TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #310 · 2月13日

by iPhone13 Pro #摄影

Hashtags

Results

找到 5 条相似帖子

搜索 #nationaldialogue

当前筛选 #nationaldialogue清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51758 · 2026/02/18 14:45

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተጨማሪ 8 ወራት የሥራ ጊዜ ተሰጠው ******************* የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተጨማሪ 8 ወራት የሥራ ጊዜ እንዲሰጠው የሕዝብ ተወካዮች ሞክር ቤት ወሰነ። ‎ ‎ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የኮሚሽኑን የአራት ዓመታት የሥራ ሪፖርት አድምጧል። ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ጥሩ ሥራ መሥራቱ ተጠቅሷል። ‎የተሰጠው ጊዜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሚያበቃ በመሆኑ በትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ እና የምክክር ጉባዔውን ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጠይቋል። ‎ ‎ምክር ቤቱም ከየካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚቆጠር ተጨማሪ 8 ወራት የሥራ ጊዜ እንዲሰጠው በሙሉ ድምፅ ወስኗል። ‎ ‎በባዬ ሙላት ‎ #Ethiopia#NationalDialogue#HoPR

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53967 · 2026/04/24 16:31

“ሌላ ሀገር የላችሁም፤ በቅን ልብ ለሀገራችሁ ሥሩ” - ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ***************** የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከማኅበራዊ ሚዲያ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባለሙያዎች ጋር ተወያይቷል። በውይይቱ ላይ ተገኝተው ገለጻ ያደረጉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም፤ ማኅበራዊ ሚዲያ ለመልካም ነገር በቅን ልብ ከተጠቀምንበት ሀገር የመገንባት ኃይሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ዘመን የተሻገሩ ችግሮችን ለመፍታት ብቸኛው አማራጭ ምክክር መሆኑን ያስገነዘቡት ኮሚሽነሩ፣ “ሌላ ሀገር የላችሁም፤ ከኮሚሽኑ ጋር በመተባባር ለሀገራችሁ ሥሩ” ሲሉ ለማኅበራዊ ሚዲያ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባለሙያዎች መልዕክት አስተላልፈዋል። በመሆኑም ሀገራዊ ምክክሩ በሚያልፍባቸው ምዕራፎች በሀገር ባለቤትነት እና በኃላፊነት ስሜት ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ከጥቂት ወራት በኋላ በሚደረገው ሀገራዊ ጉባኤ ላይም ከቅድመ ምክክር ጀምሮ ከኮሚሽኑ ጋር በመተባበር የዜግነት ኃላፊነታችሁን መወጣት አለባችሁ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። በመድረኩ እስካሁን በኮሚሽኑ የተሠሩ ሥራዎችን እና ኮሚሽኑ ከማኅበራዊ ሚዲያ ባለሙያኑዎች የሚጠብቀውን ሥራ በተመለከተ በኮሚሽ ከፍተኛ ባለሙያዎች ገለጻ ተደርጓል። በመድረኩ የተሳተፉ ባለሙያዎች ያሏቸውን ጥያቄዎች አቅርበው በኮሚሽነር መላኩ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፤ ተሳታፊዎቹ ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ እንደሚሠሩም ማረጋገጣቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። #EBC#Ethiopia#Nationaldialogue#socialmedia#socialmediainfluencers

