TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
Terug naar kanalen
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar

TGINSIGHT CHAT

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow

News and media

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1 @ETVkidschannel @EBCWORLD1 @etventertainment1

Abonnees13.5万Huidige kanaalabonnees
Gevolgde posts1,008Geïndexeerde posts
Recent bereik83,330Som van recente weergaven
Recente posts

Recente posts

Tag: #ethiopia · 323 posts

当前筛选 #ethiopia清除筛选

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በ3.3 ቢሊዮን ብር ወጪ በጣና ዳርቻ የሚገነባውን ግዙፍ የሆቴል ፕሮጀክት አስጀመሩ *************************** ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ፣ በጣና ሐይቅ ዳርቻ የሚገነባውን ግዙፍ እና ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ ግንባታ ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል። ይህ 4PBS (ፎር ፖይንት ባይ ሸራተን) በሚል ስያሜ የሚገነባው ሆቴል፤ ታሪካዊውን ጣና ሆቴል ዘመኑን በዋጀና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ዳግም ለመገንባት ያለመ ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፤ የሚገነባው ግዙፍ ፕሮጀክት የከተማዋን የቱሪዝም ገጽታ ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሸጋግርና የሀገሪቱን የብልጽግና ጉዞ የሚያንፀባርቅ መሆኑን ገልጸዋል። ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በተለያዩ የልማት ዘርፎች እያመጣ ያለውን ለውጥ ያደነቁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህንንም ፕሮጀክት በስኬትና በተቀመጠለት ጊዜ የማጠናቀቅ ኃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል። ለፕሮጀክቱ ግንባታ 3.3 ቢሊዮን ብር በጀት የተያዘ ሲሆን፣ በግንባታው ሂደትም ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ግብዓቶች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ተመላክቷል። በአሸናፊ እንዳለ #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#TourismDevelopment#BahirDar#MidrocInvestmentGroup#LakeTana

4,930 views

ፍላጎቱን በገቢ ምርቶች ላይ የመሠረተ ሀገር፣ ነጻ እና ሉዓላዊ ነኝ ማለት አይችልም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ********************* ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018ን በይፋ በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ ሀገራዊ ምርትን ማሳደግ ከምጣኔ ሀብት ዕድገት ባለፈ የሀገርን ሉዓላዊነት እና ነጻነት ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። "አለማምረት በሌሎች ሰዎች በጎ ፈቃድ ላይ እንድንወድቅና ለተለያዩ ችግሮች እንድንጋለጥ ያደርገናል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው። በግብርናው ዘርፍ በተለይም እንደ ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር እና የማምረቻ መሣሪያዎችን በሀገር ውስጥ ማምረት ካልተቻለ፣ የምግብ ዋስትናን እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደማይቻል አጽንኦት ሰጥተዋል። ባለፉት ሁለት ወራት በነዳጅ እና በጋዝ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ፈተና በመጥቀስ፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የጋዝ እና የነዳጅ ሀብት እያላት ማምረት ባለመቻሏ በኢንዱስትሪው እና በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል መፈጠሩን በማሳያነት አንስተዋል። "እርዳታ የሚቀበል፣ ምግብ የሚለምን እና ፍላጎቱን በሙሉ በገቢ ምርት ላይ ብቻ የመሠረተ ሀገር፣ ነጻ እና ሉዓላዊ ነኝ ማለት አይችልም" ነው ያሉት። ጥገኝነት እና ልመና እስካላበቃ ድረስ ሀገራዊ ክብርን ማስጠበቅም ሆነ ለልጆች የሚተርፍ ነጻነትን ማረጋገጥ አዳጋች እንደሚሆንም አመላክተዋል። በመሆኑም፣ ከጥገኝነት የተላቀቀች እና ክብሯ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለመገንባት "የኢትዮጵያ ታምርት ቤተሰቦች" እና መላው የኢንዱስትሪው ዘርፍ ተዋናዮች ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የተጀመረውን የማምረት ንቅናቄ በትጋት፣ በኅብረት እና በቁርጠኝነት በማስቀጠል፣ ሉዓላዊነቷ የተከበረ ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ሁሉም በቁርጠኝነት እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል። በመሀመድ ፊጣሞ #Ethiopia#MadeInEthiopia#AbiyAhmed#EthiopiaDelivers#EBC

