TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
Inhoud
Postinhoud
የመደመር አንቀፅ አምራች ኢንዱስትሪው ለአንድ ሀገር አጠቃላይ የውስጥ ምርት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደርጋል ሲባል በቀጥታ ከሚኖረው አስተዋጽዖ በላይ ነው፡፡ በሌሎች ዘርፎች ላይ በሚኖረው ተጽዕኖ የሚያበረክተውም አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው። የተሻለ ገቢ ያለው ማኅበረሰብ ለመፍጠር ለሚደረገው ርብርብም ዋነኛው የትኩረት ዘርፍ የአምራች ዘርፍ ነው፡፡ አምራች ኢንዱስትሪውን ወደ ከፍታ የማምጣትና የማበልጸግ ጉዳይ፣ ከኢኮኖሚና ከማኅበራዊ ጥቅሙ ባለፈ፣ ደኅንነትንና ሉዓላዊነትን ከማስከበር አንጻርም ሚናው ከፍተኛ ነው። በሌሎች ሀገራት አምራች ኢንዱስትሪ ላይ ጥገኛ ሆኖ፣ ራስን ሳይችሉ፣ ሉዓላዊ ሀገርነን ማለት ቀልድ ነው፡፡ የመደመር መንግሥት ገፅ 197 Ethiopian Broadcasting Corporation #IPDC#Ethiopia#industry#Medemer