TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
Terug naar kanalen
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar

TGINSIGHT CHAT

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow

News and media

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1 @ETVkidschannel @EBCWORLD1 @etventertainment1

Abonnees13.5万Huidige kanaalabonnees
Gevolgde posts1,008Geïndexeerde posts
Recent bereik24,480Som van recente weergaven
Recente posts

Recente posts

Tag: #africarising · 3 posts

当前筛选 #africarising清除筛选

የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የሉዓላዊነት ጉዞና የብሪክስ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ ************** ኢትዮጵያ ከውስጥ ግንባታ እስከ ዓለም አቀፍ መሪነት የምታደርገው የሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ጉዞ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እየከፈተ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየታየ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማና የገጠር ትስስርን በማጠናከር የዜጎችን የኑሮ ዘይቤ ከመቀየሩ ባለፈ የ"መደመር" ፍልስፍናን በተግባር እያሳየ የሚገኝ ስኬት ነው፡፡ በጤናው ዘርፍም በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አማካኝነት የተጀመረው የሀገር ውስጥ መድኃኒት ምርት የውጭ ጥገኝነትን በመቀነስ ረገድ ትልቅ ተስፋ ሆኗል፡፡ በዲፕሎማሲው ረገድ ኢትዮጵያ የብሪክስ+ አባል መሆኗ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት ከማሳደጉም በላይ የባሕር በር ጥያቄዋንና የንግድ ጥቅሟን ለማስከበር ትልቅ ስትራቴጂካዊ አቅም ፈጥሮላታል፡፡ ይህ ሁሉ የብልፅግና ሰንሰለት ዘላቂ የሚሆነው በሰለጠነ የፖለቲካ ተሳትፎና በዴሞክራሲያዊ ግንባታ በመሆኑ፣ እየተቃረበ ለሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ካርድ በመውሰድ በሐሳብ ውድድር ላይ የተመሰረተች ሀገርን ለመገንባት የሁላችንም ሉዓላዊ መብትና ኃላፊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ በጀመረችው ሁለንተናዊ ንቅናቄ ወደ ተሟላ ሉዓላዊነትና ብልፅግና እያመራች በመሆኗ በዚህ ታሪካዊ ጉዞ ላይ ሁላችንም አሻራችንን እናሳርፍ፡፡ ሙሉ ትንታኔውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://www.ebc.et/Home/NewsDetails?NewsId=4831 በሰለሞን ገዳ #Ethiopia#Sovereignty#BRICSPlus#EconomicGrowth#Medemer#Development#AfricaRising

5,720 views

📍 "የነገዋ አፍሪካ ብርሃን፦" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ የንጹህ ኃይል መሠረት መጣሉን ተናገሩ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ የ"አፍሪካ ዘመን" እንዲሆን ዛሬውኑ ጠንካራ መሠረት መጣል እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳሰቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፍሪካን ወደ ላቀ ዕድገት የሚያሻግሩ ሁለት ቁልፍ ምሰሶዎችን ጠቁመዋል፦ 🔹 ብቁ ትውልድ መገንባት፦ በሕፃናት ትምህርት ላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ነገን የሚረከብ ብቁ ዜጋ ማዘጋጀት። 🔹 ከተፈጥሮ ጋር የተስማማ ልማት፦ አካባቢን የማይበክልና ለቀጣይ ትውልድ የሚተርፍ የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ግንባታን ማፋጠን። ቁልፍ ነጥቦች፦ ✅ የንጹህ ኃይል ስጦታ፦ ኢትዮጵያ ለቀጣዩ የአፍሪካ ዕድገት የምታበረክተው ትልቁ ስጦታ ከውኃ፣ ከንፋስና ከጂኦተርማል የሚመነጭ ታዳሽ ኃይል መሆኑ ተገልጿል። ✅ የሕዳሴው ግድብ ፋይዳ፦ "የሕዳሴ ግድብ አፍሪካውያን ከተደመሩ አንጋፋ ሥራዎችን ጀምረው መጨረስ እንደሚችሉ ያሳየን የምሳሌነት ምልክት ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ። ✅ አረንጓዴ ዕድገት፦ ካለፈው ክፍለ ዘመን በተቃራኒ፣ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጉዞ ተፈጥሮን የማይበክልና አህጉራዊ ትስስርን የሚያጠናክር እንደሆነ ተረጋግጧል። ኢትዮጵያ ዛሬ የምትጥለው መሠረት ለነገዋ አፍሪካ የብልፅግና ጮራ እና የታዳሽ ኃይል ማዕከልነቷ ዋስትና መሆኑ ተመላክቷል። #Ethiopia#LightOfAfrica#CleanEnergy#GreenDevelopment#GERD#AfricaRising#ኢትዮጵያ

