Postinhoud
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ **************** መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎቻቸውን በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል። መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ባካሄደው 6ኛ ዙር የተማሪዎች ምረቃ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ 457 ወንድ እና 241 ሴት በድምሩ 698 ተተማሪዎችን አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው ባለፉት አምስት ዙሮች ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቅ ችሏል። ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን 1 ሺህ 08 ተማሪዎችን አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው ለ19ኛ ጊዜ ያስመረቃቸው ተማሪዎች በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምት እና በርቀት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው። ከተመራቂዎቹ መካከል 919ኙ በመጀመሪያ ዲግሪ፤ 87ቱ በሁለተኛ ዲግሪ እና ሁለት ተማሪዎች ደግሞ በሦስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል። ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲም ለ16ኛው ዙር በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት ፕሮግራሞች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 904 ተማሪዎችን አስመርቋል። በንፍታሌም እንግዳወርቅ #Ethiopia#highereducation#university#graduation https://web.facebook.com/share/p/1FGjVmKaBE/