ከጉባኤ አዳራሾች ባሻገር የሚተርክ አዲስ ገጽታ እና የኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ዝግጁነት
*******************
ኢትዮጵያ 39ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 2ኛውን የጣሊያን-አፍሪካ ስብሰባ ለመካፈል ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ከፍተኛ ልዑካንን ለመቀበል ከመቼውም ጊዜ በላይ ስንዱ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
መዲናዋ በከፍተኛ ጥራትና በዘመናዊ መልክ የተገነቡ ዓለም አቀፍ የስብሰባ አዳራሾችን እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ምቹ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማሟላት እንግዶቿን ለመቀበል በላቀ ደረጃ መዘጋጀቷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
ይህ አዲሱና ማራኪው የከተማዋ ገጽታ የእንግዶችን ቆይታ ልዩና የማይረሳ እንደሚያደርገው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተሳታፊዎች ከጉባኤው መድረኮች ባሻገር በአፍሪካውያን ጥረት እያደገ የመጣውን አዲሱን የቱሪዝም ዘርፍ እንዲመለከቱና ቆይታቸውን እንዲያራዝሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ይህ ዝግጁነት ኢትዮጵያ ለዲፕሎማሲያዊ ሁነቶች ያላትን ምቹነት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ አህጉራዊ ትብብርንና የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት ዳግም ያረጋገጠ መሆኑ ተመላክቷል።
#Ethiopia#PMAbiyAhmed#AfricanUnion#AUSummit2026#ItalyAfricaSummit#TourismEthiopia#EthiopianBroadcastingCorporation
ኢትዮ - ጅቡቲ ባቡር - ለቱሪዝም፤
ባቡርን አንዱ የጉዞዎ አካል አድርገው የቱሪስት መስህብ ቦታዎችን መጎብኘት የሚያስችሉበት አዲስና ልዩ አማራጭ አቅርበንልዎታል።
መልካም የጉብኝት ሳምንት!
Ethio-Djibouti Railway for Tourism
The Ethio-Djibouti Railway is not only a vital economic corridor but also an emerging gateway for tourism.
#PMOEthiopia
#TourismEthiopia
#VisitEthiopia
#VisitOromia
#Ethio_Djibouti_Railway
Ethio-Djibouti Railway
Connecting Business
Find us on: 👇👇👇
📌Facebook: https://www.facebook.com/share/15vDenutJd/?mibextid=wwXIfr
📌 Telegram: https://t.me/ethiodjiboutirailwayt.me+1t.me+1
📌Web: https://www.edrsc.com
📌TikTok: @ethiodjiboutirailway
📌youtube:https://www.youtube.com/channel/UCJCVzH-JGvnOPfsbrDFDIjQ
📌Call center: 9546
የ2.6 ሚሊዮን ዓመታት ዕድሜ ያለው አዲስ የሰው ዘር ቅሪተ አካል በአፋር ተገኘ!
**************
ኢትዮጵያ በድጋሚ የዓለምን ትኩረት የሳበ ትልቅ ሳይንሳዊ ግኝት አስተናግዳለች።
በአፋር ክልል በሚገኘው ሚሌ-ሎጊያ መካነ ቅርስ ስፍራ፣ ከዚህ ቀደም ተገኝቶ የማይታወቅና "ፓራንትሮፐስ" (Paranthropus) የተሰኘ የ2.6 ሚሊዮን ዓመታት ዕድሜ ያለው የቅድመ ሰው ዘር ቅሪተ አካል ተገኝቷል።
ግኝቱን የተመለከቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
አዲስ ግኝት፦ ይህ የቅድመ ሰው ዘር ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ከተገኙት ዝርያዎች የተለየና አዲስ መሆኑን ተመራማሪዎቹ አረጋግጠዋል።
የጥናት ቡድኑ፦ ግኝቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ዝነኛ በሆኑት ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ (ከቺካጎ ዩኒቨርሲቲ) በሚመራ ቡድን የተገኘ ነው።
የኢፌዴሪ ኩራት፦ የኢፌዴሪ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንደገለጹት፥ ግኝቱ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን ዳግም ያረጋገጠ ነው።
የተለየ ባህሪ፦ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ እንዳሉት፥ ይህ "ፓራንትሮፐስ" የተሰኘው ዝርያ አካባቢን የመላመድ ከፍተኛ ችሎታ የነበረው በመሆኑ በተለያዩ አካባቢዎች ይኖር እንደነበር በጥናቱ ተረጋግጧል።
ፋይዳው፦ ይህ ግኝት ለሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት እና ለዲፕሎማሲ እንቅስቃሴያችን ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ ወጣት ተመራማሪዎችን በዘርፉ ለማፍራት ትልቅ መነሳሳት ይፈጥራል ተብሏል።
የሰው ዘር መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ ታሪኳን ማደሷን ቀጥላለች!
#ኢትዮጵያ#አፋር#ቅርስ#የሰውዘርመገኛ#Ethiopia#Afar#LandOfOrigins#ScienceDiscovery#HumanOrigin#ZeresenayAlemseged#TourismEthiopia