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51168 · 2026/01/21 13:53

ሀገራዊ ምክክር፤ ለነገዋ ኢትዮጵያ አዲስ የሰላም መንገድ! 🇪🇹 *********** ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት፤ ታሪካችንም እንደዛው። ሆኖም በታሪካችን ውስጥ የተፈጠሩ ስብራቶች፣ በትርክቶቻችን መካከል ያሉ ልዩነቶች እና ለዘመናት የዘለቁ የፖለቲካ አለመግባባቶች ዛሬም ድረስ ፈተና ሆነው ቀጥለዋል። ሀገራዊ ምክክር ለምን አስፈለገ? ጥላቻን በውይይት፣ ጥርጣሬን በመተማመን፣ እና ጠመንጃን በሐሳብ ለመተካት የታለመ ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው። ይህ ምክክር የጥቂት ሰዎች ድርድር ሳይሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁሉም ያለልዩነት የሚሳተፉበት የኢትዮጵያውያን መድረክ ነው። ኢትዮጵያ እንደ አንድ ትልቅ ቤት ናት። ቤቱ ሲጠብበን፣ ግድግዳው ሲሰነጠቅ እና ጣራው ሲያፈስ፣ መፍትሔው ቤቱን ማፍረስ ሳይሆን በጋራ ተቀምጦ መጠገን ነው። ሀገራዊ ምክክሩ ይህንን ታሪካዊ እድል ይዞልን መጥቷል። ኢትዮጵያዊነት ማለት የአንድ ቀለም ድምር ሳይሆን የብዙ ቀለማት ውህደት ነው። በምክክሩ ወቅት የምናቀርበው የተለየ ሐሳብ ሀገራችንን የተሟላች ያደርጋታል። ዛሬ ተነጋግረን የማንፈታው ችግር ለልጆቻችን የቤት ስራ ሆኖ ይተርፍብናል። ይህ ምክክር ቂምን ለመቅበርና ይቅርታን ለመዝራት የቀረበ ታላቅ እድል ነው። ከምክክሩ ምን ይጠበቃል? ✅ የጋራ መግባባት፦ በሚያቃቅሩን ታሪካዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራራቢ ሐሳብ መያዝ። ✅ ጠንካራ ተቋማት፦ ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ሀገራዊ ተቋማትን መገንባት። ✅ ዘላቂ ሰላም፦ ለግጭት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን ከስራቸው ነቅሎ መፍትሔ ማስቀመጥ። የእኛ ድርሻ ምንድነው? የምክክር ሂደቱ ውጤታማ የሚሆነው ሁላችንም በቅን ልቦና ስንሳተፍበት ነው። ልዩነቶቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ አቅርበን፣ ለልጆቻችን የምትመችና የተረጋጋች ሀገር ለማሳደር የሁላችንም ባለቤትነት እና ተሳትፎ ያስፈልጋል። ልዩነቶቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ አምጥተን፣ በንግግር አሸንፈን፣ የምትከበር ሀገርን ለልጆቻችን እናውርስ። በምክክሩ ላይ እንሳተፍ!! ንግግር የሰላም መንገድ ነው! መነጋገር ያሸንፋል! 🤝 #ኢትዮጵያ#ሀገራዊምክክር#ሰላም#NationalDialogue#Ethiopia#Unity

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52114 · 2026/03/06 13:52

የሀገራዊ ምክክር 4 ዋና ዋና ጥቅሞች ****** 1. ከጠመንጃ ወደ ጠረጴዛ (ፖለቲካዊ መረጋጋት) 2. ማህበራዊ መግባባትና ዕርቅ (ብሔራዊ ፈውስ) 3. የኢኮኖሚ መረጋጋትና የኢንቨስትመንት ዕድገት 4. ጠንካራ የዲሞክራሲ ሥርዓትና የሀገር አንድነት #ሀገራዊ_ምክክር#ሰላም#ኢትዮጵያ#ብሔራዊ_ዕርቅ#NationalDialogue#EthiopianBroadcastingCorporation

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52075 · 2026/03/05 19:48

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፡ ለዘላቂ ሰላምና ለጋራ ብሔራዊ ስምምነት አዲስ ምዕራፍ **************** የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ውስብስብ ፈተናዎችን እየተጋፈጠ፣ ሀገራዊ መግባባትን ለማስፈን የሚያስችሉ ተጨባጭ ሥራዎችን በትጋት እያከናወነ ይገኛል። በሂደቱ በዋናነት ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ፣ አካታችና ተዓማኒ ለማድረግ የሚያስችሉ የዝግጅት ተግባራትን ቅድሚያ ሰጥቶ ሲያከናውን ቆይቷል። ኮሚሽኑ ጠንካራ ተቋማዊ አወቃቀርና የሕግ ማዕቀፍ በመዘርጋት ለሥራው ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩም ባለፈ፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች ሕዝባዊ ተሳትፎን መሠረት ያደረገ የተሳታፊዎች ልየታና የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራዎችን በስኬት አከናውኗል። #NationalDialogue#PeaceBuilding#ConflictResolution#NationalConsensus#EastAfrica#InclusiveDialogue