የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
ገጽ 12 ከ 15 · 169 ልጥፎች
ታትሟል ፌብ 20
#HaSab #animalwelfare ወደ አህያ ቄራ ጉዳይ ደግሞ እንምጣ! ቻይና ኢጃ'ኦ(Ejiao) የሚባል ባህላዊ መድሀኒት አላት። መድሃኒቱ ለደማነስ፣ ራስ መታወክ፣ የእንቅልፍ እጦት እና የወር አበባ መዛባት ፍትሁን ነው ተብሎ በተጠቃሚዎቹ ይታሰባል። የሚቀመመውም የአህያ ቆዳ በእሳት ተፈትኖ በሚገኘው ጄላቲን ነው። ኢጃ'ኦን ለማምረት ቻይና በአመት የ4.8 million አህዮችን እርድ ትፈልጋለች።…
#HaSab #collaboration Yo! How do you see your classmates, dorm mates, or the midfielder on the football field, the high-achieving student at the college? The active and interactive one? How do you see your surroundings? Let me tell you about a bunch of opportunities you shouldn't miss! If you're in an environment that has the chance to be exposed to diversity, this blog is for you! እንደ ግለሰብ የትምህርት ስርዓታችን የአንደኝነት አተያያችንን አዛብቷል ብዬ አምናለሁ። ከታች ጀምሮ ተሻግረን ከመጣናቸው ብዙ ደረጃዎች ስኬት በላይ በተቀደምነው አንድ ደረጃ ላይ ትኩረታችንን እንድናደርግ ሁነናል! ቀለሜዎች ከእናንተ መሃል ሁለተኛ ስለወጣ ያላዘነ ማነው? ከደረደራቸው ብዙ A+ በላይ የተፎካካሪው B ያላስደሰተው ማነው? በርግጥ አንዱ ሌላውን የመብለጥ ጉዳይ ተፈጥሯዊ መሆኑና ሁላችንም የአሸናፊነት ስሜት እና ወኔ ሌኖረን የተገባ ቢሆንም ለአንደኝነት ያለን ግምት እና የትምህርት ስርዓታችን ውስጥ ያለው የእሽቅቅድም ስሜት ግን አንድ ከአሸናፊነት ማማ ሁላችንንም የሚያወጣን መንገድ ወደጎን እንድንተው ያደረገ ይመስለኛል! መንገዱን ጠየከኝ? ቆይ እነግርሃለው ታገስ! እየተማርክ ያለኸው ዘርፍ እንደ ባህር ያለ ነው። ብትቀዳው ከያዝከው አቁማዳ በላይ የሆነ፣ ሞልቶ የሚፈስ። ስለዚህ ከምትማራቸው እልፍ ጉዳዮች በተወሰኑት ላይ ብቁ እና ከሁሉም የተሻልክ መሆንህ አይቀሬ ነው። የተወሰኑት ደግሞ ትኩረትህን ላይስቡት ይችላሉ። ወዳጅህስ? ክፍል ውስጥ ከጎንህ ያለው ተማሪ በየትኛው ሌክቸር ክላስ ይመሠጣል? ዶርም በሶ አብሮህ የሚበጠብጥ ጓደኛል የትኛውን ኮርስ ፈተና ቢኖር ባይኖር ሁሌም ያነባል? የተኛው ወዳጅህ ከየትኛው የ Clinical case ፊት አታጣውም? ይህንን የምጠይቅህ አውቀህ እንድታደንቀው ብቻ አይደለም! ማድነቅ እማ አለብህ! ነገር ግን ልነግርህ ያሰብኩት ከዛ ይልቃል። Actually its a good opportunity you shouldn't miss! potential