TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
Inhoud
Postinhoud
የኢትዮጵያ እና አርሜንያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል - አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ************************ የኢትዮጵያ እና አርሜንያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ። አፈ ጉባኤው የአርሜንያ አምባሳደር ሳሃክ ሳርጊሲያንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፤ በውይይቱም በንግድ፣ በፋይናንስ እና በትምህርት ዘርፎች ልምድ ለመለዋወጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቷል። በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት የፓርላማ ግንኙነት ለማጠናከር እና በዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ መድረኮች በቅንጅት ለመሥራት በሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የኢትዮጵያ እና የአርሜንያ የሁለትዮሽ ትሥሥር ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ እና ታሪካዊ ግንኙነት መሆኑን ገልጸው፣ ይህንን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። የአርሜንያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ በመጠቀም መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈስሱም ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ እና አርሜንያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት #EBC#Ethiopia#Armenia#diplomacy