TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar

TGINSIGHT POST

Post #51600

@ebcnewsnow

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

Weergaven11,800Weergaven van post
Geplaatst11 feb11-02-2026, 14:54
Inhoud

Postinhoud

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድ ጋር ተወያዩ ********************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድን ተቀብለው በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል። ‎"ውይይታችን በዐበይት ዘርፎች ለረዥም ዘመናት የዘለቀውን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ትስስር በማስፋት እና የወል ፍላጎቶቻችን በሆኑ ቀጣናዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራችንን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት። #Ethiopia#SaudiArabia#diplomacy#AbiyAhmed#EthiopianBroadcastingCorporation#EBC