የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
ገጽ 13 ከ 15 · 169 ልጥፎች
Join the Channel and boost your knowledge🔥 የሚጽፍ ፣ የሚናገርለት ከተገኘ ሁሉም ነገር ታሪክ አለው! የእንስሳት ሀብት ዘርፍ ታሪክ በዚህ አለ። በዘርፉ ያሉ ሰዎች ስኬት፣ውጣውረድ ፣ ልምድና ህይወት በራሳቸው አንደበት እዚህ ይደመጣል። ለሀሳብ እና አስተያየት: @yared2774@adey67 🦋#Share🦋 👩💻@Campus_Voice_2016👨💻 👩💻@Campus_Voice_2016👨💻 👩💻@Campus_Voice_2016👨💻
Hashtags
ታትሟል ኦክቶ 11
ቀለሜነት እና የእንስሳት ደህንነት(እንደ መንደርደርያ)
ታትሟል ኦክቶ 11
ቀለሜነት እና የእንስሳት ደህንነት(እንደ መንደርደርያ)
We are thrilled to announce the launch of new hashtag on our channel: #HaSab #ሀሳብ it's a fascinating hash tag platform dedicated to share insightful opinions about veterinary fields, Animal production, food safety, public health, animal welfare, one health, entrepreneurship and other related issues. The term #HaSab means "opinion" in Amharic, and its purpose is to stimulate constructive discussions and encourage meaningful change. We believe that every individual's opinion is valuable and unique, based on their own experiences, studies, and thoughts. By sharing your opinion through this platform, you can contribute to better understanding the challenges we face and inspire others to take action. We challenge all members of our channel to participate in this exciting initiative and collaborate with us in finding solutions to the problems we encounter as a sector and a country. Don't hesitate to contact us at @yared2774 & @adey67, and let's start sharing our opinions using #HaSab! https://t.me/Hasab_2016
#HaSab #Animalhealth ✳️ሰላም ውድ የCVMA ማህበረሰብ ቻናል ቤተሰቦች እረፍት እንዴት ነው? በምንስ እያለፈ ነው? ጥሩ እና አሪፍ ነው የሚል ምላሽ እንደሰጣችሁኝ አልጠራጠርም። እንደ ግሌ አንዳንድ የተሰሙኝን እና መናገር አለብኝ ብዬ ያሰብኳቸውን መልዕክቶች ለማጋራት ወደድኩ። ✳️ስሜ በተስፋሁን ይባላል የካምፓስ Voice መስራች እና Editor ነኝ። ሁል ጊዜ የትምህርት መንፈቀ አመት ከተጠናቀቀ ቡኃላ የእረፍት ጊዜ ሲመጣ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ብዙ በማቀድ ትንሽ በመስራት የማሳልፍ ነኝ፤ የምሰራት ስራ ትንሽ.....ነገር ግን ፍሬያማ እንድትሆን እጅጉን እተጋለሁ።