TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
Terug naar kanalen
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) avatar

TGINSIGHT CHAT

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow

News and media

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1 @ETVkidschannel @EBCWORLD1 @etventertainment1

Abonnees13.5万Huidige kanaalabonnees
Gevolgde posts1,008Geïndexeerde posts
Recent bereik56,010Som van recente weergaven
Recente posts

Recente posts

Tag: #development · 7 posts

当前筛选 #development清除筛选

የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የሉዓላዊነት ጉዞና የብሪክስ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ ************** ኢትዮጵያ ከውስጥ ግንባታ እስከ ዓለም አቀፍ መሪነት የምታደርገው የሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ጉዞ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እየከፈተ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየታየ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማና የገጠር ትስስርን በማጠናከር የዜጎችን የኑሮ ዘይቤ ከመቀየሩ ባለፈ የ"መደመር" ፍልስፍናን በተግባር እያሳየ የሚገኝ ስኬት ነው፡፡ በጤናው ዘርፍም በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አማካኝነት የተጀመረው የሀገር ውስጥ መድኃኒት ምርት የውጭ ጥገኝነትን በመቀነስ ረገድ ትልቅ ተስፋ ሆኗል፡፡ በዲፕሎማሲው ረገድ ኢትዮጵያ የብሪክስ+ አባል መሆኗ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት ከማሳደጉም በላይ የባሕር በር ጥያቄዋንና የንግድ ጥቅሟን ለማስከበር ትልቅ ስትራቴጂካዊ አቅም ፈጥሮላታል፡፡ ይህ ሁሉ የብልፅግና ሰንሰለት ዘላቂ የሚሆነው በሰለጠነ የፖለቲካ ተሳትፎና በዴሞክራሲያዊ ግንባታ በመሆኑ፣ እየተቃረበ ለሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ካርድ በመውሰድ በሐሳብ ውድድር ላይ የተመሰረተች ሀገርን ለመገንባት የሁላችንም ሉዓላዊ መብትና ኃላፊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ በጀመረችው ሁለንተናዊ ንቅናቄ ወደ ተሟላ ሉዓላዊነትና ብልፅግና እያመራች በመሆኗ በዚህ ታሪካዊ ጉዞ ላይ ሁላችንም አሻራችንን እናሳርፍ፡፡ ሙሉ ትንታኔውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://www.ebc.et/Home/NewsDetails?NewsId=4831 በሰለሞን ገዳ #Ethiopia#Sovereignty#BRICSPlus#EconomicGrowth#Medemer#Development#AfricaRising

5,720 views

የጀመርነው የብልፅግና ጉዞ በማንኛውም ዓይነት ጩኸት እንዳይናወጥ በደም መሠረት ላይ ያቆምነው ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ****************** ኢትዮጵያ የጀመረችው የብልፅግና ጉዞ በማንኛውም ዓይነት መሰናክል እንደማይቆም እና የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ምርቃት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ መንግሥት የሕዝብን ሕይወት የሚለውጡ ተግባራትን በሙሉ ልብ እና በሙሉ አቅም ማከናወኑን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ የልማት ጉዞ በብዙ ውጣ ውረድ እና መስዋዕትነት ያለፈ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "የጀመርነው የብልፅግና ጉዞ በማንኛውም ዓይነት ጩኸት እንዳይናወጥ በደም መሠረት ላይ ያቆምነው ነው" ብለዋል። በልማት ሥራው ላይ ጥርጣሬ ላላቸው አካላትም፣ "ሥራ ስንጀምር፣ ጨርሰን ሪቫን ስንቆርጥ ላላመናችሁ፤ የእኛ ፀሎት፣ ዕድሜ ይስጣችሁ፣ ደግመን ደጋግመን እናሳያችኋለን ነው" በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል። ልማቱን ሊያደናቅፍ የሚችል ማንኛውንም እንቅፋት መንግሥት ታግሶ እንደማያልፍ ያስጠነቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ "ሊያደናቅፈን የሚችል ማንኛውም እንቅፋት ካለ እንደ ማንኛውም ጉቶ ነቅለን በመጣል እናልፋለን" ብለዋል። ዓለም በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ መተራመስ ውስጥ እንደምትገኝ ጠቅሰው፣ ራሱን በምግብ፣ በኢነርጂ እና በተቋማት ግንባታ ያላደራጀ ሀገር የመበተን አደጋ እንደሚጋረጥበት ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለዚህ የሚመጥን የመከላከል አቅም እየገነባች መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ሀገርን ለመመገብ የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ የሚቀጥለው ትውልድ ለአምባገነንነት እና ለባርነት እንዳይጋለጥ የነቃ እና የተማረ ትውልድ መገንባት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። "ልጆቻችን፣ እኛ እና አባቶቻችን ባለፍንበት መከራ እንዳያልፉ፣ መሠረት ጥለን ማለፍ አለብን" በማለትም ቀጣይ የኢትዮጵያ ጉዞ ብሩህ መሆኑን አረጋግጠዋል። በለሚ ታደሰ #Ethiopia#Resilience#Development#Prosperity#AbiyAhmed

