TGINSIGHT CHAT
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
@ebcnewsnow
News and mediaEBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1 @ETVkidschannel @EBCWORLD1 @etventertainment1
Recente posts
Tag: #africa · 8 posts
Geplaatst 16 apr
አይ ኤምኤፍ የ2026 የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያውን ይፋ አደረገ፤ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ዕድገት ቀዳሚነቱን ይዛለች ************************** ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በአውሮፓውያኑ 2026 የሰሃራ በታች አፍሪካ ሀገራትን የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ ይፋ አድርጓል። በዚህ ትንበያ መሠረት ኢትዮጵያ በ9.2 በመቶ ከፍተኛ ዕድገት በማስመዝገብ ከቀጣናው ሀገራት ቀዳሚነቱን እንደምትይዝ ተመልክቷል። እንደ አይኤምኤፍ ሪፖርት፣ ኡጋንዳ በ7.5 በመቶ፣ ሩዋንዳ በ7.2 በመቶ እንዲሁም ቤኒን በ7.0 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግቡ ተተንብዮላቸዋል። በሌላ በኩል እንደ ናይጄሪያ (4.1 በመቶ) እና ደቡብ አፍሪካ (1.0 በመቶ) ያሉ የክፍለ አህጉሩ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች ዝቅተኛ የዕድገት ትንበያ ተቀምጦላቸዋል። በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት የነዳጅ እና የማዳበሪያ ዋጋን በመጨመር በበርካታ ሀገራት ላይ የኢኮኖሚ ጫና ቢፈጥርም፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት ግን አሁንም ጠንካራ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንደሚያሳዩ የአይኤምኤፍ ትንበያ ያመላክታል። #IMF#EconomicProjections#Africa#Ethiopia#GDPGrowth#EBC
Geplaatst 16 apr
የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀምን፣ አስፈላጊውን የሕግ ማዕቀፍ በማበጀት፣ በአግባቡ መምራት ይገባል - ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ********************** የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የመሩት የአፍሪካ ህብረት ሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት የሚኒስትሮች ስብሰባ በበይነ መረብ ተካሂዷል። ውይይቱ “ሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ አስተዳደር፣ ሰላም እና ጸጥታ በአፍሪካ'' በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው። ስብሰባው በኢትዮጵያ የወሩ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበርነት ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ ነው። የስብሰባው መሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በመክፈቻ ንግግራቸው፥ ሰው ሰራሽ አስተውሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአስተዳደር፣ የኢኮኖሚ ልማት እና ደኀንነት ጉዳዮችን በፍጥነት እየለወጠ መሆኑን ገልጸዋል። መንግሥታት እና ተቋማት በውሳኔ አሰጣጥ፣ በሕዝብ አስተዳደር፣ በደኀንነት ሥርዓት እና በኢኮኖሚ ዕቅዳቸው ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተቀናጀ መንገድ የመጠቀም ሁኔታቸው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን አንስተዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት በአፍሪካ መልካም ዕድሎችን እና ስጋቶችን ጭምር ይዞ መምጣቱንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ዶ/ር ጌዲዮን በንግግራቸው፥ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በአግባቡ በመጠቀም የሚገኙ ትሩፋቶችንም አብራርተዋል። ግጭትን አስቀድሞ ለመከላከል የሚሠሩ ሥራዎችን በማጠናከር፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራዎችን በመተግበር፣ የሽምግልና ጥረቶችን በመደገፍ እና በአጠቃላይ በአህጉሪቱ የአስተዳደር ሥርዓቶችን በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው ዘርዝረዋል። በሌላ በኩል የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም በአግባቡ ካልተመራ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማስፋፋት እና የሳይበር ወንጀሎችን በማበራከት ለሽብርተኛ ድርጅቶች እና ተባባሪዎቻቸው ጥቅም ሊውል እንደሚችል ጠቁመዋል። በመሆኑም ለዘርፉ አስፈላጊውን የሕግ ማዕቀፍ ማበጀት እና ማጠናከር እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል። #Ethiopia#MFA#Africa#AU#ArtificialIntelligence#AI#EBC
Geplaatst 10 apr
የኢትዮጵያና የቡሩንዲ ወንድማማችነት ስጦታ በአዲስ አበባ ***************** የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኤቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ በኢትዮጵያ የነበራቸው ቆይታ በምስል:- #Ethiopia#Burundi#Diplomacy#Africa#Unity
Geplaatst 4 mrt
ከአሰብ ደጃፍ ላይ ሆነው የባሕር በር የሚናፍቁት የሱልጣን አሊ ሚራህ ልጆች ************ አፋሮች ከአባቶቻቸው የወረሱትን ኢትዮጵያዊነትና የቀይ ባሕር ባለቤትነት መንፈስ ይዘው፣ በሴራ ያጣነውን የባሕር በር በሰለጠነ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማስመለስ በጽናት እንደሚታገሉ አስታወቁ። የአፋር ህዝብ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ትስስር ጥንታዊና የማይበጠስ መሆኑን የገለጹት የኤሊ ዳአር ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች፣ የቀይ ባሕር በር ለሀገር ህልውና ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። የሀገር ሽማግሌ አቶ መሐመድ አብደላ ከኤሊ ዳአር ወረዳ፣ "አፋርነት ከኢትዮጵያዊነት ጋር የተገመደ የጥንት ማንነት ነው። ሱልጣን አሊ ሚራህ አንፈሬ 'አፋር አፋር ነው፤ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ግመሎቹም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ለይተው ያውቃሉ' ሲሉ የገለጹት ይኸው የማይበጠስ ትስስር ነው። ሱልጣኑ ኢትዮጵያ የባሕር በሯን እንዳታጣ የከፈሉት ታላቅ መስዋዕትነት ዛሬም በትውልዱ ልብ ውስጥ ህያው ሆኖ ጥያቄው ሳይበርድ ይኖራል ብለዋል የወረዳው ነዋሪዎች። ዛሬም ከአሰብ ደጅ ከኤሊ ዳአር ሆነን የምናውጀው አንድ እውነት አለ፤ ቀይ ባሕር ታሪካዊ አካል የሁላችንም ኩራት ነው በማለት ተናግረዋል፡፡ አፋር ያለ ኢትዮጵያ አይኖርም። ቀይ ባሕር የኛ ነው፣ እኛ የኢትዮጵያ ነን።" በማለት የአፋርን የማይነጣጠል የኢትዮጵያዊነት ትስስር ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የባሕር በርን ለማስመለስ ለምታደርገው ዲፕሎማሲያዊ ትግል የአፋር ህዝብ እንደሚደግፍ እና ለውጤት እንዲበቃ እንደሚሰራም አቶ መሐመድ አብደላ አረጋግጠዋል። በላሉ ኢታላ #Ethiopia#RedSea#HistoricalRight#Geopolitics#MaritimeLaw#NationalInterest#Africa
Geplaatst 17 feb
ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ - ለግማሽ ሚሌኒየም የዘለቀ ወዳጅነት *********************** ታውቃላችሁ? የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ ግንኙነት የትናንት ሳይሆን የግማሽ ሚሌኒየም ታሪክ ውጤት ነው። ከቀይ ባሕር ዳርቻ እስከ ዓባይ ተፋሰስ የዘለቀው ይህ ዕድሜ ጠገብ ወዳጅነት፣ በታሪክ አጋጣሚዎች ሳይገታ ዛሬም በጽኑ መሠረት ላይ ይገኛል። የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በ16ኛው ክፍለ ዘመን በኦቶማን ኢምፓየር ዘመን የጀመረ ረጅም ታሪክ ያለው ሲሆን፣ በ1912 ዓ.ም በሐረር ከተማ የመጀመሪያው የቆንስላ ጽሕፈት ቤት መከፈቱ ለዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ ትልቅ ምዕራፍ ሆኗል። ይህ ግንኙነት በንግድ እና በዲፕሎማሲ ብቻ ሳይወሰን በባህል እና በሃይማኖት ትሥሥር ጭምር የጎለበተ ነው። ዛሬ ላይ ቱርክዬ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ቀዳሚ የውጭ ኢንቨስተሮች አንዷ ስትሆን፣ በተለይም በጨርቃጨርቅ፣ በግንባታ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የሚታየው ትብብር ለሺዎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል። በተጨማሪም የቱርክዬ አየር መንገድ (Turkish Airlines) እና የልማት ድርጅቱ (TIKA) የሁለቱን ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ይበልጥ በማቀራረብ ረገድ እንደ ድልድይ እያገለገሉ ይገኛሉ። "ወዳጅነት እንደ ወይን ጠጅ ነው፤ በቆየ ቁጥር ይጣፍጣል" እንደሚባለው ሁሉ፣ የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ ግንኙነትም በዘመናት ፈተና ውስጥ አልፎ ዛሬ ላይ ለቀጣናዊ ሰላም እና ብልጽግና ዋስትና ሆኗል። ይህ ለ500 ዓመታት የዘለቀ ወዳጅነት፣ ለቀጣዩ ትውልድ በጋራ የማደግ እና የመበልጸግ ትልቅ አርአያ ሆኖ ይቀጥላል። #Ethiopia#Turkiye#History#Friendship#Diplomacy#Africa#Europe
Geplaatst 12 feb
ኢትዮጵያ በአፍሪካና በጣሊያን መካከል የትብብር ድልድይ ****************** ኢትዮጵያ በመደመር መንፈስ 2ኛውን የጣሊያን-አፍሪካ ጉባዔ የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ታስተናግዳለች:: እንኳን ደህና መጣችሁ! #Ethiopia#Africa#Italy#AfricaItalySummit#PMOEthiopia#Medemer
Geplaatst 28 jan
የቀድሞው የአርሰናል ኮከብ ኢቢሲን ጎበኘ ************** የቀድሞው የአርሰናል የቀኝ ተከላካይ ባካሪ ሳኛ ዛሬ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን (ኢቢሲ) ጎብኝቷል። ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ቆይታ እያደረገ የሚገኘው ፈረንሳዊው ኮከብ በኢቢሲ ዋናው መስሪያ ቤት በመገኘት ዘመናዊውን የኢቢሲ የቴሌቪዥንን እና የሬዲዮ ስቱዲዮዎች ጎብኝቷል። ኢቢሲ ባሉት ዘመናዊ ስቱዲዮዎች መገረሙን የተናገረው የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ተቋሙ ያለበት ቦታ ፍጹም ደስ የሚል መሆኑንም ገልጿል። ባካሪ ሳኛ በኢትዮጵያ ያለውን ቆይታ እና የእግር ኳስ ህይወቱን በተመለከተ ከኢቢሲ ጋር ያደረገውን ቆይታ በቀጣይ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል። በአንተነህ ሲሳይ #EthiopianBroadcastingCorporation#Bacary_Sagna#africa#Arsenal
Geplaatst 23 jan
የጥቁር አንበሳው ክንፍ በሰማዩ ላይ ነግሶ አምሽቷል - የ90 ዓመታት የክብር ጉዞ! 🔥 ************************** የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ምሽት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እጅግ ዘመናዊ እና አስደናቂ የድሮን ትርዒት ቀርቧል። በልዩ ትርዒቱ የተሳተፉት በሺዎች የሚቆጠሩ ድሮኖች በቢሾፍቱ የኢትዮጵያን ሰማይ በተለያዩ መልዕክት አዘል ቀለሞች እና ቅርጾች ሲያደምቁት አምሽተዋል። በዚህም የአየር ኃይሉ የ90 ዓመታት የጀግንነት ጉዞ እና የዘመናዊነት ሽግግር በብርሃን ትርዒት ለዓለም ታይቷል። ታዳሚዎችን በእጅጉ ያስደመመው ትርዒት የአየር ኃይላችንን የጥንካሬ እና የኩራት ተምሳሌትነት ዳግም አረጋግጧል። ሁነቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ራሱን በዘመናዊ ትጥቅ እና በሰው አልባ አውሮፕላኖች በማደርጀት የአፍሪካ የኩራት ተምሳሌት መሆኑን ለዓለም ያረጋገጠበት አጋጣሚ ሆኖ አልፏል። #EBCDotstream#Ethiopia#AirForce#90thanniversary#airshow#Africa