collaborator! አዎን የዛሬው ዶርም ሜትህ የነገ ትልቅ ቢዝነስ ካምፓኒ ፓርትነርህ ሊሆን ይችላል። ዥረት የሚፈጥሩት የመርፌ ክር ታህል ቅጥነት ያላቸው የወሃ መስመሮች ተዋህደው ነው። በጋራ ጥሩ የሆናችሁበትን ነገር በማዋሃድ አልያም አንዳችሁ ጎበዝ የሆናችሁበት ነገር የሌላኛችሁን ክፍተት እንዲሞላ በማድረግ ነገ ትልቅ ደረጃ የሚደርስ #HaSab ማፍለቅ ትችላላችሁ። እመኑኝ ከግቢ ከወጣችሁ በኋላ ይህን እድል አታገኙትም! ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ገንዘብ ያለው ሰው በብዛት የሚሰማራው ንግድ ላይ ነው! ብራቮ እናንተ ደግሞ ካፒታላችሁን በጋራ አድርጋችሁ ከባንክ ብድር ተባጥሳችሁ አምራች መሆን ትችላላችሁ። በየትኛውም መስክ ሊሆን ይችላል። ይህን የሚወስነው ያንተ እና የወዳጅህ እውቀት እና ፍላጎት ነው። ከፉክክር ይልቅ የትብብር ሀይል ይበልጥ ያደምቃል። ለየብቻችን ጭላንጭል ብርሃናትን መፍጠር ላይከብደን ይችላል። መድመቅ ግን ያለው ከህብረት ነው። ከባህር ውስጥ ብዙ ወሃ የሚጨልፈውም ቢሆን ከአንድ ይልቅ ሁለት ሦስት አቁማዳ ነው። አሁን ያለው ገበያ እጅግ ፉክክር ያለበት እና ንቁ አምራች እና ሻጭ የሚፈልግ ነው። Dave Ramsay ምን ይላል መሠለህ:- " Marketing is not an option for business that wants to keep their doors open." ሁሌም በሩ ክፍት የሆነ የማይናወጥ ስኬታማ የስራ መስክ ከፈለክ የያዝከውን እውቀት፣ ጥበብ፣ ልምድ ፣ የፈጠራ ሀሳብ እና ገንዘብ ይበልጥ እንዲያተርፍ አድርገህ መሸጥ የምርጫ ጉዳይ አይደለም!! ግዴታ እንጂ። ስለዚህ የምረቃ ጋወንህን እንዳወለክ ያለህን ለረጅም አመት ተባብረህ ካጠናኸው አብሮ አደርህ(dorm mate ለማለት😁) አልያም ብርቱ ከምትለው ወዳጅህ ጋር አዋህደህ በ bulk አምርት። በገበያው ውስጥ ሁሌም ክፍት የሆነ ቢዝነስ ይኑርህ! why not? ይህንን የጻፈልህ ያሬድ ነው። ገና ተማሪ ሳለህ በተለይ በአንድ ጤና እሳቤ፣ በእንስሳት ደህንነት ዙርያ መሥራት የምትፈልገው ልዩ ሀሳብ ካለህ መተባበር እንችላለን። ማናችንም የምንሰራቸው እያንዳንዱ ስራዎቻችን የሰዎችን፣ የእንስሳትን እና የአከባቢ ጤናን ያገናዘቡ ሊሆኑ ይገባል። እኚህን የሚያጓድል ስራ ብኩን ነው። የእንስሳትን ደህንነት የሚጠብቅ ሰው ሩህሩህ ነው። ርህራሄ እውቀት ብቻ ሳይሆን ለተፈጥሮ የሚጨነቅ መልካም ልብን ይፈልጋል። ይህን ለመፍጠር ትሩ ግንዛቤ እና ሁሉን ማጣቀሻ የሚደርገው የጋራ ህግ ያስፈልጋል። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ መስራት ፋይዳው ብዙ ነውና አሳብህን ልታጋራን ወደኋላ አትበል። ሀሳብህን መሬት ለማውረድ እና ተጽእኖ ለመፍጠር መተባበር እንችላለን። የተለየ #HaSab ካለህም አጋራን። @Adey67@yared2774 ደግሞ እንዲያነቡ ወዳጆችህን ጋብዝ! መልካም የረፍት ቀን!!