6,330 views

በትውልድ መስዋዕትነት የሚገነቡ የልማት ሥራዎች የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ የሚያረጋግጡ ናቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ********************* የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች በትውልድ መስዋዕትነት የሚገነቡና የዜጎችን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። እንደ ከተማ መልሶ ማልማትና ክላስተር እርሻ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሲከናወኑ ለጊዜው የሚታዩ ተግዳሮቶች ለረጅም ጊዜ ስኬት ሲባል የሚታለፉ መሆናቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የልማቱ ድምር ውጤት በሀገርም ሆነ በቤተሰብ ደረጃ ዕድገት እንጂ ውድቀት እንደማያመጣ አስረድተዋል። የሀገር ግንባታ በዋዛ ፈዛዛ እንደማይሳካና የበለጸጉ ሀገራት ዛሬ ለደረሱበት ደረጃ የበቁት በዜጎቻቸው "ደም እና አጥንት" መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል። የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ዋናው ዓላማ ለሕዝብና ለሀገር ብልጽግና መሥራት መሆኑን አስገንዝበዋል። አሁን የሚታዩ ችግሮች ጊዜያዊ ቢሆኑም፣ በረጅም ጊዜ ሂደት ኢትዮጵያ ስታድግ የማይጠቀም ዜጋ እንደማይኖርና እያንዳንዷ ሰከንድ የኢትዮጵያን ብልጽግና በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንደምትውል አረጋግጠዋል። በቢታኒያ ሲሳይ #EBC#Ethiopia#Development#NationalBuilding#Prosperity#PMAbiyAhmed

8,070 views

የሶርጋ ኢኮ ሎጅ ግንባታ በቅርቡ ይጠናቀቃል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ***************** የሶርጋ ኢኮ ሎጅ ግንባታ ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ ሲሆን በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በሶርጋ ሐይቅ ላይ የሚገኘው የሶርጋ ኢኮ ሎጅ በአሁኑ ወቅት በ14 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ከነቀምቴ ከተማ በ6 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ብቻ የሚገኘው የሶርጋ ኢኮ ሎጅ አካባቢውን ከመጠበቅ ባሻገር በኮንስትራክሽን እና በተለያዩ አገልግሎቶች የሥራ ዕድል እንዲፈጥር ተደርጎ የተቀረፀ መሆኑን አመላክተዋል። ፕሮጀክቱ የአካባቢውን ማኅበረሰብ በመጥቀም በክልሉ ዘላቂ ቱሪዝምን የሚያበረታታ እንደሚሆንም ገልጸዋል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#PMAbiyAhmed#SorgaEcoLodge#Tourism#Nekemte#Development

7,340 views

በወለጋ ዞኖች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች አስደሳች ናቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ************************** በወለጋ ዞኖች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ተስፋ ሰጪ እና አስደሳች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት በቄለም ወለጋ፣ በምዕራብ ወለጋ (ጊምቢ) እና በምስራቅ ወለጋ (ነቀምት) ዞኖች በመዘዋወር የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወለጋ ሕዝብ ሰላም ወዳድ፣ ሥራ ወዳድ እና በፍቅር የተሞላ መሆኑን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። "የወለጋ ሕዝብ ጠላቱ እንኳን ቢሆን ተጎድቶ እና ደክሞ ቢያይ ለመርዳት ልቡ የቀና፣ እጁ የተዘረጋ፣ ትምህርት እና ዕውቀት የሚወድ ሕዝብ ነው" ብለዋል። ባለፉት ጊዜያት ያጋጠሙ ልክ ያልሆኑ ጉዳዮች ቢኖሩም፣ አሁን ላይ ተጨባጭ የልማት ሥራዎች መጀመራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። ሕዝቡ እና አመራሩ ለሀገር ብልጽግና በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ መከፋፈልን ማስወገድ፣ ሰላምን መጠበቅ እና ልማትን ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። "ወለጋ ዛሬ የደስታ ዝናብ የሚዘንብባት ምድር ናት" በማለት፣ ይህ መልካም ጅምር እንዳይስተጓጎል ሁሉም በጋራ ለሀገር ልማት እንዲቆም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። በሀብተሚካኤል ክፍሉ #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia#PMAbiy#Wollega#Development