ጓደኛዬ ያሬድ በምንሰራቸው ስራዎች ሁሌም ጉልህ ሚና ይጫወታል።በምንሰራቸው ብቻ ሳይሆን ከእኔነቴ እንዳልጎድል እንደ ታላቅ ወንድም No በተስፋ ይሄ ጥሩ አይደለም ይለኛል። ✳️ብቻ ለእኔ መሰረት መያዝ ጉልህ ሚና የተጫወተ እና ወደፊትም የሚጫወት ወንድሜ ነው ዛሬ ለወንድሜ ያሬድ Credit ለመስጠት ወይም ስለግል ታሪኬ ለማጋራት ሳይሆን አሁን ያለሁበት ጅማ ከተማ ከመጣሁበት ሰዓት አንስቶ ለሞያችን እድገት መንቀራፈፍ እንደ ግብዐት ሆኖ የሚያገለግሉ ችግሮችን ለመጥቀስ ነው።በእርግጥ በአሃዝ የተገለፀ ቁጥራዊ መረጃ ባይኖረኝም በአይኔ አይቼ በልቤ ያስተዋልኳቸውን ችግሮች እንደሚከተለው እዘረዝራለሁ። ✳️እዚህ ያለሁበት ጅማ ከመጣሁ የመጀመሪያ ችግር ሆኖ ያየሁት የመድኃኒት እጥረት ነው፤ ይሄ ችግር ቀላል የሚባል አይደለም። ለምሳሌ በ 2030 እናጠፈዋለን ብለን ዘመቻ ለጀመርነው Rabies virus vaccination የመድኃኒቱ አቅርቦት ማነስና በተገቢው አለመሰጠት ትልቅ ተግዳሮት ይሆናል። ጅማ ላይ አምና እና ካቻምና በጠየቁበት ሰዓት በርካታ Vaccine የተላከ ቢሆንም ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስላልተሰጠ የህክምና ጣቢያ የመጡት ብቻ ተከትበው መድኀኒቱ ሙሉ ለሙሉ Expired ሆኗል። አሁን ለእረፍት በገባውበት ሰዓት ደግሞ ተማሪዎች አስተባብረን ለመከተብ ስናስብ የመድኃኒት አቅርቦት የለም።ሚገርም ነው መድኃኒቱ ሲገኝ ባለሙያዎች ትኩረት አንሰጥም😔ትኩረት ስንሰጥ ደግሞ መድኃኒት የለም😔ብቻ Rabies Vaccine እንደምሳሌ አነሳው እንጂ በርካታ መድኃኒት በየህክምና ጣቢያው የለም!!! ያለውም ከጥቅም ውጪ እየሆነ ነው። የሚመለከተው አካል ትኩረት ቢሰጠው እላለሁ 🙏🙏🙏 ✳️እኛም እንደ ተማሪና ጉዳዩ ይመለከተኛል እንደሚል ባለሙያ ምን መደረግ ነበረበት❓ምንስ እናድርግ❓ ✳️ሁለተኛ በሀገር አቀፍ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ምክንያት እና በተለያዩ ምክንያቶች የህክምና ጣቢያዎች ዝግ ይሆናሉ። እንደ ጅማ ከሰሞኑ Emergency case መተው እርዳታ ባለማግኘታቸው የሞቱብን እንስሳት በርካታ ናቸው Including my neighbouring dog 😔። ጊቢው እንዲፈቅድ ባለሙያዎቹ ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ማንም ሰው የህክምና ቅጥር ጊቢ ውስጥ መገኘት ስለሌለበት እንደተከለከሉ ሰምቻለሁ። ✳️ምን ያክል የእንስሳት ህክምና ጣቢያዎች እንደ ሀገር ተዘግተው ይሁን❓ይሄን ተከትሎም ምን ያክሉ እንስሳት መዳን እየቻሉ ሞተው ይሁን❓በአንጋፋው CVMA እንኳን የአገልግሎት ጊዜ ከጠዋት 2 ሰዓት እስከ ቀን 6 ሰዓት ብቻ ነው አገልግሎት የሚሰጠው WHY❓እንደግሌ አልተመለሰልኝም❓እንደኔ እንደኔ ወጣት እና በቂ የሆነ የሰው ኃይል በዲፓርትመታችን አለን ቢቻል እስከ ቀን 11 ወይም 12 ሰዓት ቢሰራ✅ አንድ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠርና ማገልገል ይቻላል፤ሁለት እንስሳቶቹ ተገቢውን ህክምና ያገኛሉ፤ሶስት ሞያችን ይከበራል ያድጋልም። ---በተስፋሁን አበራ-- 4th year DVM
Hashtags
ታትሟል ሴፕቴ 10
