#HaSab@Hasab_2016 · Post #11 · 2023/09/10 20:18
#HaSab
#Veteducation
የሀይስኩል ተማሪዎች ስለ እኛ ምን ያስባሉ?
ዛሬ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በምሰራበት የኩሪፍቱ ሮትራክት ክለብ አማካኝነት ከ2ተኛ ደረጃ እና መሠናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር በ profession day መገናኘት ችዬ ነበር። የመርሃ ግብሩ ዋነኛ አላማ ተማሪዎች መሆን የሚፈልጓቸው ፊልዶች እና የስራ መስኮች ውስጥ ያሉ እና እየተማሩ የሚገኙ ሰዎች ስለ ሞያው መጠየቅ የሚፈልጓቸውን ጥያቄዎች በመጠየቅ ተጨባጭ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ ነበር። እኔ የእንስሳት ህክምና ተማሪዎችን(DVM) በመወከል ከጎኔ የምትመለከቷት ምዕራፍ ተወልደ ደግሞ የእንስሳት ህክምና ላቦራቶሪ ቴክኖሎጂ(VLT) ተማሪዎችን በመወከል ተገኝተናል።
በዝግጅቱ ላይ ከተገኙት ተማሪዎች እጅግ ጥቂት የሚባሉት ወደ እኛ በመምጣት ስለ እንስሳት ህክምና ለማወቅ ፍላጎት ያሳዩ ሲሆን፤ የጥያቄዎቻቸው ይዘት እና ማወቅ የሚፈልጉት ከዚህ በማስከትል የዘረዘርኳቸው ሆነው አግኝተናል።
-የእንስሳት ህክምና ክትባት ከመስጠት ውጪ ምንድነው የሚሰራው?
-የእንስሳት ህክምና ከሰዎች ህክምና የሚለየው ምንድነው?
-የእንስሳት ሀኪም ሰውን ማከም ይችላል?
-የእንስሳት ህክምና ትምህርት ጊዜ የሚፈጀው ምን ያህል ነው?
-እኔ የእንስሳት ሀኪም መሆን እፈልጋለሁ ግን የእንስሳት ሀኪሞች ደግሞ ብር ብዙ አያገኙም!
-ሰዎች ያን ያክል ትኩረት ሰጥተው እንስሳን ያሳክማሉ?
-በውሻ ተነከስን ስንል ሀኪሞች ውሻው አምጡት የሚሉን ለምንድነው?
በአጠቃላይ ለተጠየቅናቸው ጥያቄዎች የእንስሳት ጤና ዘርፍ የስራው መስክ ሰፊ እና ጉራማይሌ መሆኑን አውስተን በአጭሩ ለመረዳት፤ የክሊኒክ ስራዎች(Clinical practice)፣የስነ ህይወት ጤና ምርምሮች(biomedical researches)፣ ትምህርት(education)፣ የላቦራቶሪ ምርመራዎች(diagnostic laboratory)፣ የማማከር ስራ(consultation)፣የሀገርን የምግብ ደህንነት እና አቅርቦት ማሳለጥ( safeguarding our nations food safety and supply)፣እና የህብረተሰብ ጤና(public health) የትኩረት አቅጣጫቸው መሆኑን ለማስረዳት ሞክረናል።
ከነበረን ቆይታ እንደተረዳነው የሚመጣው ትውልድ ስለ እንስሳት ህክምና በወፍ በረረር ከመስማት ውጪ ገና በበቂ እንዳላወቀው እና አሁን ያለውጰባለሞያ ያለበት የኑሮ ሁኔታ ወደፊት እኔም ብገባ እንዲህ ነው የምሆነው የሚል ስጋት እንዳለው ተረድተናል። በተጨማሪም ሰዎች በግል የሚሰሯቸው የእንስሳት እርባታ እና መሰል ስራዎች በሌሎች የዘርፉ ባለሞያ ባልሆኑ ሰዎች በሰፊው እንደመሠራታቸው እንዲህ ያለው ስራ አላማ ተይዞለት ለትምህርት እንደሚገባ ግንዛቤው ያለ አይመስለኝም። ለእንሰሳት ያላቸው ርህራሄ እና ፍቅር ግን እጅግ አስደሳች መሆኑን በሚያወሩን ጊዜ መታዘብ ችለናል(ስለ ውሾቻቸው ሲያወሩ ፊታቸው ላይ ያለው ፈገግታ ይማርካል)
ስለዚህ በሞያችን ውስጥ ንቁ እና ደስተኛ ብሎም አርአያ የሚሆን ባለሞያ እንዲኖር። መጪው ትውልድ ከተቀዳሚ ምርጫዎቹ መካከል የእንስሳት ጤና ዘርፍ እንዲኖር የሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት ቢሰጥባቸው እላለሁ።
-የእንስሳት ጤና ባለሞያው በይበልጥ የሚሻሻልበት እና ዘርፉ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ ቢሆን
-በግል ሴክተር ውስጥ ጠንካራ ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉ የእንስሳት ጤና ዘርፍ ምሩቃንን ማፍራት
-በእያንዳንዱ ወረዳ የሚገኝ የእንስሳት ሀኪምና ባለሞያ የደሞዝ እና ደረጃ እድገት ቢሻሻል
-ጥሩ ስነ ምግባር እና ሞያ አክባሪነት ያለው አርአያ መሆን የሚችል ማፍራት።
እኚህን ጉዳዮች ትኩረት አድርጎ መሥራት የእንስሳት ጤና ዘርፍ ለሚመጣው ትውልድ በልበሙሉነት የሚመርጠው ሞያ እንዲሆን ማድረግ እንደሚችል ልባዊ እምነቴ ነው።
ያሬድ ኤርሚያስ
3rd year DVM student, AAU-OHC Founder and secretary, Membership director of Rotaract club of Kuriftu.
