TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Python Заметки

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Најди сличен содржај

Изворен канал @pythonotes · Post #310 · 22 фев.

Сегодня будет самый "двоичный" ("двойковый"? "двушный"? "двойственный"?) момент на вашем веку 🤩 Больше двоек в дататайме вы не застанете! Успейте поймать момент! Будете показывать эпичный скриншот своим внукам))) 🥸 Для продуманных (ленивых): код на скрине, который сработает только сегодня и только 1 раз! ⏱ Открывайте окошки с часами и вперёд! #offtop

Hashtags

Резултати

Пронајдени 3 слични објави

Пребарај: #nationalbankofethiopia

当前筛选 #nationalbankofethiopia清除筛选
Borkena

@borkena · Post #5880 · 27.02.2026 г., 15:05

ብሔራዊ ባንክ በብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶችን ሙሉ በሙሉ አገደ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ በተለያዩ የንግድ መድረኮች አማካኝነት በኢትዮጵያ ብር ላይ ተመስርተው የሚከናወኑ የPeer-to-Peer (P2P) የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይቶች ሕገ-ወጥ መሆናቸውን አስታውቋል። ባንኩ የወቅቱ የቁጥጥር ማዕቀፍ ያለ ባንኩ ፈቃድ የብር ጥንድ የሆኑ P2P ዝግጅቶችን አልፈቅድም ብሏል። ብሔራዊ ባንክ የክሪፕቶ ንብረቶች ገበያ ከፍተኛ ዋጋ መዋዠቅ ያለበት፣ ለማጭበርበር (Fraud and Scams) የተጋለጠ፣ እና የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ማጭበርበር ስጋት ያለበት መሆኑን አስታውቋል። እነዚህ የP2P መድረኮች በተመሰቃቀለ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው፣ በባህላዊ የፋይናንስ ተቋማት የሚገኙ እንደ የገንዘብ ማጠብ መከላከያ (AML) ያሉ የደህንነት ጥበቃዎች የሏቸውም ነው የተባለው። በተጨማሪም በአለም አቀፍ ደረጃ አንዳንድ የP2P መድረኮች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ችግሮች በማጋጠማቸው ተጠቃሚዎች ገንዘባቸውን እንዳያወጡ መከልከላቸውን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለዲጂታል ንብረቶች አስተማማኝ እና የተደራጀ የቁጥጥር ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ከአለም አቀፍ እና ከአገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጿል። የቁጥጥር ማዕቀፉ በይፋ እስኪተገበር ድረስ፣ ህብረተሰቡ በብር የሚደረጉ የክሪፕቶ P2P ግብይቶችን ከመፈጸም እንዲቆጠብ አሳስቧል። #Ethiopia#AddisAbaba#Ethiopiannews#news#NationalBankofEthiopia#ብሄራዊባንክ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ'ሴንትራል ባንኪንግ' ሽልማትን አሸነፈ *********** የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በ'ሴንትራል ባንኪንግ' ተቋም የሚሰጠውን የ2026 የክፍያ እና የገበያ መሠረተ ልማት (Payments and market infrastructure development - wholesale) ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል። ባንኩ ለሽልማቱ የበቃው በኢትዮጵያ ዋና የፋይናንስ መሠረተ ልማት ላይ ከፍተኛ እና መጠነ-ሰፊ የማሻሻያ ሥራዎችን በተሳካ ሁኔታ በማከናወኑ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ሥርዓትን ለማዘመን የወሰዳቸው እርምጃዎች ለዚህ ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዳበቁት ተጠቁሟል። ይህ ሽልማት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችን መሠረት የገበያ መሠረተ ልማት ዝርጋታን በማሳደግ፣ የገበያ ተዓማኒነትን፣ የገንዘብ ፖሊሲ ስርጭትን እና ዘላቂ ዕድገትን በማጠናከር ሪፎርሞችን ይበልጥ ለማጥለቅ ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክረዋል ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገልጸዋል። #EBC#NationalBankofEthiopia#awards#winning

ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በሌላቸው መተግበሪያዎች የሚደረጉ የዲጂታል ግብይቶችን አገደ ****************** የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ክሪፕቶ ከረንሲን ጨምሮ ፈቃድ በሌላቸው የተለያዩ መተግበሪያዎች የሚከናወኑ የአቻ ለአቻ (P2P) የዲጂታል ግብይቶችን በጊዜያዊነት ማገዱን አስታወቀ። ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቦች ከባንኩ እውቅና በሌላቸው መተግበሪያዎች ግብይት እየፈጸሙ መሆኑ በክትትል እንደደረሰበት ጠቅሷል። እነዚህ መደበኛ ያልሆኑ ግብይቶች የገበያ መረጋጋትን ከማናጋት ባለፈ፣ ለሳይበር ወንጀል፣ ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ለፋይናንስ ሽብርተኝነት የተጋለጡ መሆናቸውን ባንኩ አብራርቷል። በተጨማሪም የውጭ ምንዛሪ ዋጋን የማሳሳትና የግብይት ግልጽነት ችግሮችን እንደሚያስከትሉ ገልጿል። ባንኩ የዲጂታል ግብይት ቴክኖሎጂዎችን ደህንነት የሚያረጋግጥ አጠቃላይ የቁጥጥር ማዕቀፍ በመዘርጋት ላይ መሆኑን ጠቁሞ፣ ይህ ማዕቀፍ ይፋ እስኪሆን ድረስ ማንኛውም ፈቃድ የሌለው የዲጂታል ግብይት የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል። የፋይናንስ ሥርዓቱን ታማኝነት ለመጠበቅም ከዓለም አቀፍ ተቆጣጣሪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እየተደረገ መሆኑንም ባንኩ አመልክቷል። #Ebc#Ethiopia#NationalBankOfEthiopia#DigitalCurrency#FinancialSecurity