Naujausi įrašai
10 puslapis iš 12 · 133 įrašų
Paskelbta 09-07
ለሰርግ፣ለልደት እንዲሁም ለተለያዩ ፕሮግራሞች የሚሆን የጥሪ ካርድ እና ሰርተፍኬት ማሰራት የምትፈልጉ በ 0996697135 ወይም በዚ ቴሌግራም ያናግሩን @Ela_117
Paskelbta 09-07
Open Ai በAI የታገዘ የስራ ቅጥር ፕላትፎርም እየገነባ ነው። የChatGpt መስራች የሆነው ይህ ድርጅት እንደገለፀው ከሆነ ቢዝነሶችን እና ተቀጣሪዎችን የሚያገናኝ ፕላትፎርም እየገነባ ነው። በAI የታገዘው ይህ platform ስሙ Open Ai job platform ሲሰኝ ከሊንክዲን ጋርም ተፎካካሪ ሊሆን ይችላልም ተብሏል። ይህ ፕላትፎርም በ2026 አጋማሽ ወደ ስራ እንደሚገባ የሚጠበቅ ሲሆን ትናንሽ ቢዝነሶችንም ሊጠቅም እንደሚችል ተገልጿል።
Paskelbta 09-07
ሩዋንዳ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ራሱን በራሱ ማብረር የሚችል የአየር ላይ ኤሌክትሪክ ታክሲ አስተዋወቀች። ሩዋንዳ self-flying ወይም ራሳቸውን በራሳቸው የሚያበሩ የአየር ላይ ታክሲ በመጀመር ከአፍሪካ ፈር ቀዳጇ ሀገር መሆን ችላለች። ከChina Road and Bridge Corporation እና EHang Holdings Limited ጋር በመተባበር እንደተሰራች የተገለፀችው ይህቺ የአየር ላይ ታክሲ ኪጋሊ ላይ በተዘጋጀው የAviation Africa 2025 ፕሮግራም ላይ ለእይታ ቀርባለች። EH216-S የሚል ስያሜ ሲሰጣት ከፍተኛ ፍጥነቷ 130 ኪሎ ሜትር በሰአት እንዲሁም ለ35 ኪሎ ሜትር ወይም ለ21 ደቂቃ መብረር ትችላለች ተብሏል። ሹፌር አልባ የሆነችውና ከelectrically vertical takeoff and landing (eVTOL) የኤርክራፍት ቤተሰብ የምትመደብ ሲሆን ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶችና የአቪዬሽን ባለሙያዎች በተገኙበት በኪጋሊ ሰማይ ላይ መብረር ችላለች።
Paskelbta 09-06
#tech_tip የwindows ተጠቃሚ ከሆናችሁ ኪቦርዳችሁ ላይ የሚገኘውን የwindow key ከሌሎች ቁልፎች ጋር አንድ ላይ በመንካት የምታገኟቸው shortcuts (part 2) 1 Win + tab = task view ወይም እንደስልክ የተከፈቱ መተግበሪያዎችን ለማየት። 2 Win + Ctrl + D= አዲስ virtual desktop ለመፍጠር። 3 Win + Ctrl + Left/Right= የፈጠርናቸውን virtual desktops ለመቀያየር። 4 Win + Ctrl + F4= የፈጠርነውን virtual desktop ለመዝጋት። 4 Win + Print Screen=ኮምፒውተራችን ላይ screenshot ለማንሳት። 5 Win + Arrow keys= ሁለትና ከሁለት በላይ ነገሮችን ስክሪናችን ላይ ለመክፈት እንጠቀምባቸዋለን። ሞክሯቸው! 6 Win + Number (1-9)= taskbar (ከታች) pin የተደረጉ መተግበሪያዎችን ለመክፈት ለምሳሌ መጀመሪያ ላይ Microsoft store ከሆነ ያለው Win+1 ስንነካ Microsoft store ይከፈታል።
Hashtags
Paskelbta 09-06
የተለያዩ ቪዲዮዎችን በAI generate ማድረግ ከፈለጋቸው በዚህ የCapcut Website ላይ መስራት ትችላላችሁ። https://pippit.capcut.com/ በጣም ደስ የሚለው feature የፈለጋችሁትን ዌብሳይትም ይሁን የsocial media link አስገብታችሁለት የሚገርም video generate ያደርግላችኋል። Watermark ይኖረዋል እንጂ በጣም አሪፍ website ነው ሞክሩት።
Paskelbta 09-06
Huawei new feature on huawei mate 70 pro
Paskelbta 09-05
Instagram ላይ Live ለመግባት ከ1ሺ በላይ ፎሎዎር መኖር ግዴታ ሆኗል። ከዚህ በፊት Live ለመግባት ምንም አይነት የፎሎዎር ቁጥር አይጠይቅም ነበር። Instagram ይህን ማሻሻያ ለምን እንዳደረገ ይፋ የተደረገ ነገር የለም።
Paskelbta 09-05