9,690 views

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 ዓ.ም የታህሳስ እና የጥር ወራት ዋና ዋና የሥራ ክንውኖች ************ ባለፉት ሁለት ወራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ፣ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ሀገራዊ ብልጽግናን ለማፋጠን የተከናወኑ ስትራቴጂያዊ ተግባራት፦ ግዙፍ የመሠረተ ልማት እና የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች • የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፦ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም የሚኖረው ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በይፋ ተጀምሯል። • ታዳሽ ኃይል፦ የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመርቆ ወደ ሥራ ገብቷል። • የፋይናንስ ዘርፍ፦ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሪፎርም የሚያፋጥን የ“ፋይናንስ እመርታ” ኮንፈረንስ ተካሂዷል። • የትራንስፖርት ማሻሻያ፦ በኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር፣ በደረቅ ወደቦችና በመጋዘን ግንባታዎች ላይ የዘመናዊነት ሥራዎች ተጠናክረዋል። ቱሪዝም እና ማኅበራዊ ልማት • ገበታ ለትውልድ፦ የደምቢ ኢኮ ሎጅ እና ሸበሌ ሪዞርት (በ385 ሄክታር ላይ ያረፈ) በይፋ ተመርቀው ለቱሪስቶች ክፍት ሆነዋል። • የበጎ አድራጎት መንደር፦ ለ150 ዜጎች መኖሪያ የሚሆን የቱሉ አራራ የተቀናጀ ሞዴል መንደር ተመርቋል። • ትምህርት፦ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይ የምሁራን ሚናን የተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቧል። ብሔራዊ ደህንነት እና ዲፕሎማሲ • የአየር ኃይል 90ኛ ዓመት፦ የአቪዬሽን ኤክስፖ 2026 እና “የጥቁር አንበሳ” የአየር ላይ ትርዒት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል። • ቀጣናዊ ትብብር፦ የጂቡቲ እና የሶማሊያ መሪዎችን በጅግጅጋ ተቀብሎ በማነጋገር ቀጣናዊ መረጋጋትን የማጠናከር ሥራ ተከናውኗል። • ዓለም አቀፍ ግንኙነት፦ ከቻይና እና ከዩናይትድ ኪንግደም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ኢንቨስትመንትና በኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች ላይ ስምምነቶች ተፈርመዋል። #PMOEthiopia#AbiyAhmed#Development#EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia

9,660 views

ኢትዮጵያ የቀጣዩ የአፍሪካ የብልጽግና ዘመን ፈር ቀዳጅ ለመሆን እየሠራች ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ************************* ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ምረቃ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የሚጠበቀው የአፍሪካ የብልጽግና ዘመን ቀዳሚ ምሳሌ ለመሆን በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኑን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹ 25 ዓመታት የምዕራባውያን፣ ሁለተኛው ሩብ ደግሞ የእስያ ሀገራት የዕድገት ማማ ላይ የሚደርሱበት መሆኑን ገልጸው፤ ሦስተኛው እና አራተኛው ሩብ ክፍለ ዘመን ግን የአፍሪካ ዘመን የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህን ዕድል ለመጠቀምም ኢትዮጵያ በሕፃናት ትምህርት እና በመሠረተ ልማት (መንገድ፣ ቴሌኮም እና መብራት) ላይ ትኩረት አድርጋ እየሠራች መሆኑን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ የምታስመዘግበው ዕድገት ተፈጥሮን የማይጎዳ መሆን እንዳለበት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እንዲሁም የንፋስ እና የጂኦተርማል ኃይል ልማቶች የሀገሪቱን የንጹህ ኢነርጂ ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ለአፍሪካ አርአያ መሆናቸውን ገልጸዋል። ዛሬ የተመረቀው የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫም የዚሁ አካል መሆኑን አክለዋል። "የኢትዮጵያ ዕድገት ከጎረቤት ሀገራት ትሥሥር ውጭ ብቻውን ሊረጋገጥ አይችልም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ከጅቡቲ ጋር ያለው ጠንካራ የባቡር፣ የመንገድ፣ የኤሌክትሪክ እና የውኃ ትሥሥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። ከሱዳን፣ ከኬንያ እና ከታንዛኒያ ጋር በተመሳሳይ እነዚህን ነገሮች የምንጋራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሶማሊያ እና ከደቡብ ሱዳን ጋር በመንገድ እና በመብራት ለመተሣሠር ጥረት መጀመሩን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ በዓመቱ ልታሳካ ከያዘችው ዕቅድ ባለፉት 6 ወራት ብቻ 78 በመቶ የሚሆነውን ማሳካት መቻሏን ጠቅሰው፣ ሀገራችን በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በታዳሽ ኢነርጂ እና በከተሞች ውበት ላይ ባከናወነቻቸው ሥራዎች ምክንያት COP32 ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባዔ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ መወሰኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል። ይህም ለሀገሪቱ ትልቅ እውቅና መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው ሀገራት ጭምር የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን ተናግረዋል። በንፍታሌም እንግዳወርቅ #ebcdotstream#AbiyAhmed#Ethiopia#አይሻ2#development

9,200 views