TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar

TGINSIGHT POST

Post #52380

@ebcnewsnow

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

Weergaven9,380Weergaven van post
Geplaatst14 mrt14-03-2026, 15:23
Inhoud

Postinhoud

ዮርዳኖስና ቱርክዬ በጋሞ ዞን በደረሰው አደጋ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ሐዘን ገለጹ ************************ የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋሞ ዞን በደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘንና ልባዊ አጋርነት ገልጿል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የተከሰተው ይህ አደጋ ለሰው ሕይወት መጥፋትና መፈናቀል ምክንያት በመሆኑ፣ የዮርዳኖስ መንግሥት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን መቆሙን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ፉአድ አል-ማጃሊ አረጋግጠዋል። አምባሳደሩ ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን የተመኙ ሲሆን፣ አደጋ ለደረሰባቸውም ፈጣን ማገገምን እንዲሁም የጠፉ ዜጎች እንዲገኙ ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል። በተመሳሳይ የቱርክዬ መንግሥት በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ ሰንደቅዓላማዋን ዝቅ አድርጋ እንዲውለበለብ በማድረግ ለደረሰው አደጋ ያላትን ጥልቅ ሐዘንና አጋርነት ገልጻለች። ይህ ዓለም አቀፍ የሐዘን መግለጫና አጋርነት በኢትዮጵያ ላይ ለደረሰው አደጋ ያለውን ትኩረትና የወንድማማችነት ትስስር የሚያሳይ ነው። በቢታኒያ ሲሳይ #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#Gamo#Jordan#Türkiye#Solidarity