#HaSab #animalwelfare ወደ አህያ ቄራ ጉዳይ ደግሞ እንምጣ! ቻይና ኢጃ'ኦ(Ejiao) የሚባል ባህላዊ መድሀኒት አላት። መድሃኒቱ ለደማነስ፣ ራስ መታወክ፣ የእንቅልፍ እጦት እና የወር አበባ መዛባት ፍትሁን ነው ተብሎ በተጠቃሚዎቹ ይታሰባል። የሚቀመመውም የአህያ ቆዳ በእሳት ተፈትኖ በሚገኘው ጄላቲን ነው። ኢጃ'ኦን ለማምረት ቻይና በአመት የ4.8 million አህዮችን እርድ ትፈልጋለች። ይህ አለም ካላት 55.5 million የአህዮች ብዛት አንጻር እጅግ የተጋነነ እና ጣርያ የነካ የፍላጎት መጠን ከ1990-2018(እ.አ.አ) የቻይናን የአህያ ብዛት ከ11.1 million ወደ 2.5 million እንዲሽቆለቁል አድርጎታል። የሀገሪቱ የመካከለኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ ክፍል የዚህ መድሃኒት ሁነኛ ፈላጊ መሆንና የመካከለኛው ኢኮኖሚ በቻይና ጥሩ መሻሻል በማሳየቱ ቁጥሩን አግዝፎታል። በተጨማሪም ቻይና በምርቱ ላይ ያላትን የቀረጥ መጠን መቀነሷ እና የኢንፖርት መጠን እንዲያድግ ማድረጓ እንዲሁም የመድሃኒቱ ዝነኛ መሆን ለፍጆታው መጨመር እንደምክንያት ይጠቀሳል። እ.አ.አ በ2017 አንድ ኪሎ ለኢዳ'ኦ የሚውል የአህያ ቆዳ በ830 የአሜሪካ ዶላር ተሽጧል። ከዚህ ውስጥ 90% የተገኘው ከሌሎች እንደ አፍሪካ ያሉ የአለም ክፍሎች ኤክስፖርት ከተደረገ አቅርቦት ነው። The gardian በ2019 እንዳወጣው ዘገባ ከሆነ ይህ ፍላጎት በዚህ ከቀጠለ በኢጃ'ኦ ምክንያት የአለም የአህያ ብዛት በአምስት አመት ውስጥ በግማሽ ይቀንሳል። ቻይና አህዮቻቸውን ፍለጋ የዳበሰቻቸውን ሀገራት ዳታ ስንመለከት ደግሞ:- -ጋና እ.አ.አ በ2013 የአህያ ቄራ ከፍታ እጅግ አሳሳቢ በሆነ መልኩ የአህያ ቁጥር መመናመን፣ ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ በመስፋፋቱ በ2017 ዘግታለች። -በቦትስዋና የአህያ ቆዳ ኤክስፖርት መጀመሩን ተከትሎ 60% የአህያ ቁጥር ቀንሷል። -ታንዛኒያ ጫናውን ለመቋቋም ለ10 አመት የአህያ እርድን ከሀገሯ አግዳለች። -ናይጄርያ የኢጃ'ኦ ምርት በህጋዊም በህገወጥም መንገድ ጥሬ እቃ የሚያገኝባት ማዕከል ሆናለች -ጎረቤት ሀገር ኬንያ ደግሞ ከቻይና ጋር ይህንን ንግድ ለማሳለጥ የሁለትዮሽ ስምምነት አላት። እነዚህ ሀገራት ቀጣይ እጣ ፋንታዎቻቸው ምን የሚሆን ይመስላችኋል? ይህ ንግድ ጉዳቱ ወይንስ ጠቀሜታው ይጎላል? የሀገራችንን ጉዳይ ደግሞ በመጨረሻ ጽሑፌ እንመለከታለን። ያሬድ ኤርሚያስ 3rd year DVM student, AAU-OHC Founder and secretary, Membership director of Rotaract club of Kuriftu.
Hashtags
ታትሟል ሴፕቴ 10
#HaSab #Animalwelfare 1.4 Billion ዶላር አመታዊ ፋይዳ! ባለፈው "ከቻይና እንበልጣለን" በሚል ርዕስ አንድ ጽሑፍ አጋርቼ ነበር። ጽሑፉ በሀገራችን ያለውን የአህያ መረጃ እንዲሁም የDonkey sanctuary አመሠራረት ለመዳሰስ ሞክርያለሁ። በዛሬው ጽሑፍ ደግሞ የአህያ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እና በአሰላ ከተማ የተገነባው የአህያ ቄራን ሁኔታ ለመመልከት እንሞክር። በሀገራችን አብዛኛው የእርሻ ቦታ እና የመኖርያ መንደር እጅግ የተራራቀ ነው። ገበሬው በለሊት ተነስቶ በሬውን፣ ሞፈር እና ቀንበሩን ይዞ ሌሎች በእርሻው ወቅት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በአህያው ጀርባ አኑሮ ወደ እርሻው ይሄዳል። ቡቃያው አፍርቱ እህሉ እስኪደርስ ድረስ ለሚያከናውናቸው ተግባራት የሚጠቀማቸውን መሠርያዎች የምትሸከምለት አህያው ነች። በተጨማሪም አዝመራ በደረሰ ጊዜ አህያ የእውቅያ ስርዓቱ ላይ ትልቅ ሚና አላት።