Hashtags
ታትሟል ዲሴም 31
#Seminar #Food_Safety 3 Pathogens, 1% GDP It's not hidden that food safety needs a lot of improvements and there is a lot of work to be done for its betterment in Ethiopia, but when we are dealing with numbers from research, it's really concerning, and the negative impact on health and the economy is certainly seen. Today, a scientific seminar was presented by Professor Kebede Amenu, essentially targeting staff and students of the College of Veterinary Medicine and Agriculture of Addis Ababa University, and it was open virtually and in-person for those potentially interested. The title of the seminar presentation was "Food Safety Improvement Intervention in Low-and-Middle Income Countries: The Question of Sustainability." It was an insightful presentation that assessed the disease burden due to food safety and its economic aspects and gave suggestions for intervention and sustainability. The title I used above this topic: "3 Pathogens, 1% GDP," is about the impact of only 3 food pathogens which have an effect of 0.9% on National GDP (nearly 1%). We all know that there are numerous food pathogens. How could the number be elevated if all are added to the research mentioned! It's huge!! Among most of the things assessed by the seminar with the attractive and experienced presentation of Prof. Kebede, it was a new point of view for me that how the non-transparency of the informal food market is affecting the safety of our homes! Since we don't have food labels in our ጉሊት or ልኳንዳ, no standard, and no law enforcement, there is no means for the society to check the safety of the food in front of them before purchasing. This obviously has a negative impact. In Prof. Kebede's speaking, it is the culture that comes from the heart that can make a change but not knowledge from the head. I believe that advocacy and awareness made through any means of communication media should be considered helpful and assessed carefully since it is a vital means to reach out to the community's heart to make a culture. Prof. Kebede suggested three things for my question: "How should we use mainstream and social media to reach out to the community for intervention?" To make the long short: - Don't panic the society by sharing only the hazard - Use influencers and fun for education - Focus on the positive impact instead of blaming. Thank you, Prof. Kebede Amenu, for such a wonderful seminar and also my college and Dr. Fufa Abunna for the humble hosting. Looking forward to such kind of discussions. Kudos🙏 Yared E. (4th year DVM student)
