TGINSIGHT CHAT
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
@ebcnewsnow
News and mediaEBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1 @ETVkidschannel @EBCWORLD1 @etventertainment1
Recente posts
Tag: #au · 4 posts
Geplaatst 23 apr
የኢትዮጵያ ዲጂታል ሽግግር እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አፍሪካዊ ራዕይ ********************** ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በቴክኖሎጂው ዘርፍ የጀመረቻቸው ሰፋፊ የለውጥ እንቅስቃሴዎች ለሀገር በቀል ዕድገት ብቻ ሳይሆን ለአህጉራዊ መነቃቃት ፋና ወጊ ሆነው ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና መሪ ሆነው መሾማቸው፣ ሀገራችን በዘርፉ የደረሰችበትን ደረጃ የሚያሳይ ትልቅ አህጉራዊ ዕውቅና ነው። ይህ ሽግግር ኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የፈጠራ ማዕከል እያደረጋት የሚገኝ ሲሆን፣ የዲጂታል ሽግግርን ለሥራ ቅልጥፍና፣ ለአካታች ዕድገት እና ለሉዓላዊነት ቁልፍ መሣሪያ አድርጋ መጠቀሟንም ያረጋግጣል። በለሚ ታደሰ #Ethiopia#digitalethiopia#AU#AbiyAhmed#AI#digitalhealth#EBC ለሙሉ ዘገባው፦ https://web.facebook.com/share/p/1Gkx6KKWpw/
Geplaatst 16 apr
የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀምን፣ አስፈላጊውን የሕግ ማዕቀፍ በማበጀት፣ በአግባቡ መምራት ይገባል - ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ********************** የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የመሩት የአፍሪካ ህብረት ሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት የሚኒስትሮች ስብሰባ በበይነ መረብ ተካሂዷል። ውይይቱ “ሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ አስተዳደር፣ ሰላም እና ጸጥታ በአፍሪካ'' በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው። ስብሰባው በኢትዮጵያ የወሩ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበርነት ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ ነው። የስብሰባው መሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በመክፈቻ ንግግራቸው፥ ሰው ሰራሽ አስተውሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአስተዳደር፣ የኢኮኖሚ ልማት እና ደኀንነት ጉዳዮችን በፍጥነት እየለወጠ መሆኑን ገልጸዋል። መንግሥታት እና ተቋማት በውሳኔ አሰጣጥ፣ በሕዝብ አስተዳደር፣ በደኀንነት ሥርዓት እና በኢኮኖሚ ዕቅዳቸው ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተቀናጀ መንገድ የመጠቀም ሁኔታቸው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን አንስተዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት በአፍሪካ መልካም ዕድሎችን እና ስጋቶችን ጭምር ይዞ መምጣቱንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ዶ/ር ጌዲዮን በንግግራቸው፥ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በአግባቡ በመጠቀም የሚገኙ ትሩፋቶችንም አብራርተዋል። ግጭትን አስቀድሞ ለመከላከል የሚሠሩ ሥራዎችን በማጠናከር፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራዎችን በመተግበር፣ የሽምግልና ጥረቶችን በመደገፍ እና በአጠቃላይ በአህጉሪቱ የአስተዳደር ሥርዓቶችን በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው ዘርዝረዋል። በሌላ በኩል የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም በአግባቡ ካልተመራ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማስፋፋት እና የሳይበር ወንጀሎችን በማበራከት ለሽብርተኛ ድርጅቶች እና ተባባሪዎቻቸው ጥቅም ሊውል እንደሚችል ጠቁመዋል። በመሆኑም ለዘርፉ አስፈላጊውን የሕግ ማዕቀፍ ማበጀት እና ማጠናከር እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል። #Ethiopia#MFA#Africa#AU#ArtificialIntelligence#AI#EBC
Geplaatst 14 feb
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ቻፖ ጋር ተወያዩ ***************** ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ቻፖ ጋር በከተሞች ልማት እና ግብርና፣ ሰላም እና ደህንነትን ጨምሮ በቅድመ-ተኮር ዘርፎች መካከል የተጠናከረ የትብብር እድሎችን ለመለየት የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ብለዋል። #EBC#addisababa#AfricaUnion#AU
Hashtags
Geplaatst 14 feb
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ አዲስ አበባ ገቡ ******* የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል። #EBC#addisababa#AfricaUnion#SouthAfrica#AU