TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← () => "翠楼屋"

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

查找相似内容

Source channel @lambdaexpression · Post #310 · 2月13日

by iPhone13 Pro #摄影

Hashtags

Results

找到 1 条相似帖子

搜索 #sciencediscovery

当前筛选 #sciencediscovery清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51177 · 2026/01/21 21:03

የ2.6 ሚሊዮን ዓመታት ዕድሜ ያለው አዲስ የሰው ዘር ቅሪተ አካል በአፋር ተገኘ! ************** ኢትዮጵያ በድጋሚ የዓለምን ትኩረት የሳበ ትልቅ ሳይንሳዊ ግኝት አስተናግዳለች። በአፋር ክልል በሚገኘው ሚሌ-ሎጊያ መካነ ቅርስ ስፍራ፣ ከዚህ ቀደም ተገኝቶ የማይታወቅና "ፓራንትሮፐስ" (Paranthropus) የተሰኘ የ2.6 ሚሊዮን ዓመታት ዕድሜ ያለው የቅድመ ሰው ዘር ቅሪተ አካል ተገኝቷል። ግኝቱን የተመለከቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ አዲስ ግኝት፦ ይህ የቅድመ ሰው ዘር ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ከተገኙት ዝርያዎች የተለየና አዲስ መሆኑን ተመራማሪዎቹ አረጋግጠዋል። የጥናት ቡድኑ፦ ግኝቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ዝነኛ በሆኑት ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ (ከቺካጎ ዩኒቨርሲቲ) በሚመራ ቡድን የተገኘ ነው። የኢፌዴሪ ኩራት፦ የኢፌዴሪ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንደገለጹት፥ ግኝቱ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን ዳግም ያረጋገጠ ነው። የተለየ ባህሪ፦ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ እንዳሉት፥ ይህ "ፓራንትሮፐስ" የተሰኘው ዝርያ አካባቢን የመላመድ ከፍተኛ ችሎታ የነበረው በመሆኑ በተለያዩ አካባቢዎች ይኖር እንደነበር በጥናቱ ተረጋግጧል። ፋይዳው፦ ይህ ግኝት ለሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት እና ለዲፕሎማሲ እንቅስቃሴያችን ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ ወጣት ተመራማሪዎችን በዘርፉ ለማፍራት ትልቅ መነሳሳት ይፈጥራል ተብሏል። የሰው ዘር መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ ታሪኳን ማደሷን ቀጥላለች! #ኢትዮጵያ#አፋር#ቅርስ#የሰውዘርመገኛ#Ethiopia#Afar#LandOfOrigins#ScienceDiscovery#HumanOrigin#ZeresenayAlemseged#TourismEthiopia