(የህዳር አህያን ታውቃላችሁ? ህዳር አዝመራ የሚደርስበት ወቅት እንደመሆኑ የህዳር አህያ ለመንደሩ ሰው ሁሉ ግልጋሎት ትሰጣለች። አህያዬን ለምን ወሰድክ የለም!) ስለዚህ አንዲት አህያ ከእርሻ እስከ ጎተራ መሙላት ድረስ ፋይዳዋ ብዙ ነው። የሀገሬ ገበሬ "አህያዬ ባትኖር እኔ ና ሚስቴ አህዮች ነበርንን ይላል።" ሸክማችን ሸክሟ ሆኖ ነው እንደሰው ያለ ሸክም የምራመደው ማለቱ ነው። በተጨማሪም በሀገራችን ጉራማይሌ መልከዓ ምድር የቆላን ምርት ለደጋ የደጋውን ለቆላ ለማድረስ የአህያ ማጓጓዣ መጠቀም ግዴታ ነው። ገና መሠረተ ልማት በየደጃፋችን የደረሰልን ሀብታም ሀገር አይደለንም። እጅግ ብዙ ይቀረናል። የአቀበት ቁልቁለት ስቃይን ተቋቁሞ እንደ አህያ የተሸከመልን ቴክኖሎጂ የለም። መሠረተ ልማት ቢሟላልን እንኳ የነዳጅ ነገር እንኳን ለገጠሩ ለከተማውም ከአቅም በላይ ነው። እጅ ላይ ያለች ብቸኛ አማራጭ ነች አህያ። ቅዳሜ ገበያ ሄዶ ሊሸምት ያሰበ ከአህያ ጀርባ ላይ ሸክም ሲወርድ ሳያይ አይመለስም። ይህ ብቻ ሳይሆን በገጠር ከተማዎች የእለት ጉርሳቸው በአህያ ጋሪ ጭነት የሚጎርሱ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። የአንዲት አህያ በቤት ውስጥ መኖር ለሴቶች፣ለአቅመ ደካሞች እና ህፃናት ፍይዳው ብዙ ነው። አንድ በሬ ሊጠቀምበት የሚችለው የቤቱ አባወራ ብቻ ነው። ነገር ግን አንዲት አህያ ለአባወራው እህል በመውቃት፣ በመሸከም እና በማጓጓዝ ብታግዝ ለእማወራይቱ ደግሞ ወሃ ከሩቅ ቀድቶ በመምጣት፣ ለማገዶ እንጨት ለቅሞ ለማምጣት፣ በጓሮ ተክለው ያጸደቁት አትክልት ጀርበቸው ሳይጎብጥ የሚፈለገው ቦታ ወስዶ ለመሸጥ ግልጋሎት ይሰጣሉ። የግል ገቢም ይኖራቸዋል። እቤቱ አህያ ያለ ህፃናት "ወሃ ከምንጭ ሳትቀዳ ወደ ትምህርት ቤት አትሄድም!" አይባልም። ጉልበቱ በመጠኑም ቢሆን ከመበዝበዝ ያርፋል። ለማጥናት ጊዜ ይኖረዋል። ለአቅመ ደካሞችም የለት ገቢያቸው ጥቂት ለሆነ የአህያ ጭነት መተዳደርያ ነው። ስለዚህ አህያዎች እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት በተለይም ለገጠርራማይቱ ክፍል እጅግ ጠቃሚ ናቸው። ሰዎች እና ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ፣ ለእርሻ እና ውቅያ፣በተጨማሪም በተለያዩ የግንባታ ስራዎች ወቅት የግንባታ እቃዎች ለማጓጓዝ ያገለግላሉ። ከሌሎች የትራንስፖርት አማራጮች አንጻር(እንደ መኪና) ዋጋቸው ርካሽ መሆኑ በቀላል በታችኛው የኑሮ እርከን ያሉ ሰዎች እንዲያገኟቸው እና እንዲጠቀሙባቸው ያደርጋል። ይህ ችላ የሚባል ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አይደለም። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አህያ ለኢትዮጵያ GDP 1.4 Million የአሜሪካ ዶላር አመታዊ ፋይዳ አላት። አሁን ባለው የእንስሳት ደህንነት ደረጃ እና የግብርና አቅም ይህን ያህል ከፈየደ ይበልጥ ብናድግ እና ብንሻሻል ፋይዳው ምን ይህል ይሆን? እንቀጥላለን ያሬድ ኤርሚያስ 3rd year DVM student, AAU-OHC Founder and secretary, Membership director of Rotaract club of Kuriftu.