Hashtags
ታትሟል ዲሴም 27
#አንረሳሽም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና እና ግብርና ኮሌጅ የሁለተኛ አመት DVM ተማሪ የነበረች እህታችን ሳሮን ኤርሚያስን በማጣታችን ልባችን እጅጉን አዝኗል።💔 ለቤተሰቦቿ፣ ለጓደኞቿ ብሎም ለመላው የCVMA ማህበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን። ነፍስ ይማር!
Hashtags
#Advocacy #HaSab ውረድ ወደ መሬት! አሁን አሁን አዲስ ነገር ሳነብ ወይንም ከመምህሬ ስሰማ አንድ ሀሳብ ደጋግሞ በምዕናቤ ይመላለሳል:-'Ah, what if I had learned this earlier?!'🤦♂️ ብዙዎቹ ከጤና ጋር የተያያዙ ጉዳዎች በሀገራችን ለመላምት የተጋለጡ ናቸው። ሁሉም የመሠለውን ይናገራል። በርግጥ ከመላምት የተሻገሩ ባህላዊ እውቀጦች እንዳሉ ባይካድም.... እናም በልጅነት አእምሮም ይሁን ሁነኛ መረጃ በማጣት የብርቱካን ፍሬ ውጦ ከመችመች በአናቴ የዛፍ ቅርንጫፍ ተንዠረገገ እንደሚል ብላቴና ሆኜ ያሳለፍኩባቸውን ጊዜያት ሳስብ ፈገግ እላለሁ። ከነበርኩበት ላይብረሪ አልያም ከመማርያ ክፍል ወጥቼ ለማህበረሰቤ በሚያውቀው ቋንቋ፣ በሚረዳበት አዎድ "ይሄ የሆነው ለዚህ ነው፣ ይህ ማለት ይህ ነው!" ማለት ያምረኛል። ብዙውን ጊዜ የምንነጋገረው እርስ በእርስ ነው። (እዚህ LinkedIn ላይ ራሱ ስንት blog አነበብኩ ስንት የታተሙ ጆርናሎች አስደነቁኝ) በሞያዊ ቋንቋችን ባለን የትምህርት ደረጃ ልክ እንወያያለን እንከራከራለን ከድምዳሜ እንደርሳለን። የሚዘጋጁ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችም የሚሞሉት በባለሞያው ነው። ይህ እርስ በእርስ እንድንግባባ ቢያደርገንም ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ገና ብዙ እንደሚቀረን ጠቋሚ ነው። ለዛ ይሆን የመፍትሄ ሀሳቦቻችን መሬት የማይወርዱት? ዋናው ችግር ያለው መሬት ላይ ነው። ለመሬት እጅግ ቅርብ የሆነው ደግሞ አራሹ ነው። ህመም የጅማሮ ምልክቱን የሚያሳየው ቤት ነው። ቤት ውስጥ ያለው ደግሞ ቤተሰብ ነው። ኤኮኖሚው ሲዘም የሚያርደው የቤቱን ምሰሶ ነው። ምሰሶውን ቀጥ አድርጎ ለማቆም መሰሶ ካለበት መሄድ ያሻል። ስለዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫዎቻችን እርስ በእርስ ካለን መድረኮች የሚሻገሩ እና ማህበረሰቡ በማረዳው ቋንቋና አውድ የተተረጎመው ሆነው የሚዘጋጁ ለማድረግ ብዙ መስራት ያለብን ይመስለኛል። ባለሁበት የእንስሳት ጤና ዘርፍ - ስለተለያዩ ምርታማነትን የሚቀንሱ የእንስሳት በሽታዎች ( animal production and health) - ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በተዋሲያን የሚመጡ በሽታዎች (Zoonosis) - ስለ ጸረ-ተዋሲያን መድሀኒቶች በጀርሞች መላመድ ( antimicrobial resistance ) - ስለ ምግብ ደህንነት (food safety) - ስለ እንስሳት ደህንነት እና ፋይዳው ( Animal welfare and its impact ) - የማህበረሰብ ፣ እንስሳት እና አከባቢ ጤና ግንኙነት ( one health ) ማህበረሰቡን ለማስተማር ግንዛቤ ለመስጠት እና ለውጥ ለማምጣት ጽኑ ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ በጋራ መስራት እንችላለን። ያወቅነውን የማሳወቅ ሐላፊነት አለብንና! Advocacy for the community should be a slogan like "መሬት ላራሹ!" Lets connect on LinkedIn መልካም የረፍት ቀን!