5,760 views

ስለ ሀገር ራሱን ፋኖ ብሎ የሚጠራው ቡድን ከፍተኛ አመራር ከነበሩት ረዳት ፕሮፌሰር እያሱ አባተ ጋር የተደረገ ቆይታ ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት በኢቲቪ ዜና ቻናል እና በኢቢሲ ዶትስትሪም አማራጮቻችን ይጠብቁን! #EBC#Ethiopia#SileHager

6,200 views

"ኢትዮጵያ ለእኛ በምናብ የምትሣል ሕልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት።" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed

7,390 views

አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ የማራቶን ሪከርዱ የመኪናው ታርጋ እንዲሆን ተወሰነለት ************* ባለፈው እሑድ በተካሄደው የለንደን ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር ከሁለት ሰዓት በታች መግባት የቻለው አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ፣ ሀገሩ ኬንያ ሲመለስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ለ49ኛ ጊዜ በተካሄደው የለንደን ማራቶን 1 ሰዓት 59 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ በመግባት አዲስ ታሪክ የጻፈው ሰባስቲያን ሳዌ፣ ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአይነቱ ልዩ የሆነ አቀባበል ተደርጎለታል። አትሌቱን በናይሮቢ ስቴት ሐውስ (ቤተ መንግሥት) ተቀብለው ያነጋገሩት ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ፣ ለተመዘገበው ድንቅ ውጤት ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት አበርክተውለታል። ፕሬዚዳንቱ አትሌቱ የዓለም ክብረ ወሰን በመስበሩ 5 ሚሊዮን እንዲሁም የለንደን ማራቶንን በማሸነፉ 3 ሚሊዮን፣ በአጠቃላይ የ8 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ሽልማት ሰጥተውታል። ከገንዘብ ሽልማቱ በተጨማሪም አትሌቱ የፈለገውን መኪና እንዲመርጥ እና የመኪናው የታርጋ ቁጥርም ታሪክ በሰራበት ሰዓት እንዲሰየም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። በዚህም መሠረት የመኪናው ታርጋ “1:59:30” ተብሎ እንዲጻፍ ይሆናል። ፕሬዚዳንት ሩቶ ይህ አጋጣሚ በሕይወት ዘመን አንድ ጊዜ ብቻ የሚከሰት ብርቅዬ ስኬት መሆኑን ገልጸው ሳዌን አሞካሽተዋል። በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ ባለው የለንደን ማራቶን፣ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻም በተመሳሳይ ከሁለት ሰዓት በታች በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። በአንተነህ ሲሳይ #EBC#Ethiopia#marathon#londonmarathon#record

6,710 views

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሞዛምቢኩ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ደማቅ አቀባበል አደረጉ ************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ የመጡትን የሞዛምቢክ ፕሬዝደንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት በክብር ተቀብለዋል። የፕሬዝደንቱ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግራል ተብሎ ይጠበቃል። ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ለእውነተኛ አፍሪካዊ አጋርነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል። #EBC#Ethiopia#PMOEthiopia#Mozambique#diplomacy

9,480 views

"ኢንዱስትሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብርናን ተክቶ ከፍተኛውን የኢኮኖሚ ድርሻ የሚይዝበት መዋቅራዊ ሽግግር በጥቂት ዓመታት ውስጥ የሚፈጸም ይሆናል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed#industry

7,210 views

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግዙፍ ፋብሪካዎችን መረቁ ***************************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን በይፋ መርቀዋል። እነዚህ በዛሬው ዕለት የተመረቁ የሶላር ፋብሪካዎች በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ የሚያቀርብ ይሆናል። ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ እንዲሁም የማይበገር ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#Industry

8,160 views

ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር ማያርድት ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ ************** በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርጉ የቆዩት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር ማያርድት ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ ተመልሰዋል። ፕሬዝዳንቱ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ሲመለሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ሽኝት አድርገውላቸዋል። ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር በቆይታቸው ከከፍተኛ የኢትዮጵያ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ይታወሳል። በአሸናፊ እንዳለ #EthiopianBroadcastingCorporation#ሳልቫ_ኬር#ተመስገን_ጥሩነህ#Ethiopia#SouthSudan#SalvaKiir#Diplomacy

