንባታችንን በጽኑ መሠረት ላይ ለመጣል የሚያስችለን ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። ምርጫ የፖለቲካ ስብራቶቻችንን የምንጠግንበት፣ የህዝብን ይሁንታ የምናረጋግጥበት እና ልዩነቶቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ የምንፈታበት ብቸኛው ሰላማዊ መንገድ ነው። ስልጣን ከህዝብ የሚመነጨው፣ ሀገር የምትረጋጋው እና ብልፅግና የሚረጋገጠውበዚሁ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ነው፡፡ እርስዎስ ለ2018 ጠቅላላ ምርጫ ተዘጋጅተዋል? #በምርጫ_ብቻ! #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopiai#GeneralElections