#HaSab@Hasab_2016 · Post #4 · 2023/09/10 19:47
#HaSab
#Veteducation
ለ12ተኞች አድርሱልኝ🙏
በቅድምያ ሀገራችን ያለችበት ነባራዊ ሁኔታ በትምህርታችሁ ላይ ያደረሰውን ጫና ተቋቅማችሁ የሚያስደንቅ ውጤት በጥረታችሁ ላመጣችሁ ተማሪዎች አድናቆት እና አክብሮቴ ይድረስ።(በናንተ የወደፊቷን ኢትዮጵያ መልካም እንድትሆን እመኛለሁ)
በተለይ ባለፉት ሦስት እና አራት አመታት ውስጥ የ12ተኛ ክፍል ፈተና ማለፍ አይደለም መፈተን በራሱ ብዙ ችግሮች ያሉበት ነው።(እንክርዳድ የበዛበት እህል ሆኗል)። በርግጠኝነት ቀለሜ ሆነው ዝግጅት በማድረግ ላይ ሳሉ በተደረጉ ብርታትንና ሞራልን የሚያደክሙ ውሳኔዎች የተሰበሩ ውጤታቸው እንደምኞታቸው ያልሆነላቸው የነገ ሀገር ተስፋዎች ይኖራሉ(እናንት ጠንካሮች ሆይ ተነሱ አቧራችሁን አራግፋችሁ ለእንደገና ሩጫ ራሳችሁን ኣበርቱ)
EUEE እንደ ድሮው ኣይደለም።ጭራሽ ምንም ዝግጅት ሳያደርጉ ትምህርት ሚንስቴር አይቶ አይኔን ግንባር ያድርገው አላየሁም እያለ እልል ብለው በተሰረቁ ፈተናዎች ያለፉ ተማሪዎች እንዳሉ ሀቅ ነው። ለእነዚህም ሆነ ለሌሎች ተማሪዎች ንቁ! ዩኒቨርስቲ በተለይ የመጀመርያ አመት የመጀመርያ ሴሚስተር የሚከተለው ነው የሚል እንዳለፈበት ተማሪ መጠነኛ ሀሳቤ ይድረስ....
