TGINSIGHT CHAT
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
@ebcnewsnow
News and mediaEBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1 @ETVkidschannel @EBCWORLD1 @etventertainment1
Recente posts
Tag: #sovereignty · 4 posts
Geplaatst 19 apr
የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የሉዓላዊነት ጉዞና የብሪክስ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ ************** ኢትዮጵያ ከውስጥ ግንባታ እስከ ዓለም አቀፍ መሪነት የምታደርገው የሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ጉዞ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እየከፈተ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየታየ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማና የገጠር ትስስርን በማጠናከር የዜጎችን የኑሮ ዘይቤ ከመቀየሩ ባለፈ የ"መደመር" ፍልስፍናን በተግባር እያሳየ የሚገኝ ስኬት ነው፡፡ በጤናው ዘርፍም በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አማካኝነት የተጀመረው የሀገር ውስጥ መድኃኒት ምርት የውጭ ጥገኝነትን በመቀነስ ረገድ ትልቅ ተስፋ ሆኗል፡፡ በዲፕሎማሲው ረገድ ኢትዮጵያ የብሪክስ+ አባል መሆኗ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት ከማሳደጉም በላይ የባሕር በር ጥያቄዋንና የንግድ ጥቅሟን ለማስከበር ትልቅ ስትራቴጂካዊ አቅም ፈጥሮላታል፡፡ ይህ ሁሉ የብልፅግና ሰንሰለት ዘላቂ የሚሆነው በሰለጠነ የፖለቲካ ተሳትፎና በዴሞክራሲያዊ ግንባታ በመሆኑ፣ እየተቃረበ ለሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ካርድ በመውሰድ በሐሳብ ውድድር ላይ የተመሰረተች ሀገርን ለመገንባት የሁላችንም ሉዓላዊ መብትና ኃላፊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ በጀመረችው ሁለንተናዊ ንቅናቄ ወደ ተሟላ ሉዓላዊነትና ብልፅግና እያመራች በመሆኗ በዚህ ታሪካዊ ጉዞ ላይ ሁላችንም አሻራችንን እናሳርፍ፡፡ ሙሉ ትንታኔውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://www.ebc.et/Home/NewsDetails?NewsId=4831 በሰለሞን ገዳ #Ethiopia#Sovereignty#BRICSPlus#EconomicGrowth#Medemer#Development#AfricaRising
Geplaatst 14 apr
ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ለባሕረ ሰላጤው ሀገራት ሉዓላዊነት እና ደኅንነት ተገቢው ክብር እንዲሰጥ አሳሰቡ ************************* የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከአቡ ዳቢው አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ ጋር ባደረጉት ውይይት በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም እና መረጋጋትን ለማጠናከር የሚያስችል ባለ አራት ነጥብ የውሳኔ ሐሳብ ማቅረባቸውን ሺንዋ ዘግቧል። የውሳኔ ሐሳቡ በሰላም አብሮ መኖር፣ ብሔራዊ ሉዓላዊነት እና ዓለም አቀፍ የሕግ የበላይነት መርሆዎች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ ለደኅንነት እና የልማት ቅንጅት አስፈላጊነትም አፅንዖት ይሰጣል። ፕሬዚዳንቱ፣ “በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የባሕረ ሰላጤው ሀገራት ሉዓላዊነት፣ ደኅንነት እና የግዛት አንድነት በቅንነት ሊከበር ይገባል” ማለታቸውን የቻይና የቴሌቪዥን ጣቢያ (CCTV) ዘግቧል። #EBC#Ethiopia#middleeast#china#sovereignty#security
Geplaatst 14 apr
የሉዓላዊነት ልብ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የተደረገ ቆይታ - ክፍል 1 ዛሬ ምሽት 2:30 በኢቲቪ ዜና ቻናል እና በኢቢሲ ዶትስትሪም አማራጮቻችን ይጠብቁን! #Ethiopia#EBC#PMAbiyAhmed#sovereignty
Geplaatst 1 mrt
ትውልድ ከአያቶቹ ታሪክ በመማር ለሀገር ሉዓላዊነት የበኩሉን ሊወጣ ይገባል - አቶ ታገሰ ጫፎ ******************* ወጣቱ ትውልድ ከቀደምት አያት አባቶቹ ታሪክ በመማር ለኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡ የትናንት ጀግንነትን የሚያወሳ፣ የዛሬን ጥንካሬ የሚያሳይ እና የነገን ተስፋ የሚጠቁም የመከላከያ ሙዚየም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና በመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ተመርቆ ተከፍቷል። በምረቃው ወቅት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንደገለጹት፤ የጀግኖች አባቶችን ታሪክ የሚዘክር ሙዚየም መኖሩ ወጣቱ ትውልድ የቀደምቶችን ገድል ተረድቶ የራሱን አዲስ ታሪክ እንዲሠራ ትልቅ በር የሚከፍት ነው። ወጣቱ ትውልድ ከታሪኩ በመማር ለኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት መጠበቅ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል። የመከላከያ ቅርስ ጥናት እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ በበኩላቸው፤ ሙዚየሙ 118 ዓመታትን ያስቆጠረውን የመከላከያ ሠራዊት የጀግንነት ታሪክ ለተተኪው ትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia #DefenseMuseum#NationalDefense#History#Sovereignty