ከወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር የተሰጠ መግለጫ በዛሬዉ ዕለት ማለትም የካቲት 16/2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት እና ራያ የምርጫ ክልሎች በተመለከተ የይገባኛል ጥያቄ እስኪፈታ የሁመራ፣ የአዲረመጥ፣ የኮረም ኦፍላ፣ የጠለምት እና የራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች ከትግራይ ክልል ዉጪ ሆነዉ ለብቻቸዉ በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቁጥር ፌደም/አፌ/5/13138 ለቦርዱ በጻፈው ደብዳቤ በማስታወስ የተሰጠዉ ውሳኔ ይፋ ማድረጉ የማህበረሰቡ የዘመናት ጥያቄ እና አቤቱታ ምላሽ ለመስጠት የተወሰደ እንደ አንድ በጎ እርምጃ እንደሆነ ተመልክተናል። 2013 ዓ.ም በተካሄደዉ 6ኛዉ አገራዊ ምርጫ አከባቢው ከትህነግ አገዛዝ ነፃ ቢወጣም የመምረጥ እና መመረጥ ህገ መንግስታዊ መብቱ ሳይረጋገጥ ቀርቷል። በመሆኑም የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ማህበረሰብ በአገር ደረጃ ውክልና ሳይኖረው፣ የዜግነት መብቱ ሳይጎናፀፍ እና በጀት ሳያገኝ መቆየቱ ይታወቃል። የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት እና ራያ አከባቢ ከደርግ ውድቀት ማግስት የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ከመፅደቁ በፊት 1984 ዓ.ም በጉልበት፣ የማህበረሰቡ ፍላጎት እና አሰፋፈር ግምት ውስጥ ሳያስገባ (Unlawful and Forceful Annexation) በኋላ ትግራይ ክልል የሆነው ክልል አንድ (Region-1) የተካለለ መሆኑ ግልጽ ነው። ይህም የሽግግር ቻርተሩ አንቀፅ 13 እና አዋጅ 7/1984 በመጣስ ከህግ ውጭ የተፈፀመ ነበር፡፡ በመቀጠል በአገሪቱ ተንሰራፍቶ የነበረዉ ህዉሓት መር አንባገናነዊ የኢህአዴግ መንግስት በማህበረሰቡ ላይ በርካታ ግፍ እና በደል እየፈፀመ መቆየቱ የአደባባይ ሐቅ ነው። ማህበረሰቡ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የማንነት እና ወሰን ኮሚቴ በማደራጀት ህጋዊ በሆነ መንገድ ለሚመለከተዉ አካል ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል። እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ህዝብ ከነፃነት ማግስት አማራዊ ማንነቱን ህጋዊ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲቋጭ በተለያየ መንገድ ሲጠይቅ ቆይቷል። በመሆኑ የፌደሬሽን ምክር ቤት ከትግራይ ክልል ውጪ በመሆን አከባቢዎቹ ምርጫ እንዲያደርጉ የተወሰነው ውሳኔ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ይህ የመምረጥ እና መመረጥ መብት በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 38 በግልፅ የተደነገገ መብት ነው፡፡ እንዲሁም ይህ የውሳኔ ኃሳብ በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት አንቀፅ 10/4 የተቀመጠ ነው፡፡ ነገር ግን በትግራይ ክልል ለመስራት የተቋቋሙ እንደ እነ ስምረት ያሉ የትግራይ ፓርቲዎች ‹‹ህገ መንግስታዊ ስርዓት አልበኝነት የሚያውጅ›› በማለት መፈረጃቸው እጅግ የሚያሳዝን ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ይህም የዜጎች ህገ መንግስታዊ እና ዴሞክራሲዊ መብት የሚነጥቅ እና ኢ-ፍትኃዊ የሆነ አቋም በመሆኑ የሚወገዝ ተግባር ነው፡፡ በመጨረሻ ከፌደሬሽን ምክር ቤት በተፃፈዉ ደብዳቤ መሰረት ምርጫ ቦርዱ ይፋ ያደረገዉ ዉሳኔ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ማንነት ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባትና ለወደፊቱ የህዝቡ ድምፅ የሚከበርበት በር ከፋች የሆነ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን ውሳኔዉ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን የተወሰደ በጎ እርምጃ መሆኑ፤ የህውሓት ጸረ ሰላም አቋም እና አደናቃፊ የሆነ አሉታዊ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ማህበረሰብ በፌደራል ደረጃ ብቻ ሳይሆን በአማራ ክልል ምክር ቤት ጨምሮ ህጋዊ ውክልና እንዲኖረዉ አበክረን እንጠይቃለን። የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር የካቲት 16/2018 ዓ.ም. ሁመራ #Ethiopia#news#Wolkait#Tegede
TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
by iPhone13 Pro #摄影
Hashtags
Results
找到 1 条相似帖子
搜索 #tegede
当前筛选 #tegede清除筛选