Whatsapp አዲስ የደህንነት tool አስተዋወቀ። Safety overview የተሰኘው ይህ feature የWhatsApp ተጠቃሚዎችን ደህንነት የሚጨምር ነው ተብሏል። ይህ feature ተጠቃሚዎች ወደ ግሩፕ add ሲደረጉ ከመግባታቸው በፊት sefty overview ያያሉ። ከዚያም ምንም text ሳያዩ መውጣት የሚችሉበትን አሰራር አካቷል። እንዲሁም ኮንታክቶቻችሁ ያልሆኑ ሰዎች message ሲያደርጉላችሁ alert የሚያደርግ አሰራር እየሞከረ meta እንደሆነ ይፋ አድርጓል። በተጨማሪም WhatsApp በ2025 አጋማሽ ብቻ 6.8 ሚልዮን አካውንቶችን ban አድርጓል።
Paskelbta 09-05
Microsoft Lense መስራት ሊያቆም ነው። Microsoft Lens በ2015 ወደ ስራ የገባ እና document scan በማድረግ ወደ Word, pdf እና ወደመሳሰሉት digital format የሚቀይር መተግበሪያ ነው። ይህ መተግበሪያ Google play store ላይ ከ50 ሚልዮን በላይ download ማግኘት ችሏል። እንዲሁም በios ላይም በርካታ ተጠቃሚዎች አሉት። Microsoft lense ከplay store እና App store በNovember 15, 2025 የሚወገድ ሲሆን ከDecember 15, 2025 ጀምሮ scan ማድረግ ያቆማልም ተብሏል። ተጠቃሚዎችም በMicrosoft Lens ምትክ Microsoft 365 Copilot መተግበሪያን እንዲጠቀሙ Microsoft አሳስቧል።
Paskelbta 09-05
#እንድታውቁት ቴሌግራም ላይ ሁለት ተመሳሳይ የሚመስሉ ነገር ግን የተለያዩ settings አሉ። የመጀመሪያው settings> privacy and security ውስጥ ከገባን በኋላ የምናገኘው Delete my account ... if away for የሚለው ሲሆን ይህም ወደ ቴሌግራም ለምን ያህል ጊዜ ካልተመለስን አካውንታችንን Delete እንዲሆን የምናስተካክልበት ሲሆን አሁን ላይ ከፍተኛ የጊዜ ገደቡም 24 ወር ነው። ሌላኛው ደግሞ settings> Devices ውስጥ ስንገባ የምናገኘው Automatically terminate old sessions ... if inactive for የሚለው እና አንድ device ላይ ለምን ያህል ጊዜ ቴሌግራም ሳንጠቀም ከቆየን አካውንቱን ከዛ device ላይ ብቻ ያጥፋው የሚለውን የምናስተካክልበት ነው። አሁን ላይ ይህም ከፍተኛው ማድረግ የምንችለው የጊዜ ገደብ 12 ወር ነው።
Hashtags
Paskelbta 09-04
chatGPT Project feature ተካቶለታል። ይህን ፊቸር ለማግኘት ሦስት ሰረዙን ከነካችሁ በኋላ New project የሚለውን በመምረጥ create ማድረግ ትችላላችሁ። ሙሉ የፕሮጀክታችሁን ፋይል upload በማድረግ analyze ያደርግላቸል። -Larger file uploads per project (up to 5 for Free, 25 for Plus, 40 for Pro/Business/Enterprise) -Option to select colors and icons for more customization. -Project-only memory controls for more tailored context.
Paskelbta 09-04
እንዴት የላፕቶፓችንን የባትሪ ይዞታ ማወቅ እንችላለን? ላፕቶፕ በምትገዙበት ጊዜ የላፕቶፓችሁ ባትሪ ሲመረት የነበረው እና አሁን ላይ ያለውን የባትሪ ይዞታ/መጠን ቼክ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ይህንንም ለማድረግ በመጀመሪያ windows+R ተጭነን የሚመጣልን textbox ላይ cmd ብለን እንፅፋለን። በመቀጠልም፦ powercfg /batteryreport ብለን በመፃፍ enter እንነካለን። ከዚያም እንደዚህ አይነት/ተቀራራቢ/ ፅሁፍ ይመጣልናል። battery life report saved to file path C:\Users\yourname\battery-report.html . በመጨረሻም start ብለን ፅፈን ከጎኑ የፋይሉን path ብቻ copy አድርገን paste እናደርጋለን። ለምሳሌ፦ start C:\Users\yourname\battery-report.html አሁን ስለ ላፕቶፓችን የተለያዩ መረጃዎችን እናገኛለን። ትንሽ ዝቅ እንዳደረግን DESIGN CAPACITY እና FULL CHARGE CAPACITY የሚሉ ምርጫዎች የምናገኝ ሲሆን DESIGN CAPACITY ከሚለው አጠገብ ያለው ባትሪው ሲመረት ያለው አቅም በmWh ሲሆን ከFULL CHARGE CAPACITY አጠገብ ያለው ደግሞ አሁን ላይ ያለው የባትሪው የመያዝ አቅም በmWh ነው።