ታትሟል ዲሴም 24
የተሻለ ነገር መፈልግ ፣ አርፎ አለመቀመጥ ፣ ሁለም የተለየ ነገር ለመስራት መጠማት ፣ ተሱፋ ሳይቆርጡያለትጋት በቀጣይነት መስራት፤ ህይወት መጨረሻዉ ሽልማቱ የላቀ ነው። ፕ/ር አለማየሁ ለማ፣ በልጅነቱ የነበረው የትጋት ህይወት፣ ለዉጥን የመፈልግ ማንነት፣ በማይመች ሁነታ ያሰለፈዉ የሂይወት ትዝታ፣ ነገሮችን በቀላሉ አይቶ አለማለፍ የነበረዉ ዝንባለ፣ በተግባር ካላዩ ወደሃላ የማይሉ ጀግንነታቸዉ፣ አልፎም ተርፎም ሰዉ የሰራዉን ለምን እኔ አልሰራም እስከ ማለት ደርሶ ራሱን ከታላላቅ ሳይንትስቶች ጎራ ለመመደብ ያደርገው ጥረት እና ሙከራ ፤ ይህንን ህይወት ትግላቸዉን በእንስሳት ህክማን ላይም ምን ያህክል እንዳስቀጠለበት፤ በመጨረሻም ባአስችገርና በታላቅ ስቃይ በምመስል ጉዞ በተከታታይነት በመሥራት ድል ያነሳበትን መንገድ ፤በማይጠገብ አደበታችው ዛሬ ስያዉሱልን ዉሎዋል። እንስሳት ህክምና የመረጥኩት በልጅኔተ ነው። ቢሾፍቱ ከተማ ተወልጀ በማደጌ ፤ ከዉጭ ሃገር የመጡ ባለሙያዎች ከተማዉ ዉስጥ ያሉ እንሲሳቶቹን ሲያክሙ በድምብ አይና እነሱ የለበሱት ነጭ ልብስና ከረባት እቀናለሁኝ ፤ አልፎ አልፎም ወደ ክልንኩ የታመሙ እንስሳቶችን ይዥ ስመጣም በዛሁ አጋጣም ሳይ ነበረና በቃ እነ እንደነሱ መሆን አለብኝ ቢየ ወሰንኩት። በመጨረሻም በሃሰቤ የጸናሁትና የተደሰትኩት ድቭም ሶስተኛ አመት ስማር ነው፡፣ ከዝህም ወሳነ ተንስቸ በአራተኛ አመት ጀምረ በወረቀት ላይ ያነበብኩት በተግባር ላይ ማየት ብዙ ጥረያለሁኝ፤ ለምሳሌ ሳርጄር ሰርቻለሁኛ፣ አንማል አናቶም ፣ ምርምርንም ጀሚረ ነበረ ተማር እየለሁኝ ሌላ ቢዙ ነገር በተማርነት ቆይታዬ ሰሪችያለሁኝ። በተማርነት ቆይታየ የሰራሁት ስራዎቼ በመጨረሻም በግቢው ዉስጥ እንድቀጥር እድርጎኛል። በህይወቴ ተሱፋ መቁረጥ የምባል ነገር የለም፤ ምናልባት ላዝን እችላለሁኝ እንጅ፣ አንደኛዉ በር ስዘጋ ሌለኛዉ በር አማራጭ መፈለግ እንጅ፤ ያለትጋት በተከታታይነት መስራት 'መሞከር' 'መሞከር' ነዉ እስክ ሳካ ድረስ። ይህ እነ እስከ አሁን ድረስ ያለፍኩበት መንገድ ነው። ፕኤችድ ሥሰራ እንኩዎ በትግል ነዉ ጀምረ የጨረስኩት፤ ምንም ሳይኖረኝ አፕላይ አድርገ ሰዎች እያሾፉኝ " ድሃ ሆነህ ጀምረሃል ድሃ ሆነህ ትጨርሳለህ ስሉኝ'' እነ ግን ወደፍቱን ብቻ እያየሁኝ ተሱፋ ባለመቁረጥ ታግየ፤ በመጨረሻ ስመረቅ እነሱ ካሉት ተቃራን እንድሆን አድረገሃለሁኝ። ስለዝህ እነንተም ባመንችሁበት ነገር ላይ በቀታይነት ሳትታከቱ ሞክር ሞክር ድሉ በመጨረሻ የእናንተ ነዉና። ተሱፋን ባለመቁረጥ የህይወት ትርጉም በተግባር ያዩ፣ በተቃራን በቀታይነት በመስራት በነገሮች ላይ ድል መቀዳጀት የቻሉ ሰው ሆነህ፤ ለእኛ ትልቅ የህይወትህ ተሞክሮ ሳካፈልከን ከልባችን የሆነ ሚስጋና ይድረስህ እንላለን ፕ/ር አለማየሁ ለማ። ከተናገራቸው በጥቅቱ ነው!! ተጻፈ በአብርሃም አሰፋ! #3H-Initiative #"አዕምሮውን፣ ልቡን እና እጁን ተጠቅሞ ለማህበረሰቡ መፍትሄ የሚያመጣ ትውልድ እንፈጥራለን!!!"
Hashtags
ታትሟል ዲሴም 16
#HaSab #Experience_sharing በመጀመሪያ ይሄንን በጎ ተግባር በመደገፍ ፈጣሪ ከሰጣችሁ የህይወት ጊዜ መካካል ከ-120 ደቂቃ በላይ ጊዜያችሁን መስዋዕት በማድረግ ይሄ በጎ ተግባር የፀነሰውን እና የሚወልደውን በጎ አላማ ደግፋችሁ ለማዋለድ እና ለማረስ እኛ ጋር የተሰማራችሁ ሁሉ በ-3-H Initiative ስም ከልብ እናመሰግናለን። ዛሬ እኛ 3-H-ኦች ፣ የዕለቱ ተጋባዥ የክብር እንግዳችን (Prof. Alemayehu Lemma) እና የተነገረው የዕለቱ መልዕክት የሚመለከታቸው ተሳታፊ ተማሪዎቻችን የነበረን የጋራ የአብሮነት ጊዜ It was really ineffable and ethereal. ተጋባዥ እንግዳችን (Prof. Alemayehu Lemma) ተማሪዎችን ይመለከታሉ ብለው የሚያምኑባቸውን የእሳቸውን የህይወት ታሪክ እና ተሞክሮ ማለትም ያጋጠሟቸውን መሰናክሎች ፣ ያለፉባቸውን ውጣውረዶች እንዲሁም እሳቸው አሁን ካሉበት