6,550 views

“ሌላ ሀገር የላችሁም፤ በቅን ልብ ለሀገራችሁ ሥሩ” - ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ***************** የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከማኅበራዊ ሚዲያ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባለሙያዎች ጋር ተወያይቷል። በውይይቱ ላይ ተገኝተው ገለጻ ያደረጉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም፤ ማኅበራዊ ሚዲያ ለመልካም ነገር በቅን ልብ ከተጠቀምንበት ሀገር የመገንባት ኃይሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ዘመን የተሻገሩ ችግሮችን ለመፍታት ብቸኛው አማራጭ ምክክር መሆኑን ያስገነዘቡት ኮሚሽነሩ፣ “ሌላ ሀገር የላችሁም፤ ከኮሚሽኑ ጋር በመተባባር ለሀገራችሁ ሥሩ” ሲሉ ለማኅበራዊ ሚዲያ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባለሙያዎች መልዕክት አስተላልፈዋል። በመሆኑም ሀገራዊ ምክክሩ በሚያልፍባቸው ምዕራፎች በሀገር ባለቤትነት እና በኃላፊነት ስሜት ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ከጥቂት ወራት በኋላ በሚደረገው ሀገራዊ ጉባኤ ላይም ከቅድመ ምክክር ጀምሮ ከኮሚሽኑ ጋር በመተባበር የዜግነት ኃላፊነታችሁን መወጣት አለባችሁ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። በመድረኩ እስካሁን በኮሚሽኑ የተሠሩ ሥራዎችን እና ኮሚሽኑ ከማኅበራዊ ሚዲያ ባለሙያኑዎች የሚጠብቀውን ሥራ በተመለከተ በኮሚሽ ከፍተኛ ባለሙያዎች ገለጻ ተደርጓል። በመድረኩ የተሳተፉ ባለሙያዎች ያሏቸውን ጥያቄዎች አቅርበው በኮሚሽነር መላኩ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፤ ተሳታፊዎቹ ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ እንደሚሠሩም ማረጋገጣቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። #EBC#Ethiopia#Nationaldialogue#socialmedia#socialmediainfluencers

8,170 views

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡትን የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትን ተቀበሉ *********************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ለገቡት የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት በቤተ-መንግሥት አቀባበል አድርገዋል። ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ እና ዘላቂ ወዳጅነት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል። በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እና በጋራ ፍላጎቶች ላይ ለመምከር ፍሬያማ ውይይት እንደሚያደርጉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጉብኝት በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትሥሥር እና ሰላምን ለማረጋገጥ ሀገራችን ለምትከተለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተመልክቷል። #EBC#Ethiopia#SouthSudan#diplomacy#hornofafrica

6,860 views

አዲስ የሕግ ትርጉም፦ የሥራ ውል ማቋረጥ እና የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ********************* የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት፣ አንድ ሠራተኛ ያለ በቂ ምክንያት ከሥራ ሲቀር ስለሚወሰድ እርምጃ ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረውን የሕግ ትርጉም በመለወጥ አዲስ ውሳኔ አሳልፏል። ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት ይህ ችሎት ከመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የሕግ ትርጉም የሰጠ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት አንድ ሠራተኛ ለተከታታይ አምስት የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ያለ በቂ ምክንያት ከሥራ ገበታው ላይ ከቀረ፣ አሠሪው ምንም ዓይነት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳይጠበቅበት የሥራ ውሉን ወዲያውኑ ማቋረጥ ይችላል። ይህ አዲስ ውሳኔ "አሠሪው ለእያንዳንዱ ለቀረበት ቀን ማስጠንቀቂያ መስጠት አለበት" በሚል ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረውን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሙሉ በሙሉ የሻረ ነው። አዲሱ የሕግ ትርጉም የሥራ ዲሲፕሊንን ለማስከበርና የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትን ግልጽ በሆነ መንገድ ለመምራት ታቅዶ የተሰጠ በመሆኑ፣ በማንኛውም የፍትሕ አካል ዘንድ እንደ አስገዳጅ ሕግ ሆኖ ያገለግላል። ከመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀድሞው አሠራር ቀሪ ሆኖ በአዲሱ ትርጉም መሠረት ውሳኔዎች የሚሰጡ ይሆናል። በብርቱካን አስናቀ #Ethiopia#LabourLaw#FederalSupremeCourt#LegalRuling

5,910 views
123•••10•••20•••2627
VorigePagina 1 van 27Volgende