Hashtags
ታትሟል ሴፕቴ 10
#HaSab #Animalwelfare ከቻይና እንበልጣለን! በኢትዮጵያ በተለይም በገጠራማው አከባቢ ከሦስት አባወራዎች አንዱ አህያ እንዳለው ይታመናል። የሀገራችን የአህያ ዝርያ በአራት የሚከፈል ሲሆን እኚህ ዝርያዎች ጅማ፣ አቢሲኒያ፣ ኦጋዴን እና ሰናር የሚባሉ ሲሆን፤ በሀገሪቱ በቆላ፣ደጋ እንዲሁም በተለያዩ የምድሪቱ የተፈጥሮ ሁኔታዎች ጋር ስሙሙ ሆነው ይኖራሉ።እ.ኢ.አ በ2013 በFAO በተሰራ ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ የ7 million አህዮች መገኛ ናት። የቅርብ መረጃዎች ደግሞ ቁጥራቸው እስከ 8.5 million ሊደርስ እንደሚችል ይናገራሉ። ይህ ቁጥር ቻይናን በማስከተል በአለም ትልቅ ቁጥር ያላት ሀገር ያደርጋታል።(ከቻይና የምንበልጠው እንግዲህ በቁጥር ነው!) አህያ የፈረስ ቤተሰብ የሆነው Family Equidae አባል ነች። አመቱን ሙሉ መራባት ትችላለች። በእንክብካቤ እና በደህንነት መያዝ ከተቻለ እስከ 30 አመት ትኖራለች።(በኢትዮጵያ በአማካይ ከ4-6 ዓመት ብቻ ነው የምትኖረው)። ደረሰች የምትባልበት እድሜ ከ2-3 ዓመት ሲሆን በዚህ ግዜ ጥሩ የሚባለው የሰውነት ክብደት 105kg ነው።እህች ጠንካራ እና ብርቱ ፍጥረት ጥሩ የማስታወስ ችሎታ አላት።የተጓዘችበትን መንገድ በፍጹም አትረሳም።(የሀገር ሰው ሲተርት "የምትሄድበት መንገድ ቢጠፋህ አህያህን ተከተል።" ይላል።) የሸሆና ጥፍራቸው ጠንካራ መሆን እና አስቸጋሪ መንገዶችን ተጋፍጠው መጓዝ መቻላቸው ከሌሎች የፈረስ ቤተሰቦች ይልቅ ለሸክም እና ለማጓጓዣነት ተመራጭ አድርጓቸዋል በኢትዮጵያ አንዲት አህያ ከ6-100kg(አንዳንዴም ከዛ በላይ) ተሸክማ ከ15-20 km ያክል ርቀት ከ5-6 ሰዓታት ያለ እረፍት ልትጓዝ ትችላለች። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የምድር ወገብ ሀሩር አውራጃዎች(Tropical region) አህዮች በብዛት በመንጋጋ ቆልፍ (tetanus)፣ ተዋስያን(internal and external parasites)፣ ወበቅ(intense heat)፣ በተለያዩ የመቁሰል አደጋዎች( Traumatic injury)፣ ተገቢ የሆነ አመጋገብ እጥረት እና የሸሆና ጥፍራቸው ከመጠን ያለፈ በማደጉ ለሚመጡ ችግሮች ተጋላጭ ናቸው። በተለይም በሸክም መብዛት እና ከመጠን ያለፈ ድብደባ የሚቆስሉ እና የሚሰቃዩ አህዮች ቁጥር ቀላል አይደለም። Donkey sanctuary በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የእንስሳት ህክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል። Donkey sanctuary እ.አ.አ በ1969 ኤልሳቤት ሳፈንድሰን በተባለች የእንስሳት ደህንነት አቀንቃኝ በእንግሊዟ ዴቮን ተመሥርቷል።ሲቋቋም ዋና አላማው ለአህዮች ደህንነት ምቹ የሆነ ከባቢን መፍጠር የነበረ ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅተ በአውሮፓ፣አፍሪካ እና አሜሪካ ውስጥ በአህዮች ደህንነት ጥበቃ፣ በእንስሳት ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጥ እንዲሁም የተለያዩ ባለሞያዎችን ማስተማርና ማሰልጠን ላይ አበክሮ ይሰራል። ቅርንጫፉም በ40 ሀገራት ውስጥ ይገኛል። Donkey sanctuary በኢትዮጵያ እ.ኢ.አ በ1986 ዓ.ም በፕሮፌሰር ፍሰሃ ገ/አብ አማካኝነት ተመስርቶ እየሰራ ይገኛል።
Hashtags
ታትሟል ሴፕቴ 10