ውጤታችሁን እንደመመልከታችሁ ከወዲሁ ለሚጠብቃችሁ ኮርስ በትበት ብትሉ አሪፍ ነው። የፍሬሽ ማን ኮርሶች ከጥቂቶቹ በቀር ከ11 እና 12ተኛ ክፍል ትምህርት ጋር ያው ናቸው።(ለfinal exterme series መጽሐፍትን ነው ያነበብነው)። ችግሩ ያካልቧችኋል። አርፍዳችሁ እንደመግባታችሁ የምትማሩት ለመጨረስ እንጂ ለመረዳትም አይመስልም...ቀድማችሁ ዝግጅት አድርጋችሁ ብትገቡ ግን ቀለል ይልላችኋል። ጫናውን አሁን ባላችሁ ትርፍ ግዜ ትቀንሱታላችሁ።(እንዲያ አድርገው የገቡ ተማሪዎች በብዙ ነበር ያተረፉት)። የትምህርት መርጃ መጽሐፍት እና ስለ ኮርሶች ያለውን ሁሉMuja MercuryyyATC tube ላይ አስቀምጦላችኋል(ይመችህ ኣባቴ)
ሁሉም ነገር ግዚያችንን ይፈልጋል። ሁሉም ቢተገብርቱት ጥሩ ትሩፋት ኣለው። በተለይ አስታውሳለሁ ዩኒቨርሲቲ ስገባ ኣደርጋቸዋለሁ የምላቸው መልካም ነገሮች ሁሉ ግርርር ብለው መጥተውብኝ የቱን ላስቀድም የሚለው ነገር በጣም ግራ ኣጋብቶኝ ነበር። የፍሬሽ ማን ኮርስ ደግሞ ግዜ አይሰጥም። ቀጣይ የምትመርጡት ፊልድ አሁን ባመጣችሁት ውጤት እና በመጀመርያ ሴሚስተር ባመጣችሁት(ለአንዳንዱ ሙሉ የመጀመርያ አመት) ውጤት ላይ የተመሠረተ ነው። ታድያ ግዜያችሁን በይበልጥ የነገ ጉዟችሁን በሚወስነው ችከላ ላይ ማድረግ ሸግዬ ነው(ያራድዬ ልጅ የሚያደርገው እንደዛ ነው)
ዩኒቨርሲቲ ከመግባታችሁ በፊት ስለ ግቢዎች ወይም ፊልድ ከመምረጣችሁ በፊት ስለ ፊልዶች የሚነዙ ቀልዶች እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎቹ ሰዎች እንደሚሉት አይደለም። በጭፍን የምትጠሏቸውን ግቢዎች እና ፊልዶች አጢኗቸው። ለተራ ቀልዶች እጅ አትስጡ። በተለይ እንደግል ያለኝ ምክር የፊልድ መረጣችሁ በፍላጎትና ችሎታችሁ ይሁን የሚል ነው(ሸግዬ ውጤት ካላችሁ የፈለጋችሁበት መግባት ኣያሳስብም) "ያበላል?" የሚለው ጥያቄ interest በሌላችሁ ፊልድ ላይ እንደመግብያ ሰበብ ባትጠቀሙ መልካም ነው። ምክንያቱም የሚያጠግብ እንጀራ ለመብላት መጀመርያ እንጀራ መውደድ ያሻል!!
Lets talk vet!💙
Veterinary medicine በሀገራችን ባሉ በአስራ የሚቆጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል። እውነት ለመናገር DVM እንደደረሰኝ ባወኩ ግዜ እጅግ ትልቅ ሀዘን እና ተስፋ መቁረጥ ነበር የተሰማኝ። የደረሰኝን የሰሙ ሁሉ ፊታቸው ጨፍጋጋ ነበር(ከጥቂቶቹ በቀር)። ገብቼ ልየው ካልሆነ እቀይራለሁ በሚል መንፈስ ነበር የገባሁት። ነገር ግን ጥቂት እንደተማርኩ የገባኝ እጅግ ድንቅ ሳይንስ(የልብ የሚያደርስ) እና ሰፊ የስራ መስክ ያለው ሞያ መሆኑን ነው። ከምነግራችሁ በላይ አድማሰ ሰፊ ነው። እንደኔ ለህክምና ሞያ ጥልቅ ፍቅርና ጉጉት ያላችሁ ተማሪዎች ስለ እንስሳት ህክምናም ብታስቡና በቂ ጥናት ብታደርጉ ባይ ነኝ። ለሀገርም ለራስም የሚበጅ ነገር በዚህ አለ(እስቲ The Blue Vetን ሾፍ አድርጓት)
በቀረውስ ያሰባችሁት የሚሰምርበት የትምህርት ዘመን ከፊታችሁ እንዲመጣ እመኛለሁ። ሀገራችን ሰላም ሁና ሁሉም ወጣት የሚመኘው እየተማረ እንዲኖር ምኞቴ ነው። መልካም እድል!
ሻሎም!
Yared Ermiyas
Second year student, AAU-CVMA (DVM)
Vet Heart🩺@vetheart2021 · Post #3111 · 2025/01/10 04:29
💥 Transform Your Veterinary Practice! 💥
🩺 Join the Two-Day International Workshop on Fracture and Wound Management in Livestock hosted by EMRI-GHS and University of Wisconsin, Madison, USA.
📅 Date: [05-06 Feb 2025]
📍 Location: [EMRI-GHS Campus Ahmedabad]
💼 Registration Fees:
₹20,000 with accomodation/ ₹17000 without accomodation
👩⚕️ Why Attend?
✔ Learn cutting-edge techniques in fracture and wound management.
✔ Gain hands-on training from international experts.
✔ Receive a prestigious certificate of completion.
✔ Expand your professional network with veterinarians across India.
🔗 Limited Seats Available! Register Now: [Registration Link is in brochure as QR code]
Don’t miss this opportunity to take your veterinary career to the next level!
#VeterinaryWorkshop#LivestockCare#VetEducation#InternationalTraining