ደረጃ እንዲደርሱ ያደረጋቸውን እና ያስቻላቸውን ጥሩ አጋጣሚዎች በጥሩ ለዛ እና በማራኪ አንደበት ለታዳሚያን አቅርበዋል። እሳቸው ከተናገሯቸው ንግግሮች መካከል የተወሰኑትን እነሆ :- # " U guys have to be persistent and u have to have consistency in order to get what u want ur life" # " ተሰፋ መቁረጥ የሚባለው ነገር በኔ Dictionary ውስጥ አልነበረም" # "ሁሉን ነገር ለመሞከር አላመነታም ፤ የተማርኩትን ነገር እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ወደኋላ አልልም ነበር" # "Failure/ውድቀትን እንደ-ጥሩ አጋጣሚ ከመጠቀም ባለፈ ተስፋ አስቆርጦኝ አያቅም" # "የደሀ ልጅ ሲኒማ ቤት ላይብረሪ ነው ፤ ላይብረሪ ገብቶ Encyclopedia እና ሌሎች ትምህርት አዘል ቁምነገሮችን መቅሰም እና መሸመት በጣም እወድ ነበር While I was in University" # "የእናንተ grade እናንተን አይወስንም ፣ ትክክለኛውንም የእናንተን ማንነት አይናገርም ፤ Ur grade doesn't define u" ከላይ ለመጥቀስ የተሞከሩት ሀሳቦች Prof. Alemayehu Lemma ዛሬ ከእኛ ጋ በነበራቸው ቆይታ ከእሳቸው አንደበት ከፈለቁት ወርቃማ ንግግሮች መካከል የሚጠቀሱ እና በማይሆን ጭንቅላት ውስጥ ገብተው እንዳይባክኑ የሚያሳሱ Powerful thoughts ነበሩ ፤ The most exciting thing is that እዛ ተሰብስበን የነበርነው ስብስቦች ሀገርን ከ-ውድቀት እንዲሁም ትውልድን ከጥፋት ለመከላከል የተለየ ግን አንድ አይነት አስተሳሰብን ሲያራምድ ፣ እያራመደ እና ለማራመድ ያሰበ ስብስብ ነበር። ከ-Prof.Alemayehu Lemma ጋር ከነበረን የጋራ እና የአብሮነት ጊዜ በኋላ ተማሪዎች ስለ-ፕሮግራሙ የነበራቸውን የልብ ትርታ እና አስተያየት ለማወቅ በግል እና በቡድን አስተያየታቸውን ከ-አንደበታቸው በሚፈልቁ ቃላት ለመገምገም ጥረት አድርገን ነበር ፤ እናም ያገኘነው response አበረታች እና ይበል የሚያሰኝ ነው። ከተማሪዎች አስተያየት መካከል የተወሰኑትን ጀባ ለማለት ወደድን፦ - " Dedicated መሆንንና የህይወትን ጥፍጥና ሰው በመሆን ማጣጣም እንዳለብኝ ተረድቻለሁ" ሳሙኤል ይፍረደው-3rd year DVM - " ፍዳየን ብበላም የምፈልገው ነገር እስኪሳካ ተስፋ መቁረጥ እንደሌለብኝ" ባድማው ይታይህ-4th year DVM - "እስካሁን መኖር እንዳልጀመርኩ እና ከ-አሁን በኋላ ግን መኖር እንዳለብኝ ተረድቻለሁ" ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ተማሪ - " የህይወቴን ማርሽ የምቀይርበትን ዲስኩር አግኝቻለሁ" ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ተማሪ - "On Dec 16,2023 Everyone one was over the moon and on cloud nine by the event that was held on year 5 class. We really had a whale of time" Someone amongst of today's participant. ከላይ የተጠቀሱትን እና ከላይ የተጠቀሱትን መሰል ሀሳቦች እና አስተያየቶች ከተለያዩ የተማሪ አንደበቶች ለማግኘት የቻልን ቢሆንም ለማቅረብ የተገደድነው ግን የተወሰኑትን ብቻ ነው። የ-Prof.Alemayehu Lemma-ን recorded voice /ድምጥ በቅርቡ በዚሁ በ-3-H initiative የ-telegram group ላይ የምንለቅ መሆኑን ከወዲሁ እያስታወስን ስለነበረን የአብሮነት ቆይታ በድጋሚ በ-3-H initiative ስም ለማመስገን እንወዳለን። "Positive ነገሮችን በጭንቅላቱ አስቦ ፣ በልቡ አመዛዝኖ ፣ በእጁ ተግባር ላይ የሚያውል እንዲሁም ሀገርን ከውድቀት የሚታደግ እና ትውልድን ከጥፋት የሚከላከል ትውልድን እንቀርፃለን።" 3-H initiative #3_H_Initiative t.me/Head4Heart4HandInitiative ተፃፈ በ-Jemal D. Mengistu (James)
ታትሟል ዲሴም 16