TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar

TGINSIGHT POST

Post #52948

@ebcnewsnow

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

Weergaven10,900Weergaven van post
Geplaatst2 apr02-04-2026, 03:04
Inhoud

Postinhoud

የመደመር አንቀፅ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ለማስፋፋት ባለፉት ዓመታት ሰፊ ኢንቨስትመንት ተካሂዷል፡፡ ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትም ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። የሕዳሴ የኃይል ማመንጫን ጨምሮ ሌሎች በጅምር ያሉና በሚገባ አገልግሎት እየሰጡ ያልነበሩ ማመንጫዎችን ወደ መሥመር ለማስገባት ተችሏል፡፡ በዚህም ሀገራችን ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚያስፈልጋትን የኃይል አቅርቦት በሚገባ መሸፈን ችለናል፡፡ ካለን ዕምቅ ዐቅም አንጻር ሌሎች ብዙ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን የምንቀርጽና የምንተገብር ቢሆንም፣ የኃይል አቅርቦት ግን ጎዶሎ ሆኖ አምራችነትን ከሚጎትቱ ጉዳዮች መካከል መሆኑ አብቅቷል፡፡ በሌላ በኩል ግን የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝ ከማድረግና የኃይል መቆራረጥን ከመቅረፍ አኳያ ቀላል የማይባል የማሻሻያ ሥራ ይጠብቀናል፡፡ የመደመር መንግሥት ገፅ 206 Ethiopian Broadcasting Corporation #Medemer#GERD#Ethiopia