TGINSIGHT CHAT
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
@ebcnewsnow
News and mediaEBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1 @ETVkidschannel @EBCWORLD1 @etventertainment1
Recente posts
Tag: #unity · 3 posts
Geplaatst 10 apr
የኢትዮጵያና የቡሩንዲ ወንድማማችነት ስጦታ በአዲስ አበባ ***************** የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኤቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ በኢትዮጵያ የነበራቸው ቆይታ በምስል:- #Ethiopia#Burundi#Diplomacy#Africa#Unity
Geplaatst 29 jan
ለሀገራት ዕድገት መሠረት የሆነው አሰባሳቢ ትርክት *************** ኢትዮጵያውያን ከልዩነቶቻቸው ይልቅ አያሌ የጋራ ድሎች፣ ታሪኮችና እሴቶች ቢኖሯቸውም፤ አንድነታቸውን የሚያጠናክር የጋራ ብሔራዊ ትርክት ግን በሚገባው ልክ አልፈጠሩም። ለሺህ ዓመታት የዘለቀ የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት የሆኑት ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት አለመፍጠራቸው፣ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የመገንባት ሂደት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር ቆይቷል። የወል ትርክት ለአንድ ሀገር ሕዝብ የመዳረሻ አቅጣጫ መጠቆሚያ፣ የጋራ ማንነት መገለጫ እና ሀገራዊ መታወቂያ መሆኑን የሚናገሩት የማኅበረሰብ ልማት እና የተቋማት ሕክምና ልዩ ባለሙያው አቶ ዘላለም ይትባረክ፤ የህዝቦችን አብሮነት ለማጽናትም ትልቅ መሳሪያ ነው ይላሉ። ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ከጋራ እሴቶች ይልቅ በልዩነቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ መሠራቱ ሀገሪቱን ለማይገባ የእርስ በርስ ግጭት እና አለመግባባት ዳርጓታል ያሉት አቶ ዘላለም፤ ይህን ክፍተት ለመሙላት አሰባሳቢ ትርክት ላይ መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል። ይህ ትርክት እንደ አዲስ የሚፈጠር ሳይሆን፤ ካለፈው በጎ ታሪካችን፣ ከእንግዳ ተቀባይነታችን እና ከድል አድራጊነት ታሪካችን ተወስዶ፣ ዛሬ ካለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ተቀምሮ የሚሰናዳ መሆኑንም ጠቁመዋል። ያደጉ ሀገራት ሁሉ ወደ ዕድገታቸው የሄዱበት መንገድ የተቃኘው በገነቡት ትርክት ነው ያሉት ባለሙያው፤ ትርክት ለአንድ ሕዝብ በእርግጥም ለጋራ ግብ መግባቢያ፣ መተሳሰሪያ እና መወከያም ጭምር መሆኑን ገልጸዋል። ትርክት በሕዝቦች መካከል ያለውን ልዩነት እንደ ውበት ተጠቅሞ የወደፊት የጋራ ራዕይን መፍጠር እንደሆነም ተናግረዋል። ግለሰባዊ ዕድገት ለማኅበረሰብ ልማት መሠረት እንደሆነ ሁሉ፣ በትርክት የተቃኘ ጠንካራ ሕዝብ ደግሞ ለጠንካራ መንግሥት ግንባታ ዋስትና መሆኑን ገልጸዋል። ገዢ ሀገራዊ ትርክት መፍጠር መቻል በወደፊት የለውጥ ጉዟችን መንገራገጭ ሲያጋጥመን እርስ በርስ በመደጋገፍ፣ እንደ ሀገር ተሰናስለን አብረን መቆም የምንችልበትን አቅም ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አለውም ብለዋል። በአሁኑ ወቅት እየተደረጉ ያሉ የሀገራዊ ምክክር እና የጋራ ትርክት ግንባታ ጥረቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል እያደረገው ያለውን ተሳትፎ እንዲያጠናክርም አቶ ዘላለም ጠይቀዋል። በላሉ ኢታላ #EBC#EBCDotstream#Ethiopia#Unity#ኅብረ_ብሔራዊት_ኢትዮጵያ
Geplaatst 21 jan
ሀገራዊ ምክክር፤ ለነገዋ ኢትዮጵያ አዲስ የሰላም መንገድ! 🇪🇹 *********** ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት፤ ታሪካችንም እንደዛው። ሆኖም በታሪካችን ውስጥ የተፈጠሩ ስብራቶች፣ በትርክቶቻችን መካከል ያሉ ልዩነቶች እና ለዘመናት የዘለቁ የፖለቲካ አለመግባባቶች ዛሬም ድረስ ፈተና ሆነው ቀጥለዋል። ሀገራዊ ምክክር ለምን አስፈለገ? ጥላቻን በውይይት፣ ጥርጣሬን በመተማመን፣ እና ጠመንጃን በሐሳብ ለመተካት የታለመ ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው። ይህ ምክክር የጥቂት ሰዎች ድርድር ሳይሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁሉም ያለልዩነት የሚሳተፉበት የኢትዮጵያውያን መድረክ ነው። ኢትዮጵያ እንደ አንድ ትልቅ ቤት ናት። ቤቱ ሲጠብበን፣ ግድግዳው ሲሰነጠቅ እና ጣራው ሲያፈስ፣ መፍትሔው ቤቱን ማፍረስ ሳይሆን በጋራ ተቀምጦ መጠገን ነው። ሀገራዊ ምክክሩ ይህንን ታሪካዊ እድል ይዞልን መጥቷል። ኢትዮጵያዊነት ማለት የአንድ ቀለም ድምር ሳይሆን የብዙ ቀለማት ውህደት ነው። በምክክሩ ወቅት የምናቀርበው የተለየ ሐሳብ ሀገራችንን የተሟላች ያደርጋታል። ዛሬ ተነጋግረን የማንፈታው ችግር ለልጆቻችን የቤት ስራ ሆኖ ይተርፍብናል። ይህ ምክክር ቂምን ለመቅበርና ይቅርታን ለመዝራት የቀረበ ታላቅ እድል ነው። ከምክክሩ ምን ይጠበቃል? ✅ የጋራ መግባባት፦ በሚያቃቅሩን ታሪካዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራራቢ ሐሳብ መያዝ። ✅ ጠንካራ ተቋማት፦ ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ሀገራዊ ተቋማትን መገንባት። ✅ ዘላቂ ሰላም፦ ለግጭት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን ከስራቸው ነቅሎ መፍትሔ ማስቀመጥ። የእኛ ድርሻ ምንድነው? የምክክር ሂደቱ ውጤታማ የሚሆነው ሁላችንም በቅን ልቦና ስንሳተፍበት ነው። ልዩነቶቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ አቅርበን፣ ለልጆቻችን የምትመችና የተረጋጋች ሀገር ለማሳደር የሁላችንም ባለቤትነት እና ተሳትፎ ያስፈልጋል። ልዩነቶቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ አምጥተን፣ በንግግር አሸንፈን፣ የምትከበር ሀገርን ለልጆቻችን እናውርስ። በምክክሩ ላይ እንሳተፍ!! ንግግር የሰላም መንገድ ነው! መነጋገር ያሸንፋል! 🤝 #ኢትዮጵያ#ሀገራዊምክክር#ሰላም#NationalDialogue#Ethiopia#Unity