9,140 views

"ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ የዓለምን አካሄድ የቀየረችበት ድንቅ ታሪክ ነው" - ትሬቨር ኖዋህ *************** ቀደም ሲል የDaily Show አሁን ደግሞ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን የሚዳስስ ፖድካስት የሚያዘጋጀው አፍሪካ አሜሪካዊው ትሬቨር ኖዋህ፣ ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር ልዩ ቆይታ አድርጓል። በቆይታቸው ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያነሣው ሐሳብ እሱ ግድቡን የተረዳበት መጠን ከፍተኛ እንደሆነ አመላክቷል። ትሬቨር ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሰጠው አድናቆት እና የውይይቱ ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦ ራስን የመቻል አብዮት ትሬቨር በውይይቱ ላይ እጅግ ያስገረመው ነጥብ ኢትዮጵያ ግድቡን የገነባችበት መንገድ መሆኑን ገልጿል። ዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ፊታቸውን ባዞሩበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ የራሷን አቅም በመጠቀም እና እያንዳንዱ ዜጋ ካለው ላይ ቀንሶ በሰጠው መዋጮ ቢሊዮን ዶላሮችን ማሰባሰቧን "አብዮታዊ" ሲል ገልጾታል። ይህ ለሌሎች አዳጊ ሀገራት "ያለ ውጭ ብድር ታላቅ መሆን ይቻላል" የሚል ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን ጠቁሟል። [የ130] ሚሊዮን ሕዝብ ተስፋ ትሬቨር አክሎም፣ ይህ ግድብ ለኢትዮጵያ ዝም ብሎ ግንባታ ሳይሆን፣ [ከ130] ሚሊዮን በላይ ለሚሆነው ሕዝብ በተለይም ኤሌክትሪክ ለማያገኘው ከግማሽ በላይ ወገን፣ መሠረታዊ የለውጥ ምንጭ መሆኑን ገልጿል። ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሽግግር እያደረገች ያለችው አካባቢን በማይበክል ንፁህና ታዳሽ ኃይል መሆኑም ልዩ እንደሚያደርገው አንሥቷል። የ21ኛው ክፍለ ዘመን ዓድዋ የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ በበኩላቸው፣ በጉዳዩ ላይ ከትሬቨር ኖዋህ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፣ ግድቡን በታሪክ ትልቅ ቦታ ካለው ከ1888ቱ የዓድዋ ድል ጋር አነፃፅረውታል። ኢትዮጵያውያን ወራሪውን የፋሺስት ጦር ድል አድርገው ለአፍሪካ የነፃነት ፋና እንደሆኑት ሁሉ፣ ዛሬም ይህን ግዙፍ ግድብ በራሳቸው አቅም ገንብተው በማጠናቀቅ "የዘመኑን የዓድዋ ድል" አስመዝግበዋል ሲሉ ገልጸውታል። የራስን ወንበር ይዞ መምጣት ሁለቱም ሰዎች ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ያመጣችውን አብዮት የገለጹት፣ "ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በጠረጴዛው ዙሪያ ወንበር ካልሰጠህ፣ የራስህን የሚታጠፍ ወንበር (Folding Chair) ይዘህ መምጣት አለብህ" በማለት ነው። ኢትዮጵያ የዓለም የገንዘብ ሥርዓት ወንበር ቢነፍጋትም፣ በራሷ ጥረት የራሷን ወንበር ይዛ በዓለም መድረክ ላይ በኩራት መቀመጧን ትሬቨር ኖዋህም ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ በሚገባ መስክረዋል። በለሚ ታደሰ #EBC#ebcdotstream#GERD#TrevorNoah#MiaMottley#Adwa